ቭላዲሚር ፑቲን እንዳሉት የብሄር ማንነት ሊቀያየር ይችላል። ይህ በሰው ልጅ ታሪክ የተለመደ እና ተፈጥሮአዊ ነገር ነው። የማንም የብሄር ማንነት፤ አዲስ ወይንም ግልገል የብሄር ማንነትም ሊከበር ይገባዋል። ቭላዲሚር ቭላዲሚሮቪች ይንን ያሉት የዩክሬን የብሄር ማንነት በአንጻሩ አዲስ (ወደ 150 ዓመት) ቢሆንም መከበር አለበት፤ በግድ ሩሲያዊ ሁኑ ማለት የለባቸውም ነው።
የዩክሬን ብሔርተኝነት የተጀመረው በ19ኛው ክፍለዘመን ነው የዘመናዊ ብሔርተኝነት ርእዮት አለም አውሮፓን ማቀጣጠል ሲጀምር። በዚህ የቃጠሎ ዘመን ስለተወለደ ብሔርተኝነቱ በአደገኛ መንገድ (trajectory) ጉዞውን ጀመረ።
ማንኛውም ብሔርተኝነት እነዚህን ባህሪዎች አሉት 1) ጠላት (ጥላቻ) 2) ተረት (myth) 3) ሁሉ ገዥነት (ብሔሩ ከሁሉም ነገር ከሃይማኖቱም በላይ ነው ወይንም ጣኦት ነው)። ለምሳሌ ዘመናዊ (በጃንሆይ ዘመን የተወለደው) የኢትዮጵያ ብሔርተኝነት የጠላቱ መስፈርት በአደዋ ጣልያን ነበር የተሟላው። ተረታችን እስከ ህንድ አገር ገዝተን ነበር ይሚለው ነበር (የዛሬው ግዛት ተገቢ ነው ለማለት)። ሁሉ ገዥነትን በ«አገር የግል፤ ሃይማኖት የጋራ» የሚለው አባባል ተሟላ። ጣልያን የቅርብ ጎረቤት ስላልሆነ፤ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ሽኩቻ እየቀነሰ ስለነበር፤ ኢትዮጵያ እንደገና እስከ ህንድ ልግዛ ስለማትል ጂቡቲንም ስለማትፈልግ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ሃይማኖትን ስላልጨቆነ የኢትዮጵያ ብሔርተኝነት በርካታ ችግሮች ቢኖሩትም ጸንፍ የያዘ አልነበረም ብዙ ወደ ከፋ መንገድ አልሄድም ነበር። ግን ...
በአንጻሩ ግን አንዳንድ ብሔርተኝነቶች የብሔርተኝነት ባህሪዎቻቸውን በከፋና ጸንፍ የረገጠ መንገዶች ያሟላሉ። ዩክሬን አንዱ ምሳሌ ነው። በሃያላን ፖላንድና ሩስያ ስለተከበበች አዲሷ ዩክሬንን የሚያራምዱ ፖለቲከኞች የፖላንድና በተለይ የሩሲያን ጥላቻ የዩክሬን ብሔርተኝነት ምሶሶ አደረጉት። ዩክሬን ከሁሉም ጎረቤት ሃብታም ናት ህስቦቿም ስላቭ (slavs) ሳይሆኑ እንደ ናዚ ጀርማን ፍጹም አርያን (Aryan) ናቸው ተባለ። በመጨረሻ የሀገሪቷ ስፋት የተለያዩ ህዝቦች፤ ሀንጋሪያኖች፤ ሮሜኒያኖች፤ ፖሊሾች፤ ሩስያኖች፤ ያሉበትን ያጠቃልላል ተባለ።
በነዚህ የዩክሬን ብሔርተኝነት ልሂቃን ጸንፈኛ አቋም ምክንያት ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ዩክሬን የጸንፈኝነትና ጦርነት ቀጠና ሆናለች። የዩክሬን ብሔርተኞች አንዴ ፖሊሾችን፤ አንዴ ሮሜኒያኖችን፤ አንዴ ይህዶችን፤ እንዴ ሩስያዊዎችን ለማጥፋት ሲዠምቱ 150 አመት አሳልፈዋል። የጽንፈኝነት መጠናቸው የሚገልጸው በሁለተኛ የአለም ጦርነት ከናዚ ጀርማን ጋር ወግነው ከጀርመኖቹም በላይ ክፋትና ግድያ መፈጸማቸው ነው። የዩክሬን የፖለቲካ የገዥ መደብ ይሁን ሁሉ ያደረገው በብሔርተኝነት እጅግ ተጠምቆና ሰክሮ ሰባዊነት ሙሉበሙሉ ስለጠፋበት ነው።
