Showing posts with label culture. Show all posts
Showing posts with label culture. Show all posts

Friday, 11 November 2022

ቅራኔአችሁን እንፍታላችሁ!

በተለይ ከ1997 ከቅንጅት ዘመን በኋላ ምእራባውያን ማለትም መንግስታት፤ ኤንጂኦዎች፤ ወዘተ ኢትዮጵያዊያን የግትርነት እና የቅራኔ ማባባስ ባህል አላቸው ብለው ያወሩ ነበር። በአንጻሩ እኛ ምእራባውያን በጠቅላላ የፖለቲካ ስልጣኔ በተለይም በቅራኔ መፍታት conflict resolution ጎበዝ ስለሆንን እናንተን ኢትዮጵያውያን እናስተምራችሁ አሉ። በርካታ ስብሰባዎች ትምሕርቶች በብዙ ገንዘብ ወጪ ተካሄዱ። ውጤቱ....

(በነገራችን ላይ እኔም በግሌ ይህ ባህላዊ ችግር አለን ብዬ አምኜ የፈረንጆቹን እርዳታ እንጠቀም ከሚሉት አንዱ ነበርኩኝ።)

ባህል ውስብስብ ነገር ነው። የእገሌ ባህል እንዲህ ነው የእገሌ ባህል እንዲያ ነው በደፈናው ማለት አይቻልም። ሁኔታዎች ሁሉንም ግለሰብም ቡድኖችንም ይቀይራል። እንሆ እነዚህ የቅራኔ መፍታት ባለሙያዎች ምእራባውያን ዛሬ ትክክለኛ ግትርነት ምን እንደሆነ እያሳዩን ነው። በከንቱ ዓለምን ንዩክሊየር ጦርነት ጫፍ ላይ አድርሰዋልና!

እኛ ኢትዮጵያውያን ወዲህ ወድያ ከማየት እራሳችንን ከምእራባውያን ይሁን ከምስራቃውያን ከማነጻጸር ወደ ራሳችን ተመልክተን በራሳችን እሴቶች ተጠቅመን እራሳችን ላይ ብንሰራ ይበጃል። ከሌሎች ጥሩ ነገር መማር ጥሩ ነው ተፈጥርዋዊም ነው። ግን ብዙ ጊዜ ይህ ከጥሩ ነገር መማር አልፎ ወደ ማነጻጸር ይሻገራል እና ሁለት «ኮምፕሌክሶች» ያሳድራል፤ 1) ሌሎች በደፈናው ይበልጡናል ብሎ ማሰብ 2) የራስን እሴቶችን አለማየት። እና ማነጻጸር አደገኛ ልምድ ይሆናል ከእውነታ እንድንርቅ ያደርገናል። ስለዚህ ብዙ ግራ ከኝ ሳንመለከት ችግራችንን በራሳችን በቂ የሆኑ እሴቶች መፍታት ጥሩ አካሄድ ይመስለኛል።

Tuesday, 13 November 2018

ወግ እና ማንነት ሲናቅ ግብረ ገብ ይጠፋል

በደርግ ዘመን የተደረገውን ማሰቃየት (torture) ይታወቃል። በወያኔም ዘመን እንዲሁ መቀጠሉን ሁላችንም እናውቃለን መንግስት አምኖ የፍትህ እርምጃዎች መውሰዱ ታላቅ እርምጃ ቢሆንም።

ለምንድነው ይህ የተከሰተው የሚለውን ጥያቄ በተለያየ መንገድ መመለስ ይቻላል። አንዱ መልስ የራስን ባህል፤ ወግ፤ እና ታሪክን ንቆ እና ትቶ የሌላ የበአድ መንገድ መከተል ነው።

ኃይለ ሥላሴ (የሚመጣውን ችግር በደምን ሳይረዱ?) ራሱን የሚጠላ ፈረንጅ አምላኪ ልሂቃን ትውልድ ከፈጠሩ በፊት ዛሬ የምንሰማው አንየንት የግብረ ገብ ጥሰት እና ማሰቃየት አልነበረም። ሰው ወህኒ ቤት ይታሰራል፤ ግዞት ይላካል፤ ማናልባትም ይገደላል። እነዚህ ነገሮች በአግባብም አለአግባብም ይደረጉ ነበር። ግን «ባህላዊ» ናቸው ማለት ይቻላል፤ ለመቶዎች/ሺዎች ዓመታት የሚደረጉ ነገሮች ነበሩ።

ዘመናዊው ትውልድ ግን የበአድ ባህሪዎችን አመጣብን። በፍፁም የማይታሰቡ አስተሳሰቦች አመጣ። በፍፁም የማይደረጉቶች አመጣ። እራሱን፤ ማንነቱን፤ ኢትዮጵያዊነቱን ሳተ። ወደ ኢ-ኢትዮጵያዊነት ሙሉ በሙሉ ገባ። ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ድርጊቶች ፈጸመ። ለዚህም ነው ዛሬም ቢሆን ኢትዮጵያዊያን ስለነዚህ ድርጊቶች ሲሰማ እጅግ እሚደነግጠው።

ይህን ስል በባህላችን ችግሮች የሉም ማለቴ እንዳልሆነ መቼም ሁላችሁም ትገነዘባላችሁ! ሆኖም ችግሮችን ቀርፎ ማውጣት እና ጥሩ ነገሮችን ይዞ መጓዝ ነው እንጂ ሁሉንም አራግፎ ወደ ሌላ መንገድ መሄድ አደጋ ነው። ይህን አደጋ በተለያየ መንገዶች አይተነዋል እያየነውም ነው።

ይህ የማሰቃየት ታሪካችን እንዳይደገም አንዱ መፍትሄ ወደ ወጋችን፤ ወደራሳችን መመለስ ነው።

Wednesday, 10 October 2018

የቅራኔ መፍታት (conflict resolution) ጉድለታችን

አንዱ ከብዙ የጠ/ሚ አብይ አህመድ ልዩ የሚያረጋቸው ችሎታዎች የቅራኔ መፍታት አቅማቸው ነው። ትዕቢት፤ ቂም፤ አሉታዊነት፤ ትቶ የሁሉንም ትቅም የሚያስከብር ለሁሉም ተመራጭ የሆነ ግባ ላይ በማተኮር ችግሮችን ፈትተዋል አሁንም እየፈቱ ይገኛሉ። ይህ አቅማቸው ከኢትዮጵያ ፖለቲካዊ መሪዎች ለዘመናት ታይቶ አይታወቅም (https://ethsat.com/2018/10/ethiopia-soldiers-show-up-unannounced-at-national-palace-pm-orders-pushups/)።

@Samuel Abebe (በዚህ ትችት ላይ https://www.facebook.com/abdurahman.ahmedin.7/posts/2120966214582614?comment_id=2121015731244329) ሁላችንም በውስጣችን የምናስበውን ታላቅ ጥያቄ ጠየቀዋል፤

«መለወጥ ስህተትን ከመቀበል ይጀምራል ይባላል ትልቅ ስህተት ተፈጽሞም ከቅንጅት አመራሮች ስህተቱን ተቀብሎ እዚህ ላይ ይህን ባንሳሳት ኑሮ የሚል አመራር እንዴት ይጠፋል? ሁሉም ወደ ሌላ ሰዉ ጣቱን ይቀስራል፡ እኛስ የትኛዉን አምነን የትኛዉን እንቀበል?»

ዋና እና ተገቢ ጥያቄ ነው። ብስለት እና እውቀት የሞላው። በማንኛውም ቅራኔ አንድ ጥፋተኛ እና ሌላው ንፁሃን የለም (there are two or more sides to any conflict)። ይህን ሃቅ ማንኛውም ስለቅራኔ የሚያውቅ ባለሙያ፤ ማንኛውም የካህን፤ ማንኛውም አስተዳዳሪ፤ ማንኛውም ወላጅ የሚያውቀው ነው። ግን ብናውቀውም እንዳማናውቀው አድርገን ነው የምንኖረው። ቅራኔ ውስጥ በተገኘን ቁጥር እራሳችንን ፍፁም ንፁህ ሌላው ፍፁም ጥፋተኛ አድርገን ነው የምንቆጥረው።

ይህ ከገባን በቅንጅት ቅራኔ ህሉም ተሳታፊዎች የተወሰነ ሚና መጫወታቸውን ሊገባን ይገባል። የፈረደበት ልደቱ ጥፋት ብቻ ሊሆን አይችልም። ዋናው ችግር የሱ ነው ቢባልም ያንን ችግር ማስተናገድ አለመቻል በራሱ ትልቅ ድክመት ነው! መታመን ያለብት እና ይቅርታ የሚጠየቅበት ድክመት ነው። ታላቅ መማርያ የሚሆን ድክመት ነው።

