Friday 17 November 2017

ከማነኛዉ ወገን ነህ? ቄሱ!

(from Father Arseny: Priest, Prisoner, Spiritual Father)

በመጀመሪያ ወደ እስር ቤት ስትገባ ቀናትን ትቆጥራለህ፣ ከዚያም ሳምንታትን፣ ከሁለትዓመታት በኋላ በሚመጣዉ ጊዜ የምታደርገው ሞትን መጠበቅ ብቻ ነው፡፡ አድካሚ የጉልበት ሥራ፣መራራ ረሐብ፣ እርስ በእርስ መናቆር፣ መደባደብ፣ ብርዱና ከቤተ-ሰብ መለየቱ ያደድቡህናየማይቀረውን ሞት ብቻ እንድታስብ ትሆናለህ፡፡ ስለዚህ አብዛኛዎቹ እስረኞች በስነ-ምግባር ረገድደካሞች የሚሆኑት፡፡

ለብዙዎቻችን የፖለቲካና ለሁሉም የወንጀለኛ እስረኞች ስሜታችን እንደ ሁኔታዉ ግራና ቀኝየሚዋልል ነበር፣ የአለቃው ቁጥጥር፣ የሚሠረቅ ዳቦ፣ እርስ በእርስ መናቆር፣ በተለይ በእስር ቤቱለተመደቡ እስረኞች የተመደበው እጅግ ከባድ የጉልበት ሥራ፣ ልዩዉ የቅጣት ክፍል፣ በረዶየሚሆኑ ጣቶች ወይም በጎረቤት የእስር ቤቱ ክፍሎች ውስጥ የሚሞቱት እስረኞች ስሜትንለመቀያየር ምክንያቶች ነበሩ፡፡ ሐሳብህ ሁሉ ተራና በእነዚህ ላይ ብቻ የሚያተኩሩ ይሆናሉ፡፡ እጅግበጣም የአያሌዎቹ እስረኞች ሕልም እስከሚጠግቡ በልተው ለሁለት ወይም ለሦስት ሰዓታት ያህልመተኛት ወይም ግማሽ ሊትር ቮድካ አግኝተው ሁሉንም ጨልጠው እንደገና ሌላ ተጨማሪ ምግብቢሰለቅጡ በወደዱ ነበር፣ ይሁን እንጂ እነዚህ ሁሉ ባዶ ምኞቶች ብቻ ነበሩ፡፡

እጅግ በጣም ትቂት የፖለቲካ እስረኞች በተቻላቸው መጠን ርኅሩኅ ሆነው ለመቆየት ሞከሩ፣ራሳቸውንም ከሌላዉ በመለየት፣ እርስ በእርስ በመደጋገፍና ራሳቸውን ወደ ተራ የወንጀለኛ እስረኞችዝቅ ላለማድረግ እየጣሩ ነበር፡፡ በተቻላቸው መጠን የእስር ቤቱ ደንብ በሚፈቅደው መሠረትራሳቸውን በማያዋርድ ሁኔታ ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከእስር ቤቱ የበረንዳ ማዕዘን ላይ ቆመውቃለ-ተናብቦ/ሌክቸር ያደርጋሉ፣ ግጥም ወይም አጭር ሳይንስ-ነክ ጽሑፍ ያነባሉ፣ አልፎ አልፎምየትም ባገኙት ብጣሽ ወረቀት ሳይቀር ማስታዎሻ ይጽፋሉ፡፡ በሆነ ርእሰ-ጉዳይ ላይ ሞቅ ያለ ክርክርይነሣል፣ ይሁን እንጂ እጅግ በጣም የሚጦፈው ፖለቲካን አስመልክቶ የሚደረገው ክርክር ነበር፡፡አልፎ አልፎ የወንጀል እስረኞችም ሳይቀር በክርክሩ ይቀላቀሉ ነበር፤ ፖለቲከኞች በፖለቲካ ረገድብዙም ፍላጎት አይታይባቸውም፣ ይሁን እንጂ አልፎ አልፎ ፍላጎቱ ነበራቸው፡፡ ሰዎች በስሜትየሚቃወሟቸውን በጥላቻ ይከራከሯቸው ነበር፡፡ አባ አርሴኒ በዚህ ክርከር ፈጽመው አይሳተፉም፡፡ነገር ግን ከዕለታት አንድ ቀን ያለፍላጎታቸው ተጎትተው ገቡ፡፡

