2009/1/29
ዓ.ም.
(2016/10/9)
(pdf)
ፖሊሱን
ምንድነው የሚያበሳጭህ
ብዬ ስጠይቀው እንደዚህ
ይለኛል።
«አድሎው
በዛ፤ እድገት «ለነሱ
ሰው»
ብቻ ነው፤
ምርጥ ቦታ «ለነሱ»፤
የማይፈለግ
ስራ ለሌላው። አይን ያወጣ ነው
እኮ!
ሰዉ
እጅግ መሮታል»
ለመንግስት
እቃ የሚያቀርብ ነጋዴ
እንደዚሁ ብሎ
ይነግረኛል።
«ኮንትራቶች
አገኛለሁ። ግን ምርጥ ኮንትራቶች «ለነሱ»
ብቻ
ነው።
ጊዜ
ቢያሳልፉም ጥራት ቢያጎሉም ምንም አይባሉም።
እንደ
በፊቱ አይደለም፤ አሁን
አይን
ያወጣ ሆኗል፤ ሰዉ
በጣም ተናዷልና ሁኔታው ያስፈራል»
ባለ
ሀብቱም እንደዚሁ አይነት
እሮሮ
ያሰማኛል።
«አዎ
ደህና መሬት ማግኘት እችላለሁ
ግን ምርጥ ቦታዎቹ «ለነሱ»
ሰው
ነው። አንድ
ቆንጆ ቦታ አግንቼ ከፍተኛውን ብር ተጫርቼ
«ለነሱ»
ተሰጠ።
እጅግ
ተበሳጭቻለሁ።
አይን ያውጣ
አድሎ
ነው»
ይለኛል።
በተዘዋዋሪ
ይህ ባለ ሀብት ከገዥ
ፓርቲው ጋር በሚያስፈልገው
ደረጃ ግንኙነት አለው።
የዩኒቨርሲቲ
ተማሪውም ከትንሽ ውይይት
በኋላ
ወደዚሁ አርእስት የገባል። «የነሱ»
ተማሪዎች
የሚያገኙትን እርዳታ ብታይ። ትርፍ ትምህርታዊ
ምክር፤ ሳምፕል ፈተናዎች፤ ከነሱ አስተማሪዎች
በትርፍ ግዜ እርዳታ»
ዝምብሎ
ከማማረር ለምን እናንተም እንደዚህ አታረጉም
ብዬ ጠይቀዋለሁ።
ጥያቄዬን
ያልፈዋል፤ ስለ «እነሱ»
ነው
ማውራት የሚፈልገው።
«እነሱ»
ማን
እንደሆኑ ሁላችንም እናውቃለን። አዎ በትክክሉ
ለመናገር የኢህአዴግ አባላትና አደርባዮቻቸው
ናቸው። ግን ሰዉ
«እነሱ»
ሲል
ባጭሩ
ትግሬዎች
ማለቱ ነው፤ አድሎ ሲል የትግሬ አድሎ ማለቱ
ነው።
እውነቱን
ለመናገር የትግሬ አድሎ ገርሞኝም
አያቅም። የመንግስታችን
አወቃቀር ይህን
አድሎ የሚያስከትል ነው።
የአንድ
ፓርቲ አገዛዝ
ነው ያለን።
የፖለቲካ
ተቀናቃኝ
የለም
አይፈቀድምም። እንኳን የነፃ
ምርጫ
ከፊል
የነፃ
ምርጫ የለም። በዚህ አይነት የ«አውራ
ፓርቲ»
አገዛዝ
ሁልግዜ ለፓርቲ አባላትና ለአደርባዮቻቸው
ከፍተኛ
አደሎ ይኖራል። በደርግ ዘመን ለኢሳፓ አባላት
አድሎ አልነበረምን?
በኃይለ
ስላሴ ዘመን
ከቤተ መንግስት ግንኙነት ያላቸው የተሻለ
ያገኙ አልነበረምን?
የዛሬውም
እንደዚህ ነው።
ይህን
ሃሳብ ስናገር አብዛኛው አዳማጭ
ይገረመዋል።
«የዛሬው
አድሎ
ግን በዘር
ነው እኮ»
ይሉኛል።
አዎን
የዘር
አድሎ ነው
ግን ህይ የዘር አድሎ፤
ማለት የትግሬ አድሎ፤
መኖሩንም
ልንገረም
አይገባም። ሁላችንም የኢህአዴግን
ታሪካዊ
አመጣጥን
እናውቃለን።
ከመጀመሪያው
ህውሃት
ከኢህአዴግ
ከፍተኛ
ኃይል ያለው
ፓርቲ ነበር
ዛሬም ነው፤
ቶር ስራዊቱንና በተለይ ደህንነቱን እንደሚቆጣጠር
እናውቃለን። ደግሞ
በአንድ
ግንባር
ወይም ፓርቲ
አገዛዝ ከዛ
ፓርቲ ውስጥ ኃይል
ያለው
ቡድን
ይበልጥ
ሙስና
አድሎ
ይታይበታል!