እንደ ቅንጅት አይነት ታላቅ ድርጅት፤ እጅግ ግዙፍ የሆነ የሀገር ሃላፊነት ያለው ድርጅት ሲፈርስ ሁሉም በአመራር ያሉት በመፍረሱ ሚና ተጫውተዋል እና ሁሉም ድክመታቸውን አምነው ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል። እኛም ደጋፊዎቻቸው እንዲሁም። ያደረግነውን ስህቶቻችንን ካመንን በኋላ ብቻ ነው መማር የምንችለው እና እንዳንደግማቸው ማድረግ የምንችለው።

የቅንጅት ታሪክ ከብዙ የሀገራችን ፖለቲካ የቅራኔ መፍታት አለመቻል ታሪኮቻችን አንዱ ነው። እንዳውም በኔ እምነት የፖለቲካ እና ማህበራዊ ችግሮቻችን ዋና ጎልቶ የሚታየው ምክንያት «የቅራኔ መፍታት (conflict resolution) ጉድለታችን» ነው። በዚህ ዙርያ ብዙ ተጽፏል እና ተነግሯል ግን በቂ አልተደረገም። ዛሬም የምናያቸው ነገሮች አሉ፤

1. አንድ «አቋም»፤ ርዕዮት ዓለም፤ አስተያየት ኖሮን አብሮ መስራት አለመቻል
2. የራሳችንን ጥቅም ጎድተን ቂማችንን ለመወጣት የምናደርጋቸው ስህተቶች
3. የጋራ ማሸነፍን ከመፈለግ (አሁንም የራሳችንን ጥቅም ቢጎዳም) ሌላው እንዲሸነፍ መመኘት እና መስራት
4. ፖለቲካን እንደ ሃይማኖት ፍፁም እውነት እንዳለው መቁጠር።

የፖለቲካ አካሄዳችን እንዲሻሻል ከተፈለገ ስለነዚህ ጉዳዮች መያየት እና መፍትሄ ማግኘት ግድ ነው።

ቅራኔ መፍታት ለኛ ኢትዮጵያዊያን አዲስ ነገር አይደለም። የድሮ ንጉሶቻንን አድርገውታል። ይህን የሚያስፈጽሙ በርካታ ባህላዊ መንገዶች አሉን። ከሃይማኖታችን ደግሞ መሰረታዊ ቅራኔ መፍታት ምክንያቶችንም ዘዴዎችም አሉ። ለምሳሌ በክርስትና «ንስሃ» ማለት ማለት 1) ስተትን ማመን 2) እንዳይደገም 3) ሌላው እንዲገባው 4) እራስን ለማረም 5) እራስን ለማወቅ ወዘተ። ውየንም «አለመፍረድ» ማለት 1) ለሌላው መቆርቆር (empathy) 2) የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ ችኩሎ አለመድረስ 3) ጣት ጠኩሞ የራስን ችግር መርሳት ወዘተ።

ስለዚህ አሁን ማድረግ ያለብን እነዚህን (ምናልባት የተረሱ) ባህላዊ እሴቶችን እንደገና ማስነሳት እና ማሰራጨት ነው። ከባድ ስራ ነው ግን ምርጫ የለንም!

http://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/09/blog-post_21.html

Friday, 21 September 2018

ጎጂ ፀባዮች ላይ ዘመቻ ማካሔጅያ ጊዜ አሁን ነው!

12 ዓመት በፊት በ1998 ቅንጅት ሲፈራርስ በንዴት እና በሃዘን በሌላው የብእር ስሜ (ደሳለኝ አስፋው) የጻፍኩት ጽሁፍ። አሁንም የሚያስፈልገን ይመስለኛል።

የኢትዮጵያ ብሄርተኞች በተለይም ግንቦት ሰባት፤ ሃላፊነታችን ግዙፍ ነው። አሁንም አንዳናጠፋ (http://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/07/blog-post_31.html)። ከበፊቱ እንማር።

(አማርኛው ከታች ይቀጥላል)
---------------------------------------------

Time to Declare War on Dysfunctional Behaviours


The recent controversy surrounding Kinijit supporters in the diaspora—Kinijit USA (KUSA) and Kinijit International Leadership (KIL)—is the latest in a history of feuding and infighting among Ethiopian political interest groups and parties. Indeed, over the past few decades, we have seen countless political organizations created, only to be shortly disbanded, abandoned, or rendered ineffective, often because of intra-group conflict—conflict among the membership—and an inability to resolve conflict.

I believe that these conflicts are a fundamental reason for the absence of democracy in Ethiopia today. Indeed, it is these conflicts, magnified to a national level, that have resulted in dictatorship after dictatorship in Ethiopia. Endless feuding and infighting from the grassroots level on upwards have made it difficult for Ethiopians to attain the organic solidarity necessary to build and sustain the institutions necessary for democracy. I think it is imperative that pro-democracy activists make awareness of intra-group conflict a top priority in the struggle for democracy. But before I make my case, I would like to describe the nature of the problem in greater detail.

Here are a few interesting points. First, the intra-group conflicts we see in Ethiopian collectives are seldom caused by differences in ideology, organizational structure, or other substantive reasons. Nor are they confined to organizations whose members come from a wide variety of backgrounds and perspectives. Indeed, the most virulent conflicts occur in apparently homogenous groups whose memberships have not only similar ideologies, but similar frames of reference, perspectives, and interests. The current KUSA/KIL conflict, for the most part, is an example of this.

Another interesting point is that such conflicts occur just as much in the Ethiopian diaspora as they do in Ethiopia. This is interesting because, in the diaspora, factors such as poverty, political oppression, lack of education, etc., do not exist.

Finally, intra-group conflicts are not restricted to organizations of a political nature. They are found in all types of Ethiopian collectives. We can observe chronic feuding and infighting in families, extended families, non-political civic organizations such as professional associations, churches, local community organizations, charity organizations, and others.

So, why is there so much intra-group conflict, characterized by personal feuds and infighting, in Ethiopian society? And when there is conflict, why is conflict resolution so difficult? One explanation is that we have been brought up in an environment where certain dysfunctional behaviours that hamper effective communication and cause conflict are the norm. Below is a list of some of these behaviours that I have observed. I ask readers to reflect on whether you have seen them in yourself; in others; in meetings and other group settings.
  1. Personalization of issues: This is when we are unable to conceptually distinguish between people and their ideas or thoughts. For example, if someone objects to a suggestion I make, I see the objection as personal attack, not as a simple difference of opinion. In response to the perceived personal attack, I respond with a personal attack, instead of discussing the issues. Hence, the initial disagreement over ideas turns into a personal struggle, and because it is a personal struggle where pride and survival are at stake, we end up unable to constructively ‘agree to disagree’. Groups whose members find it difficult to ‘agree to disagree’ become paralyzed by feuding and infighting and eventually collapse.

  2. Parochialism (weganawinet): We tend to irrationally favour those from our own kin or wegen—family, village, team, ethnic group—no matter what the cost. For example, if a person from my wegen has a conflict with a stranger (be’ad), a person outside my wegen, I automatically favour my colleague, no matter what the substance of the disagreement. Furthermore, I extend the conflict to a dislike of the stranger and his entire wegen—his family, friends, place of employment, ethnic group, etc. This is the root of blood feuds (dem). Parochialism within organizations leads to ineffectiveness, as decisions are made based on who supports the decisions, rather than on their merit. It also leads to organizations being split into smaller and smaller factions, and eventually collapsing. For example, an organization may split into two main factions. Factions will develop within those factions, and further splitting will occur, until the organization fails.

  3. Chronic suspicion and mistrust (teretaray): We view each other first and foremost as potential threats. With such a heightened level of threat-awareness, any idea or thought, no matter how innocuous, is quickly considered to have negative ulterior motives behind it. Even the most innocent comments by the closest of friends can be misinterpreted as sinister, resulting in the breakup of fruitful relationships. This behaviour is a fundamental cause of conflict in a group setting. By definition, no group can be effective without trust.

  4. Paranoia: As we view everyone as a threat, we tend to disproportionately develop a paranoid outlook in our interaction with others, with the ‘threat’ foremost in our minds in all our interactions. This paranoia, in a group setting, results in organizational paralysis, with everyone looking over their shoulder and hesitant, instead of working towards the common goal.

  5. Lack of empathy and empathetic understanding: Empathy, the ability to identify with or understand others’ situation, feelings, and actions, is critical for effective communication and teamwork. However, in Ethiopian society, we are not sensitized to the importance of empathy. We do not ask questions such as ‘what in his background might have caused him to react this way’, or ‘what would I have done in his shoes’. This leads us to make erroneous judgements based on incomplete understandings, which leads to misunderstanding and conflict within groups.

  6. Lack of suspending judgement or giving others the benefit of the doubt: Suspending judgement is fundamental to effective communication. Unfortunately, the combination of chronic suspicion and lack of empathetic understanding lead to the absence of awareness about the concept of suspending judgement and giving others the benefit of the doubt. If someone does something we do not understand, we do not ask, ‘Perhaps there is something he knows that I don’t,’ or ‘Let me wait and see before making a judgement.’ We judge hastily, without taking time to examine all possibilities. This results in erroneous judgements and personal conflicts.

