አንዱ ከብዙ የጠ/ሚ አብይ አህመድ ልዩ የሚያረጋቸው ችሎታዎች የቅራኔ መፍታት አቅማቸው ነው። ትዕቢት፤ ቂም፤ አሉታዊነት፤ ትቶ የሁሉንም ትቅም የሚያስከብር ለሁሉም ተመራጭ የሆነ ግባ ላይ በማተኮር ችግሮችን ፈትተዋል አሁንም እየፈቱ ይገኛሉ። ይህ አቅማቸው ከኢትዮጵያ ፖለቲካዊ መሪዎች ለዘመናት ታይቶ አይታወቅም (https://ethsat.com/2018/10/ethiopia-soldiers-show-up-unannounced-at-national-palace-pm-orders-pushups/)።
@Samuel Abebe (በዚህ ትችት ላይ https://www.facebook.com/abdurahman.ahmedin.7/posts/2120966214582614?comment_id=2121015731244329) ሁላችንም በውስጣችን የምናስበውን ታላቅ ጥያቄ ጠየቀዋል፤
«መለወጥ ስህተትን ከመቀበል ይጀምራል ይባላል ትልቅ ስህተት ተፈጽሞም ከቅንጅት አመራሮች ስህተቱን ተቀብሎ እዚህ ላይ ይህን ባንሳሳት ኑሮ የሚል አመራር እንዴት ይጠፋል? ሁሉም ወደ ሌላ ሰዉ ጣቱን ይቀስራል፡ እኛስ የትኛዉን አምነን የትኛዉን እንቀበል?»
ዋና እና ተገቢ ጥያቄ ነው። ብስለት እና እውቀት የሞላው። በማንኛውም ቅራኔ አንድ ጥፋተኛ እና ሌላው ንፁሃን የለም (there are two or more sides to any conflict)። ይህን ሃቅ ማንኛውም ስለቅራኔ የሚያውቅ ባለሙያ፤ ማንኛውም የካህን፤ ማንኛውም አስተዳዳሪ፤ ማንኛውም ወላጅ የሚያውቀው ነው። ግን ብናውቀውም እንዳማናውቀው አድርገን ነው የምንኖረው። ቅራኔ ውስጥ በተገኘን ቁጥር እራሳችንን ፍፁም ንፁህ ሌላው ፍፁም ጥፋተኛ አድርገን ነው የምንቆጥረው።
ይህ ከገባን በቅንጅት ቅራኔ ህሉም ተሳታፊዎች የተወሰነ ሚና መጫወታቸውን ሊገባን ይገባል። የፈረደበት ልደቱ ጥፋት ብቻ ሊሆን አይችልም። ዋናው ችግር የሱ ነው ቢባልም ያንን ችግር ማስተናገድ አለመቻል በራሱ ትልቅ ድክመት ነው! መታመን ያለብት እና ይቅርታ የሚጠየቅበት ድክመት ነው። ታላቅ መማርያ የሚሆን ድክመት ነው።
እንደ ቅንጅት አይነት ታላቅ ድርጅት፤ እጅግ ግዙፍ የሆነ የሀገር ሃላፊነት ያለው ድርጅት ሲፈርስ ሁሉም በአመራር ያሉት በመፍረሱ ሚና ተጫውተዋል እና ሁሉም ድክመታቸውን አምነው ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል። እኛም ደጋፊዎቻቸው እንዲሁም። ያደረግነውን ስህቶቻችንን ካመንን በኋላ ብቻ ነው መማር የምንችለው እና እንዳንደግማቸው ማድረግ የምንችለው።
የቅንጅት ታሪክ ከብዙ የሀገራችን ፖለቲካ የቅራኔ መፍታት አለመቻል ታሪኮቻችን አንዱ ነው። እንዳውም በኔ እምነት የፖለቲካ እና ማህበራዊ ችግሮቻችን ዋና ጎልቶ የሚታየው ምክንያት «የቅራኔ መፍታት (conflict resolution) ጉድለታችን» ነው። በዚህ ዙርያ ብዙ ተጽፏል እና ተነግሯል ግን በቂ አልተደረገም። ዛሬም የምናያቸው ነገሮች አሉ፤
1. አንድ «አቋም»፤ ርዕዮት ዓለም፤ አስተያየት ኖሮን አብሮ መስራት አለመቻል
2. የራሳችንን ጥቅም ጎድተን ቂማችንን ለመወጣት የምናደርጋቸው ስህተቶች
3. የጋራ ማሸነፍን ከመፈለግ (አሁንም የራሳችንን ጥቅም ቢጎዳም) ሌላው እንዲሸነፍ መመኘት እና መስራት
4. ፖለቲካን እንደ ሃይማኖት ፍፁም እውነት እንዳለው መቁጠር።
የፖለቲካ አካሄዳችን እንዲሻሻል ከተፈለገ ስለነዚህ ጉዳዮች መያየት እና መፍትሄ ማግኘት ግድ ነው።
ቅራኔ መፍታት ለኛ ኢትዮጵያዊያን አዲስ ነገር አይደለም። የድሮ ንጉሶቻንን አድርገውታል። ይህን የሚያስፈጽሙ በርካታ ባህላዊ መንገዶች አሉን። ከሃይማኖታችን ደግሞ መሰረታዊ ቅራኔ መፍታት ምክንያቶችንም ዘዴዎችም አሉ። ለምሳሌ በክርስትና «ንስሃ» ማለት ማለት 1) ስተትን ማመን 2) እንዳይደገም 3) ሌላው እንዲገባው 4) እራስን ለማረም 5) እራስን ለማወቅ ወዘተ። ውየንም «አለመፍረድ» ማለት 1) ለሌላው መቆርቆር (empathy) 2) የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ ችኩሎ አለመድረስ 3) ጣት ጠኩሞ የራስን ችግር መርሳት ወዘተ።
ስለዚህ አሁን ማድረግ ያለብን እነዚህን (ምናልባት የተረሱ) ባህላዊ እሴቶችን እንደገና ማስነሳት እና ማሰራጨት ነው። ከባድ ስራ ነው ግን ምርጫ የለንም!