ምንም ጊዜም እስረኞች ሐሳባቸውን ለመግለጽ ይፈራሉ፣ ይሁን እንጂ ወደሞቀ ክርክርውስጥ ሲገቡ ፍርሃት ሊያስከትል የሚችለውን ነገር ሁሉ ይረሱታል፡፡ በክርክሩ ከሚሳተፉት መካከልትቂቶቹ የአሰብሁትን መናገር ሳልችል ድምፄ ታፈነ፣” ይላሉ፡፡

እስረኞች ተቆጥረው የእስር ቤቱ በሮች ተቆለፉ፣ ከግድግዳዉ በስተጀርባ ነፋሱ እየነፈሰነበር፤ ግግሩ በረዶ መስኮቶችን እንዳይከፈቱ አደረጋቸው፣ ክፍሉ የታፈነና ዕርጥበት-አዘል ነበር፣ሆኖም ግን ውስጡ ሞቃት ነው፡፡ አምፖሎቹ ከሚፈለገው ከግማሽ በታች ብርሃናቸው መጠን ባነሰያበሩ ነበር፡፡ እነዚህ ሁሉ ትካዜና ሐዘን እንዲኖር ያደርጋሉ፡፡ በመሆኑም ሰዎች ብቸኛ ይሆናሉ፡፡እስረኞቹ በአንድነት ተሰበስበው መነጋገር፣መከራከርና ያለፈውን ማስታወስ ጀመሩ፡፡ ወንጀለኛእስረኞች ካርድ ወይም እንዶሚኖ ለብር ወይም ለመቁኑን እየተጫወቱ ነበር፡፡ አባ አርሴኒ ካረፉበትአልጋ አጠገብ የተሰበሰቡ እስረኞች በመንግሥት ላይ ያላቸውን አመለካከት ርእሰ-ጉዳይ በማድረግኃይለኛ ክርክር አደረጉ፡፡ በ15 ደቂቃዎች ውስጥ 20 የሚሆኑ ሰዎች ወደ ክርክሩ ተቀላቀሉና ክርክሩጦፈ፡፡ አንዱ የአንዱን ንግግር በማቋረጥ ሥጋት ጨመረ፡፡ ከተከራካሪዎች መካከል ቀድሞ የፓርቲአባል የነበሩ፤ ከልዩ ልዩ የሕይወት ተሞክሮዎች የተማሩ ሰዎች፤ በጣም ትቂት ቭላስቶቭትሲዎችናx1ሌሎችም ነበሩ፡፡ “እዚህ ያለነው ለምድነው? ለምንም! ፍትሕ የት አለ? ሁሉም መረሸን አለባቸው!”በማለት ፊታቸውን አኮሳትረው ይጮሁ፡፡ አራት ወይም አምስት የሚሆኑ ቀድሞ የፓርቲ አባልየነበሩ በነገሩ ባለስማማታቸው “አሳዛኝ ስሕተት እየተፈጸመ ነው” በማለት ገለጹ፡፡ እንደአበባላቸውከሆነ እየሆነ ያለው ሁሉ እራሱ ስታሊን በማያውቀው በትቂት ሠርጎ-ገቦች በመሞኘት የሚፈጸምመሆኑን ገለጹ፡፡

“የሩስያ ሕዝብ ግማሹ በእስር ቤት ታጉሮ ሳለ ተታለልን! አስተዳዳሪዎቹም እንዲደመሰሱታቀደ!” በማለት አንድ ድምፅ ጮኸ፡፡

ስታሊን አሳምሮ ያውቃል፣ የራሱ ትእዛዝ ነው፣” አለ ሌላዉ፡፡

ስታሊንን በመግደል አሲርሃል ተብሎ የተያዘው ከስረኞቹ አንዱ እጅግ በጣም በመበሳጨቱድምፁ ተቆራረጠ፡፡ ትቂት ቭላስቭትስኪዎች ማነኛውንም ሐሳብና በመቃወም ጮኹ፡፡