የዩክሬን ህዝብ ያሳዝናል። ልሂቃኖቻቸው ማንነታቸውን በጸንፈኝነት እና ክፋት መሰረቱት እና ህዝባቸውን የክፋት ማንነት እስረኛ አደረጉት። ልሂቃኑ ህዝቡ ላይ ከጎረቤቶቹ ጋር በሰላም መኖር የሚችል ህዝብን ከጎረቤቱ ጋር የሚስማማ፤ ጠላት የሌለው፤ ዩክሬን ጣኦቱ ያልሆነ፤ ዩክሬናዊ አይደለም የሚለውን ትርክት ጫኑ በት። እጅግ ያሳዝናል።
ኢትዮጵያውስጥም ይህ አይነት ጸንፈኛ ዘመናዊ ብሔርተኝነት አይተናል ባለፉት 50 አመታት። የህወሓት ብሔርተኝነት አንዱ ግልጽ ምሳሌ ነው። አማራ ጠላት ነው፤ ወርቃማ ዘር ነን፤ ክርስትናም ሙስሊምነትም ከትግሬነት በታች ናቸው፤ ትግሬነት ብቸኛ እምነት/ጣኦት ነው። ይህ የህወሓት የትግራይ ብሔርተኝነት አማራን ብቻ ሳይሆን ኤርትርንም፤ ኦሮሞንም በተለያዩ ወቅቶች ፍጹም ጠላት ብሎ ሰይሟል! ታላቋን ትግራይ በራይ ደረጃ አስቀምጦ ለማስፈጸም ጦርነት አውጇል። ሚስኪን የትግራይን ህዝብ በዚህ ክፉ ርእዮት አለም አፍኖ አስክሮ ገድሎታል። እጅግ ያሳዝናል።
በኦሮሞ ብሔርተኝነትም እንደዚህ አይነት ጸንፈኛ ባህሪዎች ይታያል። ጠላት፤ አማራ። (አማራ ቢያንስ ለ32 አመት ግን ለ46 አመትም ማለት ይቻላል ስልጣን ይዞ አያውቅም ለስልጣን ታግሎም አያውቅም!)። ተረት፤ ኦሮሙማ (ኦሮሙማ የጥነትና ባህላዊ ሳይሆን ልሂቃን በዘመናዊ መንገድ manufacture ያደረጉት ብሔርተኝነት ነው "Being and Becoming Oromo" )። ሁሉ ገዥነቱ ደግሞ በሃይማኖት ላይ የሚያደርገው ዘመቻ ያሳያል፤ ኦርቶዶክስም ሙስሊምም ኦሮሞ ኦሮሙማ ከሃይማኖቱ በላይ መሆን አለበት ነው። ቄስ/ሼክ ትዛዙን ከኦሮሞ ብሔርተኛ ፖለቲከኛ ነው መቀበል ያለበት!
በመርህ ደረጃ የኦሮሞ ማንነት ተደፋፍኖ ነበር፤ ጭቆና ነበር፤ ማለት ይቻላል። ግልጽ ነው። የኦሮሞ ህዝብ እንደማንኛውም ህዝብ ማንነቱ መከበር አለብት ብቻ ሳይሆን ማንነቱን ለጎረቤቱ ማካፋል አለበት ማለት ይቻላል። ይህ ተፈጥሯዊ ነው ጤናማም ነው። ግን እነዚህ ትክክለኛ፤ ሰላማዊ እና ጤናማ መርህዎች በዘመናዊ ጸንፈኛ ብሔርተኝነት ተጠልፈዋል። የኦሮሞ ጸንፈኛ ልሂቃን ህዝቡን አስሮ ወይ ከኛ ጋር ነህ ወይንም ኦሮሞ አይደለህም ብለውት እጅግ እየጎዱት ነው።
ዘመናው ብሔርተኝነት አደገኛ ነው በቀላሉ ወደ ጽንፈኝነት ማየል ስለሚችል። ይህን recognize ማድረግ አለብን። የልሂቃን ሚና ከባድ እንደሆነ መረዳት አለብን። የሚመጣውን ጸንፈኝነት እንዴት መቅረፍ እንደሚቻልም ማጥናት አለብን። ግን ጸንፈኛ ብሔርተኝነት በጸንፈኛ ብሔርተኝነት አይሸነፍም። Scorthed earth እንደ ማሸነፍ ካልተቆጠረ! ዘዴና ብልህነት ይጠይቃል።
No comments:
Post a Comment
ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!