  7. Character assassination (sem matfat and alubalta): Rather than addressing conflict directly, we chronically spread rumours and innuendo about those with whom we disagree. We engage in character assassination because we know that it is an effective weapon in our society. Since we do not give each other the benefit of the doubt, we tend to believe bad things about others! A strategy of muddying someone’s reputation will render them useless, as people will simply have had their existing suspicions confirmed. Obviously, character assassination quickly leads to infighting and paralysis in groups, a scenario with which most of us are familiar.

  8. Lack of openness: Openness facilitates effective communication. As Ethiopians, we are not open and forthcoming about our thoughts and expect the same guarded approach from others. This is related to our lack of empathy, which makes us afraid of being judged hastily and incorrectly if we speak openly. This fear leads us to be initially vague, unclear, and non-committal, which inevitably leads to communication gaps and communication breakdown, as others persistently try to interpret the hidden meaning of what we say, and often end up interpreting negatively and incorrectly. Lack of openness leads to misunderstanding and conflict.

  9. Holding grudges (qim and mequeyem): We tend to chronically hold on to personal grudges. Understanding or forgiveness of perceived affronts is seen as weakness, as it is assumed that everyone is and remains to be a threat. In a group setting, there are bound to be conflicts, and if people hold on to grudges, there can be no effective teamwork.

  10. Envy (mequegnenet): We hate it when others are better off than us in any context, but instead of struggling to improve our own lot, we work to reduce others’! This comes from our ingrained perception that everything in life is a zero-sum game. If someone is rich, it is because another is poor. If someone is happy, it is because another is sad. It is as if the world has been alloted a fixed amount of wealth, happiness, etc., and it has been ordained that everyone should have more or less the same amount. Failing this, the ones with more must have committed some kind of crime to improve their lot and the ones who have less must be cursed.

  11. Stubbornness and lack of compromise (getterenet): Because of our zero-sum view of the world, compromise is seen as a weakness. We do not understand the concept of compromise as a building block for future win-win endeavours. Instead, compromise is seen as a loss forever.
I am sure that all of us have seen first hand these behaviours manifested in various contexts. We have also seen the resulting conflicts in our various collectives, from families to religious groups to political organizations.

On the other hand, most of us in the diaspora have been exposed to non-Ethiopian collectives where, generally speaking, such conflicts occur far less often. We have also observed that these collectives are, as a result, far more effective and efficient than Ethiopian collectives.

In order to bring Ethiopian collectives, including Ethiopian pro-democracy and human rights organizations such as KUSA and KIL, to this level, it is crucial that we find a way to raise awareness that intra-group conflict is a fundamental barrier to democracy, to put an end to our dysfunctional group behaviours, and to promote positive, constructive behaviours that reduce conflict, increase our capacity for conflict resolution, and increase collective consciousness and organic solidarity.

To this end, as a first step, I suggest that all organizations draft a code of conduct document. The aim of this document should be primarily to raise awareness about dysfunctional behaviours, the problem of intra-group conflict, and the importance of effective communication. In addition, the code of conduct should provide guidelines of behaviour and conduct, along with explanations for the guidelines.

My second suggestion is that there should be a collective attempt to stigmatize dysfunctional behaviours in our everyday lives. For example, we must make it telek newur to attack anyone personally instead of addressing issues. We must not only refuse to listen to character assassination, but openly chastise and correct those who do it. In a charitable and constructive manner, of course—we have to keep in mind that most of us engage in such behaviour almost unknowingly, because of the culture we have grown up in. Unless sensitized to the ramifications of such speech and actions, we cannot become fully aware of the consequences.

I believe that these two actions alone will result in a significant reduction in the chronic feuding and infighting in our collectives and organizations. The resulting increase in organic solidarity and collective consciousness will, in due course, crowd out dictatorship at all levels of our society, including the political. The democratic culture at the grassroots will end up being reflected at the national level.

Indeed, imagine diaspora pro-democracy groups devoid of feuding and infighting. They would make great strides in improving the prospects for democracy in Ethiopia. Imagine that behaviours such as suspicion and paranoia were no longer the norm inEthiopia. Dictatorship, which thrives on suspicion and paranoia, would disappear shortly.

Doing away with dysfunctional behaviours and intra-group conflict is the only way to achieve democracy. To those who believe in democracy for Ethiopia, I say, we need an all-out campaign: Let us declare war on dysfunctional behaviours!

Dessalegn Asfaw

--------------------------------------------

ጎጂ ፀባዮች ላይ ዘመቻ ማካሔጅያ ጊዜ አሁን ነው!


ባሳለፍናቸው ብዙ አመታት ውስጥ ብዙ ድርጅቶች ተመስርተው አይተናል። ይሁን እንጂ የእነዚህ ድርጅቶች አባሎች በውስጣቸው የሚፈጠረውን ቅራኔ መፍታት ባለመቻላቸው ድርጅቶቹ እንደሚገባቸው ያህል አይሰሩም።

እኔ እንደተመለከትኩት እነኝህ ቅራኔዎች በኢትዮጵያ ውስጥና በውጭም በምንኖር በተለያዩ ኢትዮጵያውያን ስብስቦች ውስጥ አሉ። ስብስቦች ስል የፖለቲካ ድርጅቶችና ሌሎችም ታላላቅ ስብስብ ብቻ ሳይሆን፤ የቤተሰብ፣ የዘመድ፣ የጓደኝነት፣ የሞያ ማኅበራት፣ የሲቭል ተቋማት፣ የቤተክርስትያንና ሌሎች የሃይማኖታዊ ስብስቦች፣ የኮምዩኒቲ ድርጅትና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይጨምራል። ከላይ የጠቀስኳቸው ሁሉ ሥር የሰደዱ ውስጠ-ቡድን ቅራኔዎችና ሽኩቻዎች ይገኝባቸዋል።

እነዚህ ውስጠ ቡድን ቅራኔዎች የሚፈጠሩት እምብዛም በርእዮተ ዓለም፣ በድርጅት አወቃቀርና በአንኳር ምክንያቶች አይደለም። እነዚህ ቅራኔዎች የተለያዩ አመለካከትና አነሳስ ያላቸው አባሎች በመሠረቱት ድርጅት ውስጥ ብቻ የተወሰነም አይደለም። እንዲያውም ቅራኔዎች በይብስ የሚታዩት በርእዮተ ዓለም፣ በአመለካከት፣ በግንዛቤና በፍላጎት በጣም የሚመሳሰሉ ሰዎች ባሉባቸው ድርጅቶች ውስጥ ነው።

እነዚህ ቅራኔዎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንፀባረቁትን ያህል በውጭ አገር ባሉ ኢትዮጵያውያን ውስጥም ይንፀባረቃሉ። ይህ አስገራሚ ነው፡ ምክንያቱም በውጭ አገር ድህነት፣ የፖለቲካ ችግር፣ የአስተዳደር ጉድለት ወይም የትምህርት እጥረት ሳይኖር ቅራኔዎች ግን እንደ አገር ቤት መኖራቸው ነው።

ታዲያ ለምንድነው በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር በኢትዮጵያውያን ማህበረ ሰብ፣ በግላዊ አመለካከት ውስጠ ቡድን ቅራኔ የሚኖረው? እናም ውስጠ ቡድን ቅራኔ ሲኖር ቅራኔውን ማስወገድ ለምንድነው አስቸጋሪ የሚሆነው? ለዚህ አንደኛው መልስ እኛ በነዚህ ቅራኔዎች ውስጥ የምንኖር ሰዎች በመሆናችን እነዚህ ግንኙነትን ደካማ የሚያደርጉ ሽኩቻዎችና ጎጂ ፀባዮች የህልውናችን አካል ስለሆኑ ይሆናል። ማለትም ባህላችን የነዚህ ቅራኔዎች ምንች ስለሆነ ነው።

ከዚህ ቀጥሎ እኔ የተገነዘብኳቸው አንዳንድ ጠባዮች ተዘርዝረዋል። አንባብያንን የምጠይቀው እነዚህን ጠባዮች እናንተም በራሳችሁ፣ በሌሎች ሰዎች፣ በስብስቦችና በመሳሰሉ ስብሰባዎች ተገንዝባችሁ እንደሆን ነው።

1. ነገርንና ግለሰብን ማቆራኘት

ይህ ግለሰብንና የግለሰብን ሃሳብ ለይቶ አለማየት ነው። ለምሳሌ አንድ ግለሰብ የተቃውሞ ሃሳብ ከሰጠ የሃሳብ ልዩነት መሆኑ ቀርቶ ግለሰቡን ለማጥቃት ይሞከራል። ተቃውሞ የተነሳበትም ግለሰብ በአንፃሩ አፀፋዊ ጥቃት ለማድረግ ይፈልጋል። በመጨረሻም የሃሳብ አለመግባባት ወደግለሰብ ጥል ይሸጋገራል።ይህም ግለሰቦች ክብርና ህልውናቸው የተጠቃ ስለሚመሰላቸው ነው። ላለመስማማት መስማማት የማይችሉ ሰዎች በግለ ሰባዊ ፀብና ሽኩቻ ይሽመደመዱና ቡድኖች ይፈርሳሉ።