“እነዚያ የፓርቲ አባላት መሰቀል ወይም መረሸን አለባቸው!” አለ ሌላ አንድ ሰው፡፡ከ1917 ዓ/ም ጀምሮ ዋና የቮልሼቪክ ፓርቲ አባል የነበረ አንድ ሽማግሌ ሰው በመጀርመንጦር ሠራዊት ውስጥ ካገለገለ ሰው ጋር ተደባደበና በኃይል መሳደብ፡፡

“አንተ ባንዳ ነህ!” ብሎ ጮኸ፡፡ “መረሸን ነበረብህ፣ ነገር ግን በሕይወት እስካሁን አለህ! እኔራሴ እንዳተ ያሉትን ባንዳዎች እረሽናቸዋለሁ ወይም እሰቅላቸዋለሁ፡፡ እስካሁን ድረስ ወደናንተባለመዝቴ አዝናለሁ፡፡ ስሕተትም ፈጽሜያለሁ፣ ይሁን እንጂ አንተ ባንዳዉ በዚህ እስር ቤት ውስጥከኔ ጋር ትሞታለህ ብየ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

“እኔ ባንዳ ነኝ? እኔ የሶቭየትን መንግሥት ከሚደግፉት አንዱ ነኝ!” “ማለት ትችላለህ፣ ነገር ግን አንተም ባንዳ ነህ፣ ለዚህ ነው መንግሥት እዚህ እስር ቤትያመጣህ፡፡”

በርቀት የነበሩ ሰዎች ሳቁ፣ ሆኖም ግን ክርክሩ በሞቀ ሁኔታ ቀጠለ፡፡ አንድ ሰው ድንገት“አብያተ ክርስቲያናትን አውድመው ሃይማኖትን አጠፉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ሰው ካጠገቡ ቁጭ(1) ያሉትን አባ አርሴኒን አስታወሰና “ደህና፣ ፒዮትር አንድሬየቪች ንገረን፣ ባለሥልጣናቱን እንዴትታያቸዋለህ?” ሲል ጠየቀ፡፡

አባ አርሴኒ ዝም ብለው ክርክሩን ሲያዳምጡ ቆዩ፣ ነገር ግን አሁን ያለፍላጎታቸው ወደክርክሩ ጎትተው ከተቷቸው፡፡ አባ አርሴኒ ምን እንደሚመልሱ ግልጽ ነበር፡፡ በእስር ቤቱ ውስጥ ብዙየተሰቃዩ ሰው ስለነበሩ የአባ አርሴኒ ጓደኞች ተጨነቁ፡፡

በጂትሎቭስኪ የሚመሩት ቭላስቭትሲዎች ከሌላዉ እስረኛ ራሳቸውን አግለው እየኖሩ ነበር፡፡የሚፈሩት ምንም ነገር አልነበረም፤ በምን ምክንያት እንደተያዙ ያውቃሉ፣ የሕይወታቸው ፍጻሜምቅርብ እንደሆም ይገምታሉ፡፡ ከነርሱ አንዱ “እንግዲህ በል አፍስሰው ቄሴ!” አለ፡፡

አባ አርሴኒ ላፍታ ዝም አሉና “የጦፈ ክርክር ስለያዛችሁ ክርክሩ ወደ ጭቅጭቅ ተቀየረ፣ሊትቆጣጠሩት ወደማትችሉት ደረጃ ደረሰ፡፡ በእስር ቤት መኖር አስቸጋሪ እየሆነ በመምጣቱሁላችንም ፍጻሜያችን ምን እንደሚሆን እናውቃለን፡፡ ክርክሩም መራራ የሆነው ለዚህ ነው፡፡የማይረሸን ወይም በሕይወት የሚተርፍ የለም፡፡ ሁላችሁም ባለሥልጣናቱን፣ ትእዛዛቱንና ሰዎችንትዎነጅላላችሁ፤ ሌላውን ለማስቆጣት ጎትታችሁ ወደ ክርክሩ አስገባችሁኝ፡፡

