Friday 16 November 2018

ስለ የዩኒቨርሲቲ ምደባ …

የታወቀ ችግር አለ…

ልጁ በ18 ዓመቱ ከወላጆቹ ቤት ለመጀመርያ ጊዜ ወጥቶ ወደ ሩቅ ሀገር ዩኒቨርሲቲ ይላካል። ከዛ ታላቅ ፈተናዎች እና አደጋዎች ይጠብቁታል። ብቸኝነት፤ ጥካት፤ ጭንቅ፤ ውጥረት፤ ስጋዊ ፈተኖች፤ ወዘተ። ዩኒቨርሲቲ እያለ በቀለ የለመደውን የቤተሰብ፤ ዘመድ እና በጠቅላላ የአካባቢ ድጋፍ የለውም። የሚደርሱበት ችግሮችን ከሞላ ጎደል ብቻውን መውጣት ይኖርበታል። አንዳንዱ ልጅ ፈተናውን ይወጠዋል አንዳንዱ ደግሞ ፈተናው ይውጠዋል።

መሰረታዊው ችግር ይህ ነው፤ «ለሰው ልጅ ከትውልድ ሀገሩ ተነቅሎ ብቻውን ሌላ ሩቅ ቦታ መሄድ ኢ-ተፈጥሮአዊ ነው»። ይህ «ስደት» ጎጊ ብቻ አይሆን «ኢ-ተፈጥሮአዊ» ነው። የሰው ልጅ በተፈጥሮ ወላጅ እና እህት ወንድሞች ብቻ ሳይሆን ዘመድ አዝማድ እና መንዳር አለው። ከነዚህ መሃል ሆኖ ነው ጤናማ ኑሮ መኖ የሚችለው።

ለዚህም ነው በሰው ልጅ ታሪክ የትውልድ ቦታን ትቶ ብቻውን ተሰዶ ሌላ ቦታ መሄድ የሌለው። ሰው ከተሰደድም 1) በታላቅ ችግር ምክንያት ነው የሚሰደደው እና 2) ብቻውን ሳይሆን ከመላ ቤተሰቡ እና መንደሩ ጋር ነው አብሮ የሚሰደደው። እንጂ የሰው ልጅ ብቻውን ቤቱን ትቶ አይሄድም።

ሁለተኛው ችግር ደግሞ ቤታቸውን ትተው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚሄዱት ገና ልጆች ናቸው። ቤተሰብ የመሰረቱ ጎልማሶች አይደሉም። ብዙዎቹ ሃላፊነትም አለመዱም። «ተማሩ እና እራሳችሁን ቻሉ» እየተባሉ ከሌላ ሃላፊነት ነፃ ሆነው ያደጉ ናቸው። እንደ ድሮ ልጆች የበሰሉ አይደሉም። ሽፋናቸው የበሰለ ይመስላል ግን ጥሬ ናቸው።

ሶስተኛ ችግር… በተፈጥሮ የሰው ልጅ ላቅማዳም ካለፈ የትወሰነ ዓመት በኋላ ቤተሰብ ይመሰርታል። እንደገና ይህ ጠፈጥሮ ነው ነአ ተፈጥሮን መታገል አጉል ነው። እነዚህ ልጆች ኃይለኛ የስጋዊ ፈተና አለባቸው። ብቻቸውን ዩኒቨርሲቲ ሲሄዱ ፈተናው ይበልጣል። ገቤተሰቦቻቸው ጋር ቢሆኑ እና በሃላፊነት እና ድጋፍ በከበቡ ይሻላል። ቢያንስ ለተወሰነ ጊዜ ፈተናውን ተቆጣጥረውት ትምሕርታቸውን ሲጨሩሱ ወደ ቤተሰብ ምስረታ መሄድ ይችላሉ።

በነዚህ ምክንያቶች ልጆችን ከቤተሰብ ነቅሎ ወደ ሩቅ ዩኒቨርሲቲዎች መላክ አይመረጥም። እነ ልጆቼ ከቤት ሆኖ ተምረው እንዲዳሩ ነው ፍላጎቴ። ይህ ትክክለኛው ተፈጥሮአዊ መንገድ ነው ብዬ አምናለሁ።

ይህን ሁሉኡ ስል የፖሊሲ አውጪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ እንደ ህዝብን ማስተዋወቅ እና ማቀላቀል መንገድ እንደሚያዩት ይገባኛል። ጥሩ አላማ ቢሆንም ጉዳቱ ከጥቅሙ የሚበልጥ ይመስለኛል። ቢያንስ አስተማሪዎችን የመመደብ እድል መስጠት ነው። እድሜአቸው ትልቅ በመሆኑ ምናልባትም ቤተሰብ ስላላቸው ከባድ ቢሆን ይሻላል።

No comments:

Post a Comment

ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!