2. ወገናዊነት

የፈለገው ቢሆን ለምናውቀው ወገን፣ ቤተሰብ፣ መንደር፣ ቡድንና ዘር መወገን እንፈልጋለን። ለምሳሌ ወገናችን የሆነ ሰው ከሌላ ወገን ግለሰብ ጋር ቢጋጭ የነገሩን ሁኔታ እንኳን ሳናውቅ ወገንተኛነታችንን እናሳያለን። በዚህም ቅራኔ ምክንያት ጥላቻውን አስፍተን የተቃዋሚውን ወገን፣ ቤተሰብ፣ ጓደኞች፣ የሥራ ቦታ፣ ጎሳ እናወግዛለን። ይህ ለደም መፋሰስ ምንጭ ሊሆን ይችላል። ወገናዊነት ቡድን ያፈርሳል ምክንያቱም ውሳኔዎች በወገናዊነት እንጂ በትክክለኛነታቸው ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ወገናዊነት ድርጅቶችን ከፋፍሎ ድርጅቶቹን ያፈርሳቸዋል። ለምሳሌ አንድ ድርጅት ሁለት ቦታ ይከፈልና ሁለቱ ደግሞ ብዙ ቦታ እየተከፈሉ በመጨረሻም ባጠቃላይ ደርጅቱ ይፈርሳል።

3. ጥርጣሬ

በመጀመሪያ ደረጃ እርስ በእርሳችን የምንተያየው በጥርጣሬ መንፈስ ነው። በዚህም ምክንያት ጉዳት የሌላቸው ሃሳቦች እንኳን ከጀርባቸው ሌላ ነገር አላቸው ተብለው ይፈራሉ። ፍፁም የዋህ የሆነ የጓደኛ አመለካከት እንኳን በጥርጣሬ እንደ እርኩስ ሃሳብ ተተርጉሞ የዳበረ ግንኙነት ይፈርሳል። ይህ አይነት ጠባይ የደርጅቶች ውስጠ ቅራኔ መሠረታዊ ምክንያት ነው። ለእውነት ከሆነ መተማመን ከሌለ ምንም ዓይነት ድርጅት ውጤታማ ሊሆን አይችልም።

4. ፍርሀት

ሁሉንም ሰው እንደ አደገኛ ሰው ስለምናይ በአስተሳሰባችንና በአመለካከታችን ውስጥ ፍርሀት ይዳብራል። እንዲህ አይነት ፍርሀት ድርጅቶችን ሽባ ያደርጋቸዋል። ይህም የሚሆነው ሁሉም በፍርሀት እያመነታ ጉዳይን ከግብ ለማድረስ ወደፊት መሄድ ስለማይቻል ነው።

5. ተቆርቋሪ አለመሆን

የሌሎችን ስሜት፣ ተግባርና ሁኔታ ራሳችንን በሌላው ቦትና ሁኔታ አድርገን አለማየት ለሌላው አለመቆርቆርን ያመጣል። ተቆርቋሪ መሆን ለጤናማ ግንኙነት አስፈላጊ ነው። አንድ ሰው አንድ ነገር እንዴት ሊሰራ እንደቻለ ወይንም ደግሞ እኛ በሱ ቦታ ብንሆን ኖሮ ምን ማድረግ እነደምንችል እራሳችንን አንጠይቅም። ይህ ወደተዛባ ፍርድና ጎዶሎ ግንዛቤ ያመራና በቡድኖች ውስጥ አለመግባባትና ቅራኔን ይወልዳል።

6. ለመዳኘት ወይም ለመፍረድ መቸኮል

ለመዳኘት አለመቸኮል ለጤናማ ግንኙነት መሠረት ነው። ጥርጣሬና ለሌላው አለመቆርቆር ተደማምረው ውዝግብ ከማቅለል ይልቅ ፍርደ ገምድልነትን ያመጣሉ። አንድ ሰው እኛ የማይገባንን ነገር ካደረገ ቆይ እስቲ እኛ የማናውቀውና እሱ የሚያውቀው ነገር ሊኖር ይችላል ብለን እራሳችንን አንጠይቅም ወይንም ከፍርድ በፊት ትእግሥት አናደርግም። የነገሮችን የመሆንና ያለመሆን ሁኔታ ሳንዳስስ ለመዳኘት እንቸኩላላን። ይህ ወደተዛባ ፍርድና ግለሰባዊ ቅራኔ ውስጥ ይከተናል።

7. ስም ማጥፋትና አሉባልታ

ቅራኔዎችን ከመፍታት ይልቅ የማይግባቡን ሰዎች ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ እናደርጋለን። እንዲህ አይነቱ ዘመቻ በማኅበርሰባችን ውስጥ እንደሚሰራ እናውቃልን። አምታችና አሻሚ የሆኑ ነገሮችን በስነሥርዓት ሳንዳስስ ስለግለቦች የሚባለውን መጥፎ ነገር ማመን እንመርጣለን። የግለሰቦችን ክብር የሚነካ ነገር በማድረግ ግለሰቦችን ከጨወታው ውጭ እንዲሆኑ እናደርጋለን። ቀደም ብሎ እንዲህ አይነት ግንዛቤ ያለው ጭንቅላት ጥርጣሬውን የስም ማጥፋቱ ተግባር ግልፅ ያደርግለታል። እንዲህ አይነቱ አሉባልታ ብዙዎቻችን እንደምናውቀው ወደግለሰቦች ሽኩቻ፣ የቡድኖች ሽባነትና የድርጅት ውድቀት ያመራል።

8. ግልፅ አለመሆን

ግልፅነት ጤናማ ግንኙነት እንዲካሄድ ይረዳል። እኛ አስተሳሰባችንን ግልፅ ካለማድረጋችን ባሻገር የሌላውም አስተሳሰብ ግልፅ ይሆናል ብለን አንጠብቅም። ይህም በግልፅ ከተናገርኩ ምንነቴ ይታወቃል፣ እዳኛለሁ የሚለውን ፍራቻ ያመጣል። በዚህ ምክንያት ነገሮችን አድበስብሰንና በግድየለሽነት የግንኙነት ክፍተት ፈጥረን የድርጅት ውድቀትን እናመጣለን ምክንያቱም ሌሎች የተደበቀ ነገር አለ ብለው ስለሚገምቱ።

9. ቂም መያዝና መቀየም

ቂመኛነት ከባህላችን የመነጨ ስለሆነ ቂም እንይዝና ይቅር ማለትን እንደድክመት እናየዋለን ምክንያቱም ሁሉም እንደአደገኛ ስው ስለሚታይ ነው። በቡድን ስራዎች ውስጥ ሁሌም አለመግባባት ሊኖር ስለሚችል ቂም የምንይዝ ከሆነ ምንም አይነት ውጤታማ ሥራ መሥራት አይቻልም።

10 ምቀኝነት

በብዙ መንገድ ሰዎች ከኛ ተሽለው ሲገኙ እንደነሱ ተሽሎ ለመገኘት ከመጣር ይልቅ እነሱ እንደኛ እንዲሆኑ ወደታች እንጎትታቸዋለን። ይህ የሚሆነው፣ ሲደመር ዜሮ እንደሚሆን የሂሳብ ስሌት እንዱ ሀብታም የሚሆነው ሌላው ደሀ ስለሆነ፣ አንዱ ደስተኛ የሆነው ሌለውን ስላሳዘነ ነው ከሚል ግንዛቤ ሊሆን ይችላል። ይህ ዓለም የተወሰነ ሀብት፣ ደስታና የመሳሰሉት ነገር እንዳለው አድርገን እናይና ሁላችንም ድርሻችንን እንጠይቃለን። በመሆኑም ሰዎች የከበሩት የሆነ ወንጀል ሠርተው ሲሆን ያጡት ደግሞ ተረግመው ነው ብለን እናስባለን።

11. ግትርነት

መቻቻልን የምናየው እንደድክመት ነው። የመቻቻልና የመደራደር ፅንሰ ሃሳብ ለወደፊቱ ውጤታማ ጥረቶች የመሠረት ድንጋይ መሆኑን አንረዳም። እንዲያውም መቻቻልን የምናየው እንደተሸናፊነት ነው።