“ኮሚኒስቶች ምዕመናንን አስረዋል፣ አብያተ ክርስቲያናትን ዘግተዋል፣ ሃይማኖትን ትተዋልብላችኋል፡፡ አዎ፣ ላዩን ሲታይ እውነት ይመስላል፤ ነገር ግን እስቲ በጥልቀት እንመልከተው፣ያለፉትን ጊዜያት በጥልቀት እንመልከት፡፡ ከኛ ከሩስያውያውን ሕዝቦች መካከል ብዙዎቹሃይማኖታቸውን ክደዋል፣ ባለፉት ዘመናት ውስጥ ለነበሩ አባቶች ክብር መሥጠት አቆሙ፡፡በመሆኑም ብዙ መልካምና ብርቅ ነገሮችን አጠናል፡፡ በስሕተት ጎዳና እየሄደ ያለ ማነው?ባለሥልጣናቱ ብቻ ናቸውን? አይደሉም፣ እኛም ራሳችን በስሕተት መንገድ ላይ ነን፣ ስለሆነምአሁን ራሳችን የዘራነውን እያጨድን ነው፡፡

“በምሁራኑ፣ በመኳንንቱ፣ በነጋዴዎችና በሲቪሉ ማኅበረ-ሰብ የተደረጉትን መጥፎምሳሌዎች እናስታውስ፡፡ እኛም በቤተ ክህነቱ ዘርፍ ያለን ሰዎች የበለጠ ክፉዎች ነበርን፡፡“የካህናቱ ልጆች አርቲስቶችና አብዮተኞች ሆኑ፣ የካህናቱ ቤተሰቦች አባቶቻቸው በየምክንያቱበመዋሸታቸው እምነት ስላጡባቸው ካህናቱን ከነሃይማኖታቸው ናቋቸው፡፡ ከአብዮቱ ረጅም ዓመታትአስቀድሞ ካህናቱ ለነፍስ ልጆቻቸው ታማኝ እረኞች አልነበሩም፡፡ ቅስና እንደማነኛውም የሙያ ዘርፍበመቆጠሩ ካህናቱ በሀልወተ-እግዚአብሔር የማያምኑና ከቤተ ክርስቲያን በሚገኘው ገንዘብ እየጠጡየመጠጥ ሱሰኞች ሆኑ፡፡

“ካገራችን ገዳማት መካከል አምስቱ ወይም ስድስቱ የክርስትና ማዕከሎች ነበሩ፤ የቫላምገዳም፣ ኦፕቲና ፑስቲን ከነታዋቂ መምህራኑ/ስተራርትሲx2 ፣ ዲቬዮቭስኪ ኮንቬንትና እንዲሁምየሳሮቭ ገዳም ይገኛሉ፡፡ ሌሎችም ገዳማት አሁን እምነት-አልባ በመሆናቸው የሃይማኖተኛ መነኮሳትመገኛ ሳይሆኑ ተራ የማኅበረ-ሰብ መጠራቀሚያ ሆነዋል፡፡

“አሁን ሰዎች ከነዚህ ገዳማት ምን ይማራሉ? ምን ዓይነት ምሳሌ የሚሆን ነገርስ ተቀመጠ?“ልጆቻችንን በተገቢው መንገድ አላሳደግናቸውም፣ ጠንካራ የእምነት መሠረትአላስቀመጥንላቸውም፡፡ እንግዲህ ይህን ሁሉ ልብ በሉ! ለዚህ ነው ሰዎቻችን ፈጥነው ሁላችንንምየረሱን፣ ካህናቶቻቸውን ረስተዋል፣ እምነታቸውንና ቤተ ክርስቲያናቸውንም በመርሳት ለማፍረስቆርጠው ተነሡ፣ እንዲሁም የጥፋት ዘዴ በመቀመር ካህናቱ የጥፋት መሪዎች ሆኑ፡፡

“ይህን ሁሉ ልብ ካልነው ጣታችንን ወደባለሥልጣኖቻችን ብቻ አንቀስርም፣ ምክንያቱምየእምነት-አልባ ዘሮች ራሳችን ባዘጋጀነው አፈር ላይ ተዘሩ፡፡ ከዚያም እነዚያ ዘሮች ተራቡ፤ እናምመታሰርን፣ መሰቃየትን፣ የንጹሐንን ደም መፍሰስ አቆጠቆጡ፡፡ ይሁን እንጂ በሀገሬ ውስጥ የሆነውሁሉ ቢሆንም ዜጋዋ ነኝ፡፡ ካህን እንደመሆኔ መጠን ሀገራችንን የመጠበቅና የመርዳት ኃላፊነት(2):: እንዳለብን የነፍስ ልጆቼን እመክራለሁ፡፡ አሁን እየተፈጸመ ያለው መቆም አለበት፤ በፍጥነትመስተካከል ያለበት እጅግ ታላቅ ስሕተት ነው፡፡”