ለምን
ቢባል ሙስናና
አድሎ ዋና የኃይል ማከማቸትና ማንጸባረቅ
መንገድ
ናችሀው።
ምርጫ ወይም የፖለቲካ ውድድር ሰለሌለ ኃይል
በዚህ መልኩ ነው የሚከማቸው። በአውራ
ፓርቲ አገዛዝ ሌላ
አካሄድ ሊኖር
አይችልም።
ይህ
ሁሉ እያልኩኝ ሳለ
በኔ
አመለካከት የትግሬ
አድሎ ካሉት
የሀገራችን የፖለቲካና
ህብረተሰባዊ ችግሮች
ትንሹ
ነው። ለኢህአዴግ ግን
ዋናው ችግሩ
ነው!
ይህ
እንዴት ይሆናል?
ለኔ
ዋናው ችግር የአንድ ፓርቲ የልማት መንግስት
አገዛዙ የህዝቡን የአንድነትና
የህብረተሰባዊ
መንፈስ እያጠፋ መሆኑ ነው። ከሌሎች
ጽሁፎች
እንደጠቀስኩት የኢህአዴግ
መንግስት
ለህዝቡ ያቀረበው
ውል እንዲህ ነው፤ ልማት
ሰጥሃለሁ፤
አንተ
ደግሞ በስልጣኔም
ይሁን በሙስናዬ
አትምጣብኝ።
በዚህ ውል
መሰረት
ሰዎች ከመሬታቸው ይፈነቀላሉ። መሬታችሁ
ለባለ ሀብት ይፈለጋል እየተባለ
ሳንቲም ተሰተው ይባረራሉ፤ ክስ ላይ ባለስልጣኑ
ወይም አደርባዩ ጥፋተና ቢሆንም ይረታል፤
ሰዎች ትንሽ ጸረ ኢህአዴግ ነበር ቢናገሩ
ይታሰራሉ፤
ህዝቡ ከፍርድ ቤት ፍትህ አያገኝም፤
ጉቦ ካልሰጠ ውይም ወዳጅ ከሌለው ንብረቱን፤
ስራውን፤
ወዘተ ሊያጣ
ይችላል። ለኔ
እነዚህ ችግሮች ከትግሬ
አድሎ እጅግ
የሚበልጡ ናቸው።
ፍትህ፤ ነፃነት፤ ወዘተ አለመኖራቸው
ነው ዋናው ችግር። ሁለተኛ ደረጃ
ችግር
የማንም
አድሎ።
ሶስተኛ ደረጃ
ችገር የትግሬ
አድሎ
ነው።
በተዘዋዋሪ
ባለንጀራችን
መሬቱን ሲቀማ፤ አለ አግባብ ሲታሰር፤ ፍትህ
ሲያጣ፤
ወዘተ ማንኛችንም
ዞር ብለን
እንርዳህ አንለውም።
አይዞህ ብለን
የገንዘብም ወይም ሌላ
ድጋፍ አንሰጠውም።
የራሳችንን
ኑሮ፤ የራሳችንን
የ«ልማት»
ድርሻ
እያሳደድን
ባለንጀራችን
እየተጎዳ
ዝም እንላለን።
ምንስት
ላይ ጮኸን እንታሰር አደለም። እንርዳው፤
ግን አንረዳውም። ታላቁ
ችግር ይህ ነው። እውነቱን
ለመናገር ኢህአዴግን በስልጣን እስካሁን
የጠበቀውም ይህ መንፈስ ነው።
ግን ይህ መሰረታዊ ችግር እያለ መንግስቱን የሚያናጋው የዘር ችግሩ ነው። ይህ የሰውን አስገራሚ ባህሪ ያሳያ። «ሀገሬን በዚህም በዛም አበላሽ ግን በዘሬ አትምጣብኝ! ጉቦኛና ዘራፊ ሁን ግን በዘር ስም አታድርገው!» እኛ ኢትዮጵያዊያን እንዲህ እንላለን። ያሳዝናል።
ይህን አውቆ ኢህአዴግ የዘራውን ነው የሚያጭደው። ግን ለሀገሪቷ ህልውና አይበጅም። እኛ የ«ትግሬ አድሎ» ሳይሆን ምንም አይነት «አድሎ»ን አንፈልግም ስንል ነው ሀገራችን የሰላም መንገድ የምትጀምረው።
ይህን አውቆ ኢህአዴግ የዘራውን ነው የሚያጭደው። ግን ለሀገሪቷ ህልውና አይበጅም። እኛ የ«ትግሬ አድሎ» ሳይሆን ምንም አይነት «አድሎ»ን አንፈልግም ስንል ነው ሀገራችን የሰላም መንገድ የምትጀምረው።
No comments:
Post a Comment
ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!