Monday 20 September 2021

ምእራቡ ለምን ኢትዮጵያን ኢትዮጵያዊያንን ትንቃለች

የምእራቡ/ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ያላቸው አቋም እንደዚህ ፅንፍ የያዛ የሆነው አንዱ መክነያት ለኢትዮጵያ በተለይም ለኢትዮጵያዊነት የፖለቲካ ጎራው ያለቸው መጠን የለሽ ንቀት ነው። ኢትዮጵያ/ ኢትዮጵያዊነት ምንም አቅም የለውም፣ በጣታችን ገፋ ካርግነው ይፈራርሳል የሚል ድምዳሜ ላይ ከደረሱ ቆይተዋል። ይህ ድምዳሜ ላይ የደረሱበት ምክነያቶቹ ባጭሩ ይህን ይመስላሉ፤ 

1. በ1983 የደርግ ጦር ባንዴ መቅለጡ፣ 
2. ህዝቡ ህወሓትን ከሞላ ጎደል በበቂ ሁኔታ አለማታገሉ፣
3. የኢትዮጵያዊነት ጎራው ፖለቲከኖች እርስ በርስ ሲፋጁ ለ30+ ዓመት አቅመ ቢስ ሆነው ሲቆዩ፣ 
4. 8%ን "የወከለው" ህወሓት ሀገሩን በቀላሉ ሲገዛ፣ 
5. የህወሓትና የሻብያ ዲያስፖራ የፖለቲካ ተሳትፎ የኛን በአስር እጥፍ በልጦ ሲገኝ። ለምሳሌ ሲጠየቁ ባንድ ቀን 20 ሚሊዮን ሲያዋጡ የኛ ዲያስፖራ ደግሞ በ27 ዓመት ጠቅላላ ሶስት ሚሊድንም ያላዋጣና ሳይደራጅ መቅረቱ፣
6. "በቅኝ ግዛት ያልወደቀችው ኢትዮጵያ" የስንዴና ስኮላርሺፕ ለማኝ ሆና ስትቀር፣
7. ዛሬም አንዳንድ ኢትዮጵያዊ ነን ባዮች መንግስትን ለማዳከም ይጥራሉ።

ምእራባውያን ይህን ሁሉ አይተው ነው ኢትዮጵያም (አማራውም) ደካማ አቅመ ቢስ ናቸው ብለው የደመደሙት።

በተጨማሪ የምእራቡ የኢትዮጵያ " አዋቂዎች" በኢትዮጵያ (ለነሱ አማራ) ባህል ጠንካራና አስፋሪ ቋንቋ ነው የሚሰራው ብለው በለብለብ ጥናቶቻቸው ደምድመዋል። ለዚህም ነው የአሜሪካ መንግስት መግለጫዎች ባልሰለጠነና ተራ ቋንቋ የተጻፉት።

መእራቡ ኢትዮጵያን እንደሚንቅ ማውቁ ምን ይጠቅመናል? እውነታንና የራስን ሰህተቶችን የላወቀ ስህተቶቹን ይደግማል፣ ችግር ውስጥ ይገባል፣ ሊጠፋም ይችላል። ከላ የተጠቀሱት የተናቅንበት ምክነያቶች ሁሉ እኛ ኢትዮጵያዊያን በራሳችን ላይ የመጣናቸው ችግሮች ናቸው። ከ1968-83 እርስ በርስ ሰንፋጀ እራሳችንን አጠፋንና በሩን ለጠላቶች ከፈትን። እና ህወሓትን ከተራ ሸፈታ ወደ ሀገር ገዥነት አጎለበትን። እኛ ነን ይህን የደረገ ነው፤ ባንከፋፈል ኖሮ የትም አይደርሱም ነበር። ወነኛው መማር ያለብ ትምሕርት ካሁን በሗላ የመከፋፈል ባህሪአችን መጥፋት አለበት። የህልውና ጉዳይ እንደሆነ መረዳት አለብን።

ሁለተኛ መማር ያለን ትምህርት ምን ያህል እራሳችን እንደጎዳንና ገና ጉድጓድ ውስጥ መሆናትን ነው። በጣም ብዙ የዓመታት ስራ እንዳለብን ማወቅ አለብን። ስራው ብዙ ስለሆነም ትእግስት እንደሚያስፈልግን አምነን መንግስትንም እራሳችንንም  መታገስ አለብን።