“ስለዚህ የኛዉ ቄሴም ኮሚ ሆንሃላ! አለ አንድ ሰው “ኮሚኒስት” የሚለውን ኮሚ ብሎበማሳጠር፡፡ ቅዱስ ትመስላለህ፣ ይሁን እንጂ አንተ በሁለት ቢላዋ የምትበላ አራጆ ነህ፣ ለካስ ቅስቀሳእያካሄድህ ነው! ለባለሥልጣናቱ እየሠራህ ነው!” አለና አባ አርሴኒን በመጥፎ ሁኔታ ገፍትሮከሚከራከረው ሕዝብ መከካከል አስወጣቸው፡፡

ክርክሩ በጦፈ ሁኔታ ቀጠለ፣ ነገር ግን ብዙ ሰዎች ቡድኑን እየተውት ወጡ፡፡

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ትቂት እስረኞች አባ አርሴኒን መበቀል ጀመሩ፡፡ በምሸት ደበደቧቸው፣አንድ ሰው ባልጋቸው ላይ የፊኛዉን ፈሳሽ ለቀቀባቸው፣ ሌላዉም ደግሞ መቁኑናቸውንሠረቃቸው፡፡ እኛ የርሳቸው ጓደኞቻቸው ደግሞ ካጥቂዎቻቸው ለመታግ ሞከርን፡፡ ሆኖም ግን አጥቂቡድኖቹ አመለ-ብልሹዎች ስለነበሩ ማነኛውንም ጉዳት የማድረስ አቅሙ ነበራቸው፡፡ባንድ ምሸት ጆራ ግሪጎሬንኮ የሚባል ከኪየቭ የመጣ ሰው አባ አርሴኒን የቭላሶቭቲዎች መሪወደ ሆነው ጂሎቭስኪ ወሰዳቸው፣ ጂሎቭስኪ ካልጋዉ ላይ ተጋድሞ ከጓደኞቹ ጋር እያወራ ነበር፡፡“ቄሴ፣ ከኛ ወገን ነህን ወይስ ከኮሚኒስቶች? ለእስር ቤቱ ባለሥልጣናት እየሠራህ መሆኑንደርሰንብሃል፣ ኑዛዜ ትቀበልና አሳልፈህ ለነሱ ትሠጣለህ፡፡ አሁን ምን እንደምናደርግህ እኛ ብቻ ነንየምናውቅ፣ ትምህርት ሊሆንህ የሚችል ምት እንመታሃለን፡፡ እንሂድ ጆራ! በቅድሚያ ግን ቄሴየሚለውን እንስማ፡፡”

ጆራ ግሪጎሬንኮ በሁሉም ሰው ዘንድ የተጠላ ነበር፡፡ አጭር፣ ወፍራምና ትክሻዉ ሰፋ በማለቱአንገት የሌለው ይመስላል፣ ፊቱ ጠባሳ ስለበዛበት መልከ-ጥፉ ሲሆን በሆነ ባልሆነው የሐሰትፈገግታ ፈገግ ይላል፡፡ ይህ ተዳምሮ ሰውየውን አስቀያሚ አድርጎታል፡፡ ምንም እንኳን የቭላሶቭአባል በመሆኑ ብቻ በእስር ቤቱ ውስጥ ቢገኝም በጀርመን ሠራዊት ውስጥ በመረሸን ተግባር ላይየተሳተፈ ነው የሚል የሐሜት ወሬ ይወራበታል፡፡ አባ አርሴኒ በዕርጋታ ወደጂትሎቭስኪተመለከቱና “በሰዎች ሕይወት ላይ መወሰን የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ አንተ አይደለህም፡፡የአንተ ቡድን አባል አልሆንም፣” አሉት፡፡ ከዚያም ከጂትሎቭኪ በተቃራኒ ካልጋው ላይ ቁጭ አሉና“ልታስፈራራኝ አትሞክር፡፡ ለኡኡታ፣ ለድብደባና ለሞት ዛቻ ቤተሰቡ ነኝ፡፡ በዚህ ዓለም ላይየምኖረውን ጊዜና የእያንዳንዳችንን ዕድሜ በሚወስን በእግዚአብሔር ያለምንም ቅድመ-ሁኔታአምናለሁ፡፡ የምሞትበት ጊዜ አሁን ከሆነ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ እኔም ሆንሁ አንተ ይህንመለወጥ አንችልም፡፡ ሁላችንም እንደሥራችን ሊፈረድብን ወደእግዚአብሔር ፍርድ መቅረባችንአይቀርም፡፡

“በእግዚአብሔርና በደጋግ ሰዎች መልካም ሥራ አምናለሁ፣ እስከመጨረሻዋ እስትንፋሴድረስ በዕርግጥም አምናለሁ፡፡ አንተስ? አምላክህ የት አለ? እምነትህስ የት አለ? ስለሚሳደዱትአሳዳጆች ብዙ ትናገራለህ፣ ነገር ግን እስካሁን ራስህ እያሳደድህ ነው፣ እያዋረድህና እየገደልህ ነው፡፡እጆችህን ተመልከት፣ በደም ተጨማልቀዋል!”

ጂትሎቭስኪ እጆቹን አነሣና በተለየ ሁኔታ አተኩሮ አያቸው፤ ከዚያም ወደአባ አርሴኒተመለከተ፡፡ እጆቹን ከጭኑ ላይ አሳረፋቸውና በጣቶቹ ሲጥጥ የሚል ድምፅ በፍጠር “ስለማላውቀውማነኛውም ነገር ለመናገር አትሞክር!” አለና አባ አርሴኒን እንደገና በጥልቀት ተመለከታቸው፡፡ግሪጎሬንኮ ከላይኛው ተደራቢ አልጋ ላይ ሆኖ “አርካዲ ሴሚዮኖቪች፣ ቄሴ በሃይማኖት በዐልየሚያስተምር ሰው ይመስላል፤ ለምን አሁን ገድለን አንገላገልም?” በማለት በብስጭት ተናገረ፡፡

“ዝም በል፣ ግሪንጎሬንኮ!” ሲለው መለሰና ጂትሎቭስኪ “ወደውስጥ ከማስገባታችን በፊትየሚለውን ሁሉ ይበል፡፡ ቄሶች ማነብነብ ሥራቸው ነው፣ ልክ እንደኮሞኒስት ካድሮዎች፣” አለ፡፡

አባ አርሴኒ ቀጠሉ፤ “አንድ ሰው አንድ ቀን አንተን ሃይማኖተኛ ነበረ አለኝ፣ ግን ለምንታምናለህ? ሰዎችን አሰቃይተህ የገደልህ በማን ስም ነው? ስለዶስቶቭስኪ--ስትናገር አስታውሳለሁ፣በጣም የምትወደው ደራሲና የሩስያውያን ነፍስ መሆኑን ተናግረሃል፤ “ዘ-ብራጊስ ካራማዞቭ”በተሰኘው መጽሐፉ የዞሲማን ቃለ-ምክር እጠቅሳለሁ፡፡ ከመሞቻ አልጋዉ ላይ ሆኖ በዙሪያዉከበውት ለነበሩ ሰዎች እንዲህ አለ፤ “ከሀድያንን፣ ክፋት የሚያስተምሩትን፣ ማቴሪያሊስቶችንናክፉዎችንም ሳይቀር አትጥሏቸው፣ ምክንያቱም ከእነርሱ መካከልም ትቂቶቹ በእውነት ርኅሩኆችአሉና፣ በተለይ ደግሞ በዘመናችን፡፡ የእግዚአብሔርን ሰዎች ውደዱ፡፡ እመኑና ታላቅ የእምነት ደረጃይኑራችሁ፡፡ ለሁሉም ሰዎች መልካም ሥሩ፣ ስቃዮቻቸውን በመሸከም ዕርዷቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰውስለሕይወት እንደገና እንዲያስብና ስህተቱንም እንዲያርም ጊዜ አለው፣ ይህን ማድረግም ይገባዋል፡፡ይህን ከተናገሩ በኋላ አባ አርሴኒ ተነስተው ወደአልጋቸው አመሩ፡፡ ነገር ግን ግሪጎሬንኮከአልጋዉ ላይ ዘለለና አባ አርሴኒን አንገታቸውን አነቃቸው፡፡ በዚያ ቅጽበት በተሰበሰቡት ሰዎችመካከል አንድ ረጅምና ጠንካራ ሰውየ እየተጎማለለ ብቅ አለ፣ ይህ ሰው በእስር ቤቱ ውስጥ“መርከበኛዉ” በሚል ስም ይታወቃል፡፡ ኦዴሳ ላይ በፖለቲካ ምክንያት ተይዞ ለአስራ-አምስትዓመታት በዚህ እስር ቤት ውስጥ እንዲቆይ እስከተፈረደበት ጊዜ ድረስ በእርግትም መርከበኛ ነበር፡፡”ግዴለሽ፣ ደስተኛና ጥሩ ጀግና ሰው ነበር፣ እንደማናችንም በእስር ቤት ቢቆይም ጤናማ የሰውነትአቋሙን እንዳለ ነበር፡፡

መርከበኛዉን ከበው የሚመለከቱትን ሰዎች እየገፈተረ መጣና ግሪጎሬንኮን ያለማመንታትአነሣና በዕቃ እንደተሞላ ጆንያ ወደጂትሎቭስኪ ቡድን አባላት ወረወረው፡፡

“ስማ አንተ ምናምን! አሁን ሩስያ ውስጥ እንጂ ጀርመን ውስጥ አለመሆንህን ልታውቅይገባል!” አለና ወደጂትሎቭስኪ ዞሮ ያለማመንታት በኦዴስያኛ የአነጋገር ዘይቤ “የኔ ክቡር ሆይ፣ጓደኞችህን ፀጥ ብታሰኛቸው ይበጃሃል! ያለበለዚያ ማንቁርታችሁን እዘጋዋለሁ፡፡ ሁላችሁም ፀጥበሉ!”

የጂትሎቭስኪ ቡድን አባላት ተንቀጠቀጡ፤ ብዙ እስረኞችም መጡና አባ አርሴኒንናመርከበኛዉን ለማገዝ በተጠንቀቅ ቆሙ፡፡

መርከበኛዉ ወደግሪጎሬንኮ መጣና “ፒዮትር አንድሬየቪችን መንካት አትችልም! አንድ ነገር ቢሆኑእኔ በግሌ ስለእርሳቸው እገድላሃለሁ፣ ከመግደሌ በፊት ስስ ብልትህን መትቼ በመጣልእጫወትብሃለሁ፣” አለው፡፡ ከዚያም አባ አርሴኒን ጠራቸውና “ፒዮትር አንድሬቪች፣ እንሂድ! አሁንአስጨንቀናቸዋል፡፡ ለእርስዎ የተለየ አክብሮት አለኝ፡፡ በሰላም ደግመን እንደምንገናኝ ተስፋአደርጋለሁ፡፡”

በሦስት ሳምንታት ውስጥ ጆራ ግሪጎሬንኮ ወደሌላ እስር ቤት ተዛወረ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮጂትሎቭስኪዎች ፀጥ አሉ፣ ለሰዎችም ከበሬታ ማሳየት ጀመሩ፡፡ ክርክሩ ግን እንደቀጠለ ነበር፣ አባአርሴኒ ግን ከዚያ ጊዜ ጀመሮ በክርክር መሳተፋቸውን አቆሙ፡፡

(1)  ቭላሶቨትስ በጄነራል ቭላሶቭ ስር ይታዘዙ የነበሩ ሩስያውያውን ወታደሮች ሲሆኑ ከውጭ ሆነው ኮሚኒዝምን ለመዋጋትከጀርመን ጦር ሠራዊት ጋር ተቀላቀሉ፡፡ ጦርነቱ በጀርመኖች ተሸናፊነት በመደምደሙ በመጨረሻ በጦር ቃል-ኪዳን ተባባሪሀገራት ወደሩስያ እንዲመለሱ ተደረገና ከሞላ-ጎደል ሁሉም ሲሰቀሉ የቀሩት ደግሞ ወደልዩ የሞት ካምፕ ተላኩ፡፡


(2) ስተራርትስ “ስታሬትዝ” ለሚለው ቃል የብዙ ቁጥር ሲሆን ትርጉሙ ሰዎች ሃይማኖታዊ ምክር ለማግኘት የሚሄዱበትታዋቂ መምህር ማለት ነው፡፡ የኦፕቲና ገዳም እንደነዚህ ዐይነት መምህራንን በማፍራት የታወቀ ነው፡፡ 

No comments:

Post a Comment

ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!