http://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/09/blog-post_21.html
የሰላም ክፍሌ ይትባረክ ብሎግ፤ ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለኝን ትናንሽ ሀሳቦች በትህትና አቀርባለሁ። ለስሕተቶቼም በቅድሚያ ይቅርታ እጠይቃለሁ
Showing posts with label compromise. Show all posts
Showing posts with label compromise. Show all posts
Wednesday, 10 October 2018
Monday, 27 August 2018
Some thoughts on Oromiffa as the second federal language...
I fully support the idea that Oromiffa should become the second federal language, for various reasons. These include the relatively large number of Oromiffa speakers in Ethiopia, political events over the past few decades, including Oromo nationalism, Oromo region ensuring Amharic is not taught in Oromo schools as part of its drive towards Oromo nationalism, thereby created facts on the ground to force the issue, etc. make this seem to be the most prudent political direction. And I would add - and I would consider this the most important benefit of having Oromiffa as a federal language - that this can actually reduce ethnic nationalism and thereby ethnic conflict by increasing integration and the integrated population. I've written previously about this (https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2016/09/curbing-ethnic-nationalism-via_26.html and http://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/07/towards-integrated-ethiopia.html). To repeat, this means that by making Oromiffa a federal language, and thereby, for example, encouraging Amhara Region to achieve full fluency in Oromiffa, we increase integration, and we reduce ethnic nationalism, which for me is one of the existential issues for Ethiopia.
However, I think there are two very important points to make here. First, the issue of Oromiffa as a federal language is often presented as one of principle, and this is done so to claim a moral high ground. I think that in order to avoid building on sand, we have to be honest and acknowledge that this is a political issue, not one of 'principle', insofar as principle exists. By principle I mean values such as equality, restoration, fairness, etc. By principle, a Somali can demand the same for the Somali language. Why should Amharic and Oromiffa be privileged, he can rightly ask? He might even add that while before only Amharic speakers had an 'advantage' over him, now both Amharic and Oromo speakers have this 'advantage'. (I put 'advantage' in quotes because it can easily be considered a disadvantage. A Somali who is properly taught Amharic and Oromiffa in school becomes trilingual whereas the Oromo remains monolingual - the Somali is better off.) So let us not pretend this is an issue of principle, of righteousness vs unrighteousness, of morality vs immorality, of oppressed vs oppressor. Oromiffa becomes a federal language not because of the need for equality, restoration, or fairness, but for political and practical reasons, for the same reasons as Amharic remains, because it is spoken, natively or not natively, by a large number of citizens who have the political power to enforce their demand.
A second, implicit idea in all of this is the desire for many to make this a political negotiating tool vs Oromo ethnic nationalism. "If you want us to support you in making Oromiffa a federal language, then give us ... in exchange." What most are asking in return is, I think, a revision of ethnic federalism to make it less ethnic and more national - a revision of the constitution in other words. Some are also asking for culturally symbolic concessions such as changing the script to Geez. As I said above, given that the demand is political, the demand for political concessions is certainly fair, in my mind. It makes sense, and it makes sense to carry this into the negotiating room and the public discussion sphere. What will come of it, we'll see.

Wednesday, 5 October 2016
ፖለቲካ ሃይማኖት አይደለም!
2009/1/24
ዓ.ም.
