Showing posts with label Ginbot 7. Show all posts
Showing posts with label Ginbot 7. Show all posts

Tuesday, 19 March 2019

የግንቦት ፯፤ አዴፓ እና አብን ግብ የዜግነት ፖለቲካ ነው፤ አሁኑኑ ይተባበሩ

የመጨረሻ ዸቂቃ እየደረሰ ስለሆነ ጸጉር ቅንጠሳችንን ትተን ወደፊት እንራመድ።

የግንቦት ፯፤ አዴፓ እና አብን ግብ ከሞላ ጎደል አንድ ነው። ግንቦት ፯ የዜግነት ፖለቲካን ነው ማስፈን የሚፈልገው። በሌላ ቋንቋ ህገ መንግስቱን ከጎሳ አስተዳደር ወደ ብዝሃነት ያለው የዜጋ አስተዳደር መቀየር ነው።

አዴፓ በይፋ አይናገረው እንጂ ወደ ዜግነት ፖለቲካ ማምራቱ የታወቀ ነው። ህገ መንግስቱ በዚህ መንገድ ይቀየር ቢባል አዴፓ ይደግፈዋል።

አብን ደግሞ አንዳንድ መሪዎቻቸው ምንም ቢደነባበሩ ሁለት አላማ አለኝ ብሎ በይፋ ተናግሯል። እነዚህን ፩) የአማራ ህዝብ ጥቅምን ማስከበር እና ፪) ህገ መንግስቱን ወደ ዜግነት አስተዳደር መቀየር።

ስለዚህ ሶስቱ ድርጅቶች፤ ግንቦት ፯፤ አዴፓ እና አብን፤ የዜግነት ፖለቲካ በኢትዮጵያ እንዲሰፍን ይታገላሉ። ታባባሪ ናቸው እና እንደ ታባባሪ አብረው ሊሰሩ ይገባል።

ግቡ የዜግነት ፖለቲካ ነው። የግቡ ምክንያት የጎሳ ፖለቲካ የግጭት መንስኤ ስለሆነ የባህል ብዝሃነት ያለው የዜግነት ፖለቲካ ብቻ ነው ሰላም የሚያመጣው ነው።

ይህን ግብ ለመምታት ሶስቱ ፓርቲዎች የተለያየ መንገድ ይጠቀሙ ይሆናል። ግን ሶስቱም በአንድ አቅጣጫ እየሄዱ ስለሆነ ከመጠላለፍ ተቆጥበው ወደ መደጋገፍ ሊገቡ ይገባል። ለሶስቱም የሚጠቅም ነገር ነው።

በመቸረሻ ግንቦት ፯ ጠንክሮ ድርሻውን ማሟላት አለበት። አዴፓ ጠንካራ ነው፤ አብን አባላትን በደምብ እየሰበሰበ ነው። ግን ግንቦት ፯ ከብዙሃን ድጋፉ አንጻር ገና ነው። መፍጠን አለበት፤ አማራጭ የለም።

Friday, 19 October 2018

Disarmed! አለች ርዕዮት ዓለሙ

በዛሬ እለታዊ ፕሮግራም የርዕዮት ዓለም አስተያየትን (https://www.youtube.com/watch?v=b1OuvNmwxeY) በተመለከተ...

ነጥቧ ከሞላ ጎደል እንዲህ ነው፤ እነ «ቲም ለማ» ከመጀመርያዉኑ በጭፍን አምነን መከተል («መደገፍ») አልነበረብንም። ለ«ዴሞክራሲ» መታገል መቀጠል ነበረብን እና እነ «ቲም ለማ» እውነትም ዴሞክራቶች ቢሆኑ መሃል መንገድ እንገናኛለን ነው። ዛሬ እነ ጠ/ሚ አብይ አድሎ እያሳዩ እየሆነ የፈራሁት ሁኔታ እየተከሰተ ነው ግን አሁን እኛ ለዴሞክራሲ የምንታገለው ቡድን እራሳችንን "disarm" አድርገናል። በተወሰነ ደረጃ "its' too late" ነው የምትለው።

ምን መሳርያ ኖሮን ነው "disarm" ያረግነው ነው ጥያቄው! እኛ ኢትዮጵያ ብሄርተኞች ከሁሉም ፖለቲካ ኃይሎች የመጨረሻ ደካማ ነበርን ዓመት በፊት ዛሬም እንዲሁ። ምንም "disarm" አላረግንም። ነው ግንቦት 7 ሀገር መግባት አልነበረበትም ወይንም ጥጥቁን መፍታት አልነበረበትም ነው? ዓመት በፊት በኦሮሚያ የነበረው ሁኔታ ይታወቃል። በኦህዴድ ያለው ሁኔታ ይታወቃል። «ጠባቦች» በርካታ ነበሩ አሁንም ናቸው። እንደ አብይ በነሱ ላይም ከነሱ ጋርም ነው የመንግስት ግልበጣ ያደረጉት። እኛ የኢትዮጵያ ብሄርተኞች ኢሚንት ነው ያደረግነው።

ታድያ ዛሬ ጠ/ሚ አቢይ ፈልገውም ባይፈልጉም ኦሮሞ ብሄርተኞቹን ወድያው መቆጣጠር ባይችሉ ምን ይገርማል። የኢትዮጵያ ብሄርተኛው ቡድን ለ50 ዓመት መደራጀት ያልቻለው ዛሬም ስላልቻለ ነው ይህ የሚከሰተው። የአዲስ አበባ ህዝብ ገና ድሮ ቢደራጅ ኖር (ዋጋውን ከፍሎ) ይህ ሁሉ አይሆንም ነበር። ዛሬም ባለፉት ስድስት ወራት መደራጀት ይችል ነበር። አሁንም ይችላል። ላለመቻሉ እነ ጠ/ሚ አቢይን መውቀስ ተገቢ አይደለም። በፍፁም ተገቢ አይደለም። እንደልማዳችን የራሳችንን ችግር ሌላ ላይ እየለጠፍን ነው።

እኛ መጀመርያ ተደራጅተን ታክቲካል አላያንስ ከነ ጠ/ሚ አቢይ ጋር መፍጠር ነው። አሁን ላለውን ችግር እሱ ላይ ከመለጠፍ ፋንታ ስራችንን ሰርተን ብልህ ፖለቲከኞች ሆነን እራሳችንን አጎልብትን መገኘት ነው። ሀውሓት ያደረገው፤ ኦሮሞ ብሄርተኞች ያደረጉትን እኛ ሊያቅተን አይገባም።

ይቅርታ አድርጉልኝ ግን የኛ የኢትዮጵያ ብሄርተኞች ፖለቲካ በመደራጀት ብቻ ሳይሆን በስልትም እጅግ ደካማ ይመስለኛል። የህዝብ/ብዙሃን ቁጥር አለን ግን ድርጅት የለንም። ስለዚህም አቅመ-ቢስ ነን። ልሰዚህ ይህ ