Wednesday, 7 February 2018

ሞኙ ህብረተሰብ

ከአባ ቲኾን (ሼቭኩኖቭ) መጸሃፍ Everyday Saints፤ «ሞኙ ህብረተሰብ»። ትርጓሜው የኔ አይደለም።
ሞኙ ህብረተሰብ

በአንድች ሰነፍና የተኛች ይቢዛንቲየም ከተማ: የጥሩውን እና የሽማግሌውን ጳጳስ ምክር ተቃውሞ እና ልመና ትንሽ እንኳን ሳይፈሩ የከተማው ሰዎች በሚሰሩት ግብረ ገብ መጣስና ህግ ማፍረስ ሀፍረተ ቢሶች ሆነዋል። እንደውም በጳጳሱ ላይ ሳቁበት በዕኩይ ስራቸውም ገፉት።

በመጨረሻም ሽማግሌው ጳጳስ ሞተ እና አዲስ ጳጳስ ተሾመላቸው። አዲሱ ተሿሚም የከተማው ሰዎች እስኪደነቁ እና እስኪያዝኑ ድረስ  ስርዓት የሌለው በቅንጦት የሚኖር ጉቦኛ ሆነ እና ደጉን እና ሟቹን ጳጳስ እንዲናፍቁ አደረጋቸው ።

በተደጋጋሚ የሚፈጽመውን ጉቦኝነት ማዋረድ ድብደባ እና ከሁሉበላይ ደግሞ ማመን ያቃታቸው ለከት የሌለው ረብሻ መቋቋም ባለመቻላቸው በአንድነት ሆነው ወደ እግዚአብሔር «ጌታ ሆይ እንደዚህ አይነት ጭራቅ ለምን ላክህብን?» በማለት ጮሁ።

እንዴት እንደሚጸለይም አያውቁም ሰለነበር ዝም ብለው ጮሁ። ከብዙ ጩኸት በኋላ ጌታ ለአንዱ የከተማው አባት ተገልጾ «ከእሱ የከፋ ለማግኘት ሞከርኩ ነገር ግን ለማግኘት አልቻልኩም» አለው።

No comments:

Post a Comment

ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!