Tuesday, 13 November 2018

ወግ እና ማንነት ሲናቅ ግብረ ገብ ይጠፋል

በደርግ ዘመን የተደረገውን ማሰቃየት (torture) ይታወቃል። በወያኔም ዘመን እንዲሁ መቀጠሉን ሁላችንም እናውቃለን መንግስት አምኖ የፍትህ እርምጃዎች መውሰዱ ታላቅ እርምጃ ቢሆንም።

ለምንድነው ይህ የተከሰተው የሚለውን ጥያቄ በተለያየ መንገድ መመለስ ይቻላል። አንዱ መልስ የራስን ባህል፤ ወግ፤ እና ታሪክን ንቆ እና ትቶ የሌላ የበአድ መንገድ መከተል ነው።

ኃይለ ሥላሴ (የሚመጣውን ችግር በደምን ሳይረዱ?) ራሱን የሚጠላ ፈረንጅ አምላኪ ልሂቃን ትውልድ ከፈጠሩ በፊት ዛሬ የምንሰማው አንየንት የግብረ ገብ ጥሰት እና ማሰቃየት አልነበረም። ሰው ወህኒ ቤት ይታሰራል፤ ግዞት ይላካል፤ ማናልባትም ይገደላል። እነዚህ ነገሮች በአግባብም አለአግባብም ይደረጉ ነበር። ግን «ባህላዊ» ናቸው ማለት ይቻላል፤ ለመቶዎች/ሺዎች ዓመታት የሚደረጉ ነገሮች ነበሩ።

ዘመናዊው ትውልድ ግን የበአድ ባህሪዎችን አመጣብን። በፍፁም የማይታሰቡ አስተሳሰቦች አመጣ። በፍፁም የማይደረጉቶች አመጣ። እራሱን፤ ማንነቱን፤ ኢትዮጵያዊነቱን ሳተ። ወደ ኢ-ኢትዮጵያዊነት ሙሉ በሙሉ ገባ። ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ድርጊቶች ፈጸመ። ለዚህም ነው ዛሬም ቢሆን ኢትዮጵያዊያን ስለነዚህ ድርጊቶች ሲሰማ እጅግ እሚደነግጠው።

ይህን ስል በባህላችን ችግሮች የሉም ማለቴ እንዳልሆነ መቼም ሁላችሁም ትገነዘባላችሁ! ሆኖም ችግሮችን ቀርፎ ማውጣት እና ጥሩ ነገሮችን ይዞ መጓዝ ነው እንጂ ሁሉንም አራግፎ ወደ ሌላ መንገድ መሄድ አደጋ ነው። ይህን አደጋ በተለያየ መንገዶች አይተነዋል እያየነውም ነው።

ይህ የማሰቃየት ታሪካችን እንዳይደገም አንዱ መፍትሄ ወደ ወጋችን፤ ወደራሳችን መመለስ ነው።

No comments:

Post a Comment

ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!