12. አጉል ይሉኝታ

ይህ ሌላውን ሰው ላለማስቀየም የሚወሰድ ባህለዊ እርምጃ ነው። የግለሰቦችን ወይንም የቡድኖችን ሕልውና ላለመንካት ሲባል ከእውነት የራቀ ሃሳብ ወይንም ድርጊትን ሳናስተካክል ወይንም ሳናርም ስለምናልፍ ሁሉም እርስ በርሱ እንዳይተማመን ይሆናል። ለእውነት መቆም የተፈጠሩትን ብቻ ሳይሆን ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን ሁሉ ሊያቃልል ይችላል።

13. አስመሳይነት

ራስን አለመሆንና እንደሳንቲም ሁለት ገፀታ ይዞ መጓዝ በቡድን አባሎችና ደርጅቶች ውስጥ ከፍተኛ አደጋ ያመጣል። የማናውቀውን እናውቃለን፣ የሌለንን አለን ካልን ሥራችን ልብወለድ እንጂ ተጨባጭ ነገሮችን ሊያንፀባርቅ የሚችል አይ ሆንም። በመሆኑም እንዲህ አይነቱ ጠባይ መጋለጥና መቆም ይኖርበታል።

በመጨረሻም እነዚህ ከላይ የተገለፁት ፀባዮች በኛ በኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን በሌላው የሰው ዘር ውስጥ በመጠኑ የሚገኙ የስነ ልቦና ባህርያት ናቸው። ነገር ግን እነዚህ ፀባዮች አሁን እኛ ካለንበት ድህነትና የማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ለመውጣት በምናደርገው ትግል ላይ ያላቸው ጎጂ ሚና ታውቆ አስፈላጊውን እርማት ማድረግ ይኖርብናል። የተሻለ ሥርአት ለማምጣት የአስተሳሰብ ለውጥ ማድረግ እንደሚያስፈለግ ማወቅ አለብን።

Tuesday, 18 September 2018

ኦኤምኤንን ከመክሰስ ሌላ ሚዲያ አቋቁመን እንብለጠው

በርካታ ጽሁፎቼ ስ«ለሃላፊነት» መውሰድ ነው። የሰው ልጅ ችግሮች ሲያጋጥሙን ሌሎችን ከመውቀስ እኛ ምን ብናደርግ ነው፤ ምን ብንሳሳት ነው፤ ምን ቀድሞ ዝግጅት ባናደርግ ነው ብለን እራሳችንን መጠየቅ አለብን። በዚህ አካሄድ ብቻ ነው ችግሮቻችንን መፍታት የምንችለው።

ሌሎችን መውቀሱ ዋጋ የለውም። ለምን ብትሉ ችግርን የሚፈጥሩ ሰዎች አውቀው የሚያደርጉት ከሆነ የኛ እነሱን መውቀስ በሃሪና ተግባራቸውን አይቀየርም። ይቀየራሉ ብለን ስንጠብቅ ችግሮቻችንን እያባባሱ ይቀጥላሉ! እኛ እየተጠቃን እንቀጥላለን። በራሳችን ያለን መተማመን እየቀነሰ ይሄዳል። የሰለባ አስተሳሰብ (victim mentality) እና የዝቅተኝነት መንፈስ (inferiority complex) እያደረግን እየጠነከረብን እንሄዳለን። አሉንታዊ እና ብሶታዊ ሰዎች እንሆናለን።

ግን ችግር ሲያጋጥመን ሃላፊነት ወስደን ምን ብናደርግ ባናደርግ ነው ይህ ችግር ያጋጠመን ካልን እራሳችንን የችግሩ መፍትሄ እናደርጋለን። እራሳችንን እናጎለብታለን (empower)። ችግሩን ሰፋ አድርገን እናያለን። ኃይል እንዳለን ይገባናል እና በራሳችን እንድንተማመን (confidence) ያደርገናል። አዎንታዊ እርምጃዎች ወስደን ከችግራችን እራሳችንን እናወጣለን። ደግሞ ችግር እንዳይገጥመን ደግሞ እራሳችንን እናጠነክራለን። ለደህንነታችን ሌሎችን መለመን እንደማያስፈልገን ይገባናል ስለዚህም በማንነታችን በተገቢው እንኮራለን።

በቅርቡ በቡራዩ እና ዙርያ በተከሰተው የጎሳ ማጥፋት (ethnic cleansing) ክስተት በርካቶች ኦኤምኤን ተለቪዥን ጣብያን እንደ አንድ ጥፋተኛ ከሰዋል። ኦኤሜን ላይ የሚቀርቡ ተንታኞች የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ ስለሚያደርጉ ነው አንዱ ምክንያት እንደዚህ አይነት ክስተት የሚከሰተው ይባላል። ኦኤምኤን ነው ችግራችን እና ይዘጋ ወይንም እስከሚስተካከል ይታገድ ይባላል።

ጥሩ ነው። አጥፊ አጥፊ ነው ተብሎ መንግስትን ህግን አስከብሩ ማለትም የዘር ማጥፋት ቅስቀሳን አቁሙ ማለት ተገቢ ነው። ግን በዚ ላይ ብቻ ማተኮር እራስን አቅመ-ቢስ ማድረግ ነአ ማዋረድ ነው። አንዴ መንግስት ተነግሯል፤ መንግስት ያውቃል፤ ይበቃል። ኦኤምኤንን ደጋግሞ መክሰስ ኦኤምኤንን ማጎልበት ነው። በኛ ላይ ብዙ ኃይል አለህ እና ጫና መፍጠር ትችላለህ ማለት ነው። እኛ የአንተ ሰለቦች ነን ብሎ ማለት ነው። ይህ አካሄድ ኦኤምኤንን ያጎለብታል እኛን ደግሞ አቅመ-ቢስ ያደርጋል። የሰለባ እና የዝቅተኝነት ስሜት እንዲአድርብን ያደርጋል። በዋናነቱ ደግሞ ችግሩ እንዲቀጥል እንዲባባስ ያደርጋል።

መሆን ያለበት አንዴ መልዕክታችንን ለመንግስት ካስተላለፍን በኋላ እና ለህዝቡ የኦኤምኤንን ጥፋት ካገለጽን በኋላ ወደ ራሳችን ስራ መግባት ነው። 10% ጊዜአችን ስለ ኦኤምኤን እውነቱን መናገር ካጠፋን 90% ጊዜአችንን እራሳችን በራሳችን መፍትሄ በማግኝነት ነው ማድረግ ያለብን።

በዚህ በሚዲያ የዘር ማጥፋት ጉዳይ ምንድነው እኛ ማድረግ የምንችለው? ብዙ ነገሮች አሉ ግን አንዱ ቀላሉ ጠንካራ የኦሮምኛ ሚዲያ ማቋቋም ነው። ይህን ነው ኢሳት ረዥም ዓመታት በፊት የመከረው ግን ይህ ሙከራ አቅሙ እጅግ ደካማ ነው። ስለዚህ ያልንን አቅም (resources) ሰብስበን ኦኤምኤንን የሚበልጥ ሚዲያ በማቋቋም መስራት አለብን። ይህን ካደረግን እና ከተሳካ ግማሹ ችግር ይጠፋል። ስለ ኦኤምኤን ማልቀስ ይቀራል። ይህ አካሄድ አሉታዊ ከመሆን አዉንታዊ ያደርገናል።

ሁሉ ጉዳዮቻችንን በዚህ መልኩ ብናያቸው ጥሩ ይመስለኛል። ጣት ከመጠቆም እራስን ማየት እና እራስን አጎልብቶ መፍትሄ በራስ ባግኘት። እንዲህ አይነት አስተሳሰብ ቢኖረን ኖሮ ስንት ያለፍንባቸው ችግሮች አይኖሩም ነበር። በጥቂት ድጋፍ ያለው ህወሓትም አንገዛም ነበር! ስለዚህ የአስተሳሰብ ለውጥ ላይ እናተኩር፤ ከህጻንነት ወደ ሃላፊነት የምንወስድ አዋቂዎች እንቀየር።

Monday, 17 September 2018

ችግሩም የኛ ነው መፍትሄውም የኛ

በምን «ሞራል» ነው ቅንጅት ያፈራረስነው አሁን ሀገራችን የደረሰበትን ሰቆቃ በኦሮሞ ብሄርተኞች፤ ህወሓት፤ ወዘተ የምናሳብበው? መብም «ሞራል» ነው ኢዲኡን ያፈረስነው ችግሮቻችንን በነዚህ የምናሳብበው? በምን ሞራል ነው ላለፉት 27 ዓመታት ይህ ማለት የሚቻል ድርጅት ማቋቋም ያልቻልነው የአንድ አናሳ አምባገነናዊ መንግስት ማውረድ ያልቻልነው ችግራችንን በሌሎች የምናሳብበው? እስከ ዛሬ እርስ በርስ እየተጣላን፤ እከሌ አላከበረኝም፤ እከለ ሰላም አላለኝም፤ እከሌ የሌላ ቡድን ነው ወዘተ እያልን ለጥፋታችን ሃላፊነት ከመውሰድ «ኦኤምኤን» እንደዚህ አደረገን ጃዋር እንደዚህ አደረገን ስብሃት ደጋ እንደዚህ አደረገን የምንለው? ጥፋቱ የኛ ነው መፍትሄውም ከኛ ብቻ ነው መምጣት የሚችለው። የዘራነውን እያጭድን ነው። የክፍፍላችን ውጤት ይህ ነው። 

ካሁን ወድያ እራሱን «ኢትዮጵያዊ ነኝ» በ«ኢትዮጵያዊነት አምናለው» የሚል ሰው ችግራችን ሌሎች ላይ ከለጠፈ ኢትዮጵያዊ አይደለም። ለራሱ ችግር ሃላፊነት መውሰድ የማይፈልግ ገጓደኞቹ ጋር በሰላም ተባብሮ ተማምኖ አብሮ ከመስራት በጠላቶቹ መገዛት የሚመርጥ ነው! 

ይቅርታ ካሁን ወድያ መወሰን አለብን። የሰፈር ህፃናት ነን «እሱ ነው፤ እሱ ነው» ብለን የምናሳብብ ወይን አዋቂዎች ነን ችግራችንን አይተን ሃላፊነት ወስደን የምናስተካክል። ሃላፊነት ወስደን። ሃላፊነት ወስደንጅን!!

ጃዋር አያረገውም። እነ ስብሃት ነጋ አያረጉትም። እነሱ ላይ መቾህ እና መለመን የህፃን በሃሪ ነው ፋይዳ የለውም። ይህ ግልጽ ነው እንዴት አይገባንም። ምናልባት በህፍረት አንገታችን ድረስ ተሞልተን ከህፍረታችን መሸሽ ወድደን ይሆን? እስከ ዛሬ ምንም ስላላደረግን አፍረን እውነታን እየሸሸን ይሆን? አላውቅም? አይገባኝም።

እንዴ፤ ጣልያን ሲወርረን የኛ ህዝብ እና መሪ ጣልያንን አትወሩን ብለው ሲለምኑ አልሰማንም! ተደራጅተው ተዋጉ። አላለቀሱም። ጣልያኖችን አለመኑም። እርስ በርስ ተባብረው አብረው የሚችሉትን ሰሩ።

አሁን ግን ላለፉት 50 ዓመት እርስ በርስ መቃረን፤ መተቸት፤ እንደ ተራ ሰፈር ወረኞች «ጸጉር መጎተት» ነው ስራችን። መከፋፈልን «ስፖርት» አድርገነዋል። እንጂ በምን ሂሳብ ነው 8% እወክላለሁ የሚል ህወሓት ሀገራችንን ለ27 ዓመት የገዛው?! 

አሁንም ይህን ነው በሽታችን። ይህን ከመስተካከል በቀር ምንም ምንም አማራጭ የለም። የራሳችንን ችግር ማየት ማመን ማስተካከል ከባድ እና ቁስል የሚነካ ስራ ነው የሚሆነው ግን ግድ ነው። ማንም የሚንበረከከልን የለም።

ችግሩም የኛ ነው መፍትሄውም የኛ። 


Friday, 14 September 2018

ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ…

…ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?

ሌላ ሰውን በኛን ሃሳብ ለማሳመን ስንሞክር ከአንደበታችን ይልቅ ስራችን ማለትም ምሳሌአችን ነው ዋና ሚና የሚጫወተው። ምንም ጥሩ ሃሳቦች ቢኖሩን፤ ምንም ጥሩ አቀራረብ ቢኖረንም፤ ሃሳባችንን በተግባር የምናውል ጥሩ ምሳሌ ካልሆንን ማንም አይሰማንም፤ አያምነንም፤ አይከተለንም።

በ«ኢትዮጵያዊነት» ወይንም በ«ኢትዮጵያ ብሄርተኝነት» የምናምነው ይህን ነጥብ ጠንቅቀን ብናሰብበት ጥሩ ይመስለኝም። የኛም የኢትዮጵያም ህልውናን ይመለከታልና። የኢትዮጵያ ብሄርተኞች ፖለቲካ ታሪካችን የእርስ በርስ (አለ ጥሩ ምክንያት) መቃረን እና መጋጨት ነው (http://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/07/blog-post_31.html)። በኃይለ ሥላሴ ዘመን ሹማምንቶቹ እየተጣሉ ለፍርድ እና ለዳኝነት  ጃንሆይ ደጅ ረዥም ሰልፍ ይሰለፉ ነበር። ዛሬም የፖለቲካ ድርጅቶቻችን ከሚገባው ማለትም ብዙሃን ደጋፊዎቻቸው ቁጥር አንጻር እጅግ ደካማ ናቸው የመሰባሰብ፤ መወያየት፤ መስማማት እና መተባበር አቅማችን ደካማ ስለሆነ። ይህ የሚያሳየው የኛ የኢትዮጵያ ብሄርተኞች የረዥም ዓመታት የንትርክ፤ የመጣላት፤ የአለመተማመን ወዘተ ታሪክን ነው።

ይህን ታሪክ ሁሉም አይቶታል እና ያውቀዋል። በተለይም የጎሳ ብሄርተኞች (ጸንፈኛም ለዘብተኛም) የሚባሉት ከኛ «ተቃራኒ» የፖለቲካ አቋም ያላቸው ይህንን የኛ ደካማ የፖለቲካ ጠባይ አይተውታክ። ንቀውናልም ማለት ይቻላል። በአንጻሩ እኛ እነሱን «ዘረኛ አትሆኑ»፤ «በግለሰብ እኩልነት እና መብት እመኑ፤ «ከኛ ሰላማዊ እና ፍትሃዊ አቋም ተማሩ» ወዘተ እንላቸዋለን። ግን በጎሳ አስተዳደር የሚያምኑት እኛን የኢትዮጵያ ብሄርተኞች ሲያዩ እርስ በርስ ስንጣላ እና ስንለያይ ነው የሚያዩት። ከኛ ጥሩ ምሳሌ አያዩም። ታድያ እንዴት እኛ የምንለውን ሊያምኑ እና ሊከተሉ ይችላሉ። ይከብዳቸዋል።

ግን እኛ ጥሩ ምሳሌ ብንሆን፤ የፖለቲካ ጎራችን ንፁ ቢሆን፤ እርስ በርስ ያለን ግንኙነት በፍቅር እና በሰላም የተሞላ ቢሆን የጎሳ ብሄርተኞችም ሌሎችም ወደኛ አቋም ይበልጥ ይሳቡ ነበር። «የነሱ አስተሳሰብ ይህንን ሰላም እና ስልጣኔ የሚያመጣ ከሆነ እኛም ወደነሱ እንጠጋ እና ከዚህ ብልጽግና እንካፈል» ይሉ ነበር። «እውነትም ፖለቲካ አቋማቸው ልክ መሆን አለበት» ይሉ ነበር።

ስለዚህ አሁን ባለው እና በሚመጣው የፖለቲካ ግንባታ እና ውድድር በደንብ ከመግባታችን በፊት እኛ የኢትዮጵያ ብሄርተኞች መጀመርያ እራሳችንን መፈተሽ አለብን። ቀጥሎ የነ ጠ/ሚ አብይን ምሳሌ ተከትለን ንስሃ ገብተን ይቅርታ መጠየቅ ያለብን ይመስለኛል በህዝቡ ዘንድ እምኔታ ለማግኘት እና ህሊናችንን ለማርካት። እኛ ፍፁም ነን ችግሩ ከኢህአዴግ፤ ህወሓት፤ ደርግ ወዘተ ነበር ማለቱ ልክ አይደለምም አዋጪም አይደለም። እውነታ የሆነውን የኛ ታሪካዊ ጥፋቶችን ልክ እንደ ጠ/ሚ አብይ አምነን፤ ተቀብለን መናገር አለብን። ከዚህ በኋላ ነው የፖለቲካ እንቅስቃሴአችን ውጤታማ መሆን የሚችለው።



Tuesday, 14 August 2018

ተረት ተረት፤ «ጎሰኝነት ዘረኝነት ነው»

ይህም ከፊል እውነታ አለው። አማራ ማየት አማርኛ መስማት የሚጠሉ ጸንፈኛ ኦሮሞ ብሄርተኞች አሉ። ግን ጎሰኝነትን «ዘረኝነት» ብሎ መሰየሙ ችግሩን በትክክል አይገልጸውም ወደ መፍትሄም ለመምጣት አይረዳም። ላስረዳ…

«ዘረኝነት» የሚለው ቃል ብዙ ትርጉም ያለው፤ የተወሳሰበ፤ ኃይል ያለው ቃል ነው። የምንጠቀምበት አንድ ነገርን ወይንም ሰውን ክፉ መጥፎ ነው ብለን ለመሰየም ነው። ከክፉ ጋር ውይይት የለም ድርድር የለም። «ዘረኝነት» ብለን ሰይመን ከዚህ ሀሳብ ጋር ውይይትም ድርድርም አያስፈልግም ነው የምንለው «ዘረኛ» ስንለው። ትክክለኛ አካሄድ አይደለም።