(2016/10/4)
(pdf)
ዛሬም
ጠንካራ፤ ህዝብን የሚወክል፤ ኢህአዴግን
በመጠኑም ቢሆን ሊጋፈጥ የሚችል የተቃዋሚ
ድርጅት በኢትዮጵያ የለም። (ደህና
የሚባለው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስም
በምንም ሚዛን እነዚህን መስፈርቶች አያሟላም።)
ይህ
እውነታ ሁላችንም የምናውቀው ነው፤ የዛሬው
የህዝብ እንቅስቃሴ ከቀጠለና ከጨመረ አለመሪነትና
ድርጅት እንዴት ይሆናል ብለን እንሰጋለን።
ኢህአዴግ
ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ለ25
ዓመት
ደህና ተቃዋሚ ድርጅት ኖሮ አያውቅም። የነበሩትም
ያሉትም ደካማ፤ በቀላሉ የሚፈሩና የሚበታተኑ፤
እርስ በርስ ተጣልተው እራሳቸውን ከጥቅም
ውጭ የሚያደርጉ ወዘተ ናቸው።
የዚህ
ሁኔታ ያልሆነበትን ምክንያት ተጠንቅቀን
እናውቃቸዋልን። ኢህአዴግ ጠንካራ ስለሆነ
አይደለም። ተቃዋሚዎች ኢህአዴግ ጥቂት ህዝብ
ነው የሚወክለው እያልን በዛው ትንፋሻችን
ጠንካራ ነው ማለት አንችልም!!
ኢህአዴግ
በኃይሉ ሳይሆን በፈቃዳችን
እንደሆነ የሚገዛው እናውቃለን፤ እራሳችንን
አናታልል።
ታድያ
ለምንድነው ተቃዋሚው ለመደራጀትም የሚያቅተው።
እንደምናቀው አንዱ ዋና ችግር የተቃዋሚ
ፖለቲከኖችም ህብረተሰብም የአለመስማማት፤
እርስ በርስ መጣላት፤ እሩቅ ማሰብ አለመቻል፤
ወዘተ ነው። ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ተጽፏል።
ሆኖም ከዚህ ጽሁፍ አንድ ሌላ ተቃዋሚን
የሚያደክመው ምክንያት ላቀርብ እወዳለሁ፤
ይህ ፖለቲካን እንደ ሃይማኖት ማየትና የሚከተለው
ግትርነትና አለመቻቻል።
ሃይማኖት
በአንድ እውነት የተመሰረተና የማይቀየር
ነው። ለምሳሌ እንደ ኦርቶዶክስ ክርስቲያንነቴ
ክርስቶስ ሞተና በሶስተኛው ቀን ተነሳ ብዬ
አምናለው ከዚህ እምነትም ዝንፍ አልልም፤
ይህ ፍፁም እውነት ነውና።
ግን
ይህንን ዝንፍ አለማለትን ወደ ፖለቲካ ወይም
ሌላ የህይወት ዘርፍ ማምጣት የለብኝም። ቅንጅት
ፓርላማ ይግባ አይግባ ፍፁም እውነት ያለው
የሃይማኖት ጉዳይ አልነበረም፤ ከሁለቱም
አቋሞች ጥሩ የሆኑ የሚያስኬዱ ምክንያቶች
ነበሩ። የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ጎሳን ያካትት
አያካትት፤ ይህም የድርድር ጉዳይ ነውንጂ
እውነትና ውሸት የለበትም። ወዘተ። በፖለቲካ
ወይም በስራ ወይም በቤተሰብ ኑሮ መደራደር፤
የሌላውን አስተያየት መረዳት፤ ለሌላው
መቆርቆር፤ ላለመስማማት መስማማት፤ ወዘተ
አስፈላጊ ነው።
ለምሳሌ
ስንቶቻችን ነን የተለያዩ የፖለቲካ አቋሞቻችንን
ቀይረን የማናውቀው?
አንዳንዶቻችን
የኃይለ ስላሴን መንግስት በግዜው እንደግፍ
ነብር ዘሬ ግን ዴሞክራሲአዊ አለመሆኑን
አንወድም እንላለን። ስንቶቻችን በኮምዩኒዝም
በኢህአፓ ወዘተ እናምን ነበር ዛሬ ግን ተሳስተን
ነበር እንላለን። ስንት የደርግ ደጋፊ የነበሩና
አሁን ንስሃ የገቡ አሉ። እርግት ኢህአዴግንም
በአንድ ወቅት የደገፉ አሉ!
ታድያ
ሃሳባችንን ሲያስፈልግ የምንቀይር ከሆነ
ለምንድነው ከኛ ፖለቲካዊ ሃሳብ ጋር የማይስማማ
ባልደረባ ሲያጋጥመን ከሱ ጋር ጦርነት የምንገባውም
የጋራ ፖለቲካ ድርጅታችንንም የምናፈርሰው?!
ይህ
የሚሆነው ፖለቲካን እንደ እምነት ምንም ድርድር
የማይደረግበት ነው ብለን ስለምንቆጥር ነው።
በፖለቲካ
ደረጃ መስማማት፤ አለመከፋፈል፤ አንድ መሆን
ከፈለግን የሃሳብ ልዩነቶችን በሚገባው በትህትና
መቀበልና ማስተናገድ አለብን። የግትርነትና
አጉል እረግጠኝነት መንፈሳችንን ማስወገድ
አለብን። እንደዚህ ማድረግ ስንችል፤ በተለይ
የፖለቲካ ትህትናችንን ማዳበር ስንችል ነው
የተቃዋሚ ድርጅቶቻችንን በቂ አቅም እንዲኖራቸው
ማድረግ የምንችለው።
ትህትናና
ግትር አለመሆን፤ እነዚህን ብቻ እናስታውስ።
Subscribe to:
Posts (Atom)