ጎሰኝነትን እስቲ እንደዚህ ብናየው ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖረን ይረዳል ጎሰኝነትን ለመቀነስ ለማጥፋትም ምን ማድረግ እንዳለብን እንድንረዳ ይረዳናል። ጎሰኝነት ገና ሲጀመር በውይይት፤ በማስረዳት እና በማስተማር ማጥፋት ይቻላል። ግን ጎሰኝነት አንድ ደረጃ ካለፈ ውይይት ከሞላ ጎደል አይሰራም።

ለምሳሌ ጎሰኛው ኦሮሞነቱ እጅግ አይሎ ኢትዮጵያዊነቱ እጅግ ከመነመነ ስለ ታሪክ እና ፖለቲካ ምን ብትሰብከው ለውጥ ሃሳቡን አይቀይርም። «ዘረኛ» ብትለውም ፋይዳ የለውም። ይህ ስወ ዘረኛ ሳይሆን ማንነቴ ሙሉ በሙሉ «ኦሮሞ» ነው ብሎ ወስኗል። ሀገሬ ኦሮሞ ነው ኢትዮጵያ አይደለም ነው የሚለው። ኢትዮጵያን ይጠላ አይጠላ አይደለም ዋናው ጉዳይ። ኦሮሞ ነኝ ማለቱ ነው። ልክ እንደ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የተለያዩ ሀገሮች እንደሆኑ ሱዳናዊው በኢትዮጵያ ያለው መብት ውስን እንደሆነ እንዲሁም በተገላቢጦሽ ለኦሮሞ ብሄርተኛው በኦሮሚያ እና ኢትዮጵያ ያለው ልዩነት እንዲሁ ነው። ሌላ ሀገር ንኝ ነው የሚለው። ይህን የማንነት ስሜቱን ደግሞ ልንከለክለው አንችልም። «ዘረኛ» ማለቱ ዋጋ የለውም ምናልባትም ማባባስ ነው።

ታድያ ጎሰኝነት ይህ ከሆነ ምን ችግር አለው ትሉ ይሆናል? የሀገሩ ማንነት መምረጥ የሰው ልጅ «መብት» ከሆነ ምን ክፋት አለው? «ዘረኝነት» ካላልነው መጥፎነቱን እንዴት እንግለጽ? መልሱ ቀላል ነው፤ ጎሰንኘት «መብት» ቢሆንም የታላቅ ግጭት ምንጭ ነው። በአንድ ሀገር ጎሰኝነት በተለይም ጎሰኝነት እና ብሶት (grievance) አብረው ሲኖሩ ከፉ ግጭቶች ይኖራሉ። ይህ በቴኦሪ ወይንም በሌሎች ሀገራት ብቻ የሚታይ ሳይሆን ለ27 ዓመት በኢትዮጵያ የታየ ነው። ለግጭቶች ደግሞ በመንግስት አምባገንነት አናሳብብ፤ መንግስት ያልተሳተፈበት ግጭቶች ብዙ ነበሩ አሁንም አሉ። አልፎ ተርፎ መንግስት በግጭቶቹ ቢሳተፍባቸውም ባለ ክፍተት ነው እየገባ እየበጠበጠ የነበረው እንጂ የሌላ ልዩነት የመፍጠር አቅም አልነበረውም።

ስለዚህ ጎሰኝነት ወይንም የጎሳ እና ሀገር ሚዛን ከልክ በላይ ወደ ጎሳ ሲያመዝን ችግሩ ጎሰኝነት «ዝረኝነት» መሆኑ ሳይሆን የግጭት ምንጭ መሆኑ ነው። መፍትሄውም የግጭት ምንጭ ነው ብለን ጎሳን እንደ ጽንሰ ሀሳብ ከሀገሪቷ ህገ መንግስት ማውጣት እና በ«ቋንቋ እና ባህል» ጽንሰ ሀሳቦች መተካት ነው።

ተረት ተረት፤ የትግራይ ገዥ መደብ አገዛዝ እና የ«አማራ ገዥ መደብ» አገዛዝ አንድ ናቸው

«የትግራይ ገዥ መደብ አገዛዝ እና የ«አማራ ገዥ መደብ» አገዛዝ አንድ ናቸው»። ይህ ተረት ተረት (myth) በበርካታ ሰዎች ሲደጋገም ወደ እውነታ እያማራ ነው። በቅርቡ ባደረጉት ኑዛዜአቸው የቀድሞ ጠ/ሚ ታምራት ላይኔም ደግመውታል። «የአማራ ገዥ መደብ ብይ አማራ ብዙሃን እንደነገዱት ነው ህወሓት የትግራይ ገዥ መደብ በትግራይ ብዙሃን የነገዱት» ብለዋል። ይህ አስተያየት እጅግ የተሳሳተ ነው።

የሁለቱ አገዛዞች መሰረታዊ ልዩነት ይህ ነው፤ በደርግ እና በንጉሳዊው ስርዓት ጎሳ፤ ዘውግ፤ ብሄር አይነት ጽንሰ ሀሳቦች በህግ ደረጃ አልነበሩም። አገዛዙ በህግ ደረጃ ከጎሳ እና ከጎሰኝነት ውጭ ነበር። በህወሓት አገዛዝ ግን ጎሳ እና ጎሰኝነት በህግ የተደነገገ ነው። ጎሰኝነቱ በልምድ ወይንም በባህል ደረጃ ሳይሆን ህጋዊ ነው። ይህ መሰረታዊ ልዩነት ነው።

በኃይለ ሥላሴ መንግስት ማንኛውም ግለሰብ በጎሳ ምክንያት ከመንግስታዊ ስልጣን እና ሹመት አይከለከልም ነበር። አይከለከልም ብቻ ሳይሆን ጎሳው ጭራሽ እንደ ጉዳይ አይነሳም፤ በህግ እና ስረዓት ደረጃ ጎሳ የሚባል ጸንሰ ሀሳብ የለም። በዚህም ምክንያት በኃይለ ሥላሴ መንግስት በርካታ ከተለያዩ ጎሳ የሆኑ ባለ ስልጣኖች ነበሩ።

ሆኖም የአስተዳደር ቋንቋው አማርኛ ነበር። ይህ ከጅማ ለተወለደው ኦሮሞ መሰናከል ነበር። የገዥ ስረዓቱ ንጉሳዊ ነበር። ይህ ከኮንሶ የተወለዱት ባዕዳዊ ስረዓት ነበር። በነዚህ አይነት ምክንያቶች አማራ ያልሆኑ ወደ ስልጣን ለመቅረብ ከአማራ ይልቅ ይከብዳቸው ነበር ማለት ይቻል ይሆናል። አማራ ቋንቋውን በማወቅ ከሌላው ይበልጥ እድል ነበረው ማለት ይቻላል። እንዲሁም የአዲስ አበባ ተወላጅ ይበልጥ እድል ነበረው ማለት ይቻላል። በዚህ ደረጃ በተለያዩ የጎሳ ተወላጆች የስልጣን እና ሹመት እድል ልዩነት መኖሩን መካድ አይቻልም። ግን ይህ ልዩነት የታሪክ አጋጣሚ ነው እንጂ በህግ የተደነገገ አልነበረም። ስለዚህ አማራ ያልሆነው ቢከብደውም ወደ ስልጣን መምጣት ይችል ነበር። አድሎ ነበር ግን አድሎው ህጋዊ አልነበረም ስለዚህ ሊቀለበስ የሚችል አድሎ ነበር።

የህወሓት አገዛዝ ግን መሰረቱ ጎሰኝነት ነበር። ህወሓት የትግራይ ድርጅት ለትግራይ ህዝብ ነው። አማራው በአማራነቱ ቦታ የለውም። ቋንቋ ባለመቻሉ ወይንም የፖለቲካ ባህሉን ባለማወቁ ሳይሆን በአማራነቱ ምክንያት ስልጣን ሊይዝ አይችልም። በህወሓት ዘመን አድሎ መቀልበስ የማይችል የጎሳ የደም አድሎ ነበር።

ይህን የ«ትግራይ ገዥ መደብ» እና የ«አማራ ገዥ መደብ» አገዛዝ ልዩነት ስንመለከት አንድ ትልቅ ትምሕርት እንማራለን። ይህ ስለ የጎሳ አገዛዝ አደገኝነት ነው። ጎሳ የትውልድ የደም ጉዳይ ስለሆነ በመሰረቱ ህዝብን የሚለይ እና አድሎ (discrimination) የሚያመጣ ነው። በዚህ ምክንያት ነው የጎሳ አገዛዝ የግጭት (conflict) ፋብሪካ የሚሆነው።

የጎሳ መብቶችን ለማስተናገድ የጎሳ አስተዳደርን ከመጠቀም ወይንም የጎሳ መብቶች በህግ ከማወጅ የቋንቋ እና የባህል መብቶችን ማደንገድ ይሻላል። ቋንቋ እና ባህል ማንም መማር መቀየር የሚችለው ስለሆነ መሰረታዊ አድሎ የላቸውም። በዚህ ምክንያት በአድሎ የተነሳ የተጨቋኝ ስሜቶችን አያዳብርም ስለዚህ ግጭትን አያበዛም።

ይህን ተመስርተን ነው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ጸንፈኛ ነው የምንለው። ዓለም ዙርያ ሀገራት የቋንቋ እና ባህል መብቶችን በህጋቸው ያስተናግዳሉ። የጎሳ መብቶችን በዚህ መንገድ ያስተናግዳሉ። ግን የትም ሀገር ጎሳን በህጋቸው አያስተናግዱም። በጎሳ እና በቋንቋና ባህል ያለውን ልዩነት በግጭት መጋበዝ አኳያ በድምብ የታወቀ ስለሆነ ነው እንዲህ የሆነው። ግን ኢትዮጵያ ብቸኛዋ ጎሳን በህግዋ ውስጥ ያካተተች ናት። ለሀገራችን ህልውና ይህን መቀየሩ አስፈላጊ ነው።

Wednesday, 21 March 2018

«ሴኩላሪዝም»

ትንሽ አመታት በፊት አንድ የመንግስት ስራተኛ የሆነ ዘመዴ የኦርቶዶክስ መዝሙር ከመስሪያቤት ኮምፕዩተሩ ላይ ማዳመጥ ክልክል እንደተደረገ ነገረኝ። ለምን ብዬ ስጠይቀው ክርስትያኑም ሙስሊሙም የሚፈልገውን መዝሙር፤ ስብከት፤ ትምሕርት እያዳመጠ እና ኮምፕዩተሩ ላይ ሥዕል እየለጠፈ የሰራተኞች እርስ በርስ ግጭት ሊፈጥር ይችላል ተብሎ ተከለከለ አለኝ። የሚገርመው ነገር ግን 1) ከመስሪያቤቱ እንደዚህ አይነት ግጭቶች አልነበሩም እና 2) ክልከላው በተራ ትዛዝ ሳይሆን ከከፍ ያለ የአስተዳደር ደረጃ በመመርያ ምልክ የተላለፈ ነበር። የመመርያው ርዕስ ደግሞ «ሴኩላሪዝም» ነበር።

ይህን ታሪክ ስሰማ እጅግ አዘንኩኝ። መቼ ነው መንግስቶቻችን፤ ምሁሮቻችን እና ልሂቆቻችን የምዕራብ ዓለም ርዕዮት ዓለምና ፍልስፍና ይዘው አገራችን ላይ መጫን የሚያቆሙት? ካለፉት የ100 ዓመታት ታሪካችን አይማሩምን?

እስቲ «ሴኩላሪዝም» ባጭሩ ምን እንደሆነ እንመልከት። «ሴኩላሪዝም በዓለማችን እግዚአብሔር የለም/አይሳተፍም ብሎ ማሰብ ነው»። ሴኩላሪዝም እግዚህብሔር ሊኖር ላይኖርም ይችላል ግን ከዓለማችን ከሕይወታችን ከለት ኑሮአችንም አይሳተፍም የሚለው አመለካከት ነው። እግዚአብሔር ካለ እዛው ከዙፋኑ ወይንም ገነቱ ተቀምጦ ይመለከተናል። በሃይማኖት እና በእግዚአብሔር በግል ምርጫችን ልናምንባቸው የምንችል የእምነት ሥርዓቶች ናቸው። በሀሳብ ደረጃ ነው የምናምንባቸው ካላሰኘን ደግሞ ከሀሳባችን እናስወግዳቸዋለን!

ይህ አስተሳሰብ በተለያየ መንገድ ወደ ክርስትያን የሆነውን አስተሳሰብ ገብቷል። «ዓለማዊ» እና «መንፋሳዊ» የምንላቸው ቃላት በተሳሳተ መንገድ እንጠቀማለን። ዓለማዊ ስንል ስራችን፤ ትምሕርታችን፤ ገበያችን፤ ንግዳችን ወዘተ ነው። እግዚአብሔር እነዚ ነገሮች ውስጥ እንዳለ አናምንም። ስለዚህም ነው በነዚህ የህይወት ዘርፎቻችን ኢ-ክርስትያናዊ ነገሮች እያደረግን እያለን አማኞች ነን የምንለው። እሁድ እሁድ ግን ቤተ ክርስትያን ሄደን ወደ መንፈሳዊስ ዓለም እንሸጋገራለን። እዛ ጨዋ ነን፤ ጥሩ ስነ መግባር አለን፤ ጭንቀቶቻችንን አስተንፍሰን ወደ ዓለማችን እንመለሳለን።

ይህ ግን የውሸት ክርስትና ነው። በእምነታችን እግዚአብሔር በሁሉም ቦታ በሁሉም ነገር አለ። «እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም። ሰው በስውር ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር።» ኤር 23:23-24።

ስለዚህ ትምሕርት ቤት ብሄድ፤ መስሪያ ቦታ ብሄድ፤ እርሻዬ ላይ ብሆን፤ ትራንስፖርት ላይ ብሆን፤ መጠጥ ቤት ብሄድ፤ በሁሉም ቦታ እግዚአብሔር አለ። ሕይወታችንን እግዚአብሔር ያለበትና የሌለበት ብለን ልንከፋፍለው አንችልም። በሁሉም ቦታ በሁሉ ደቂቃ ከኛ ጋር ነውና።

ይህ የሚያሳየን የሰው ልጅ ክርስትያንም ሴኩላሪስትም አብሮ ሊሆን አይችልም። ብዙዎቻችን ወደዚህ ስህተት ብንገባም ሊሆን የማይችል ነገር ነው። ለክርስትያኖች እግዚአብሔር ልኬት የለውምና። በተጨማሪ ሴኩላሪዝም እግዚአብሔርን ከለት ኑሮአችን ማጥፋት ስለሚፈልግ የክርስትና ተቃራኒ ብቻ ሳይሆን ጠላት እንደሆነ ግልጽ ነው።

«እናንተ ኦርቶዶክሶች፤ ሙስሊሞች፤ ፕሮቴስታንቶች አብሮ መኖር አትችሉም። ስለዚህም (እግዚአብሔራን ተክቼ!) ከላያችሁ ሆኜ አስተዳድራችኋለሁ» ይላል ሴኩላሪዝም / ሴኩላሪስቱ። «እኔ ነኝ ስልጡኑ፤ ከማንም ጋር የማልጋጨው፤ ከሁሉም ጋር የምግባባው፤ ሁሉንም የማከብረው» ይላል። እውነቱ ግን ሴኩላሪስቱ እንደዚህ ሲል ሁሉንም በሰላም ለመጠበቅ ሳይሆን አላማው ይህን አስመስሎ «እግዚአብሔር የለም» የሚባለውን ሃይማኖትን ለማስፋፋት ነው። እግዚአብሔር ከአዕምሮአችን ብቻ ነው ያለው እንጂ ከስራ ቦታችን፤ ገበያ ቦታችን፤ መንገዶቻችን፤ ሚዲያዎቻችን፤ ከለት ኑሮአችን የለም ብለን ካመንን ቀጥሎ እግዚአብሔር የትም የለም ማለት የሚቀጥለው ቀላል እርምጃ ነውና!

በተጨማሪ እግዚአብሔር ከለት ኑሮአችን ከሌለ የማህበረሰብ የአገራችን ድንጋጌዎች ከየት ሊመጡ ነው? ከሴኩላሪዝም ርዕዮት ዓለም ከ«እግዚአብሔር የለም» ሃይማኖት ሊመጡ ነው! አያችሁ ሴኩላሪዝም እራሱን ገለልተኛ አድርጎ እንዴት «እግዚአብሔር የለም» ሃይማኖትን ሰተት ብሎ እንደሚያሰፍን።

ኢትዮጵያ የሃይማኖት አገር ናት። ታሪካችን ትውፊታችን ከዚህ የተያያዘ ነው። ማንነታችን ይህ ነው። ሴኩላሪዝም ደግሞ የህን አፍርሶ «እግዚአብሔር የለም» ሃይማኖትን ነው ማስፈን የሚፈልገው። ይህ ሂደት እንዴት እንደሚሰራ ለማወቅ የምዕራብ ዓለሙን ያለፈውን 400 መቶ ዓመት ታሪክ መመልከት ነው። ስለዚህ ሴኩላሪዝም ኢ-ኢትይጵያዊ እንደሆነ ተረድተን ወደ አገራችን ሰተት ብሎ እንዳይገባ መጠንቀቅ አለብን። በተለይ ደግሞ ወደ ልባችን ሰተት ብሎ እንዳይገባ መጠንቀቅ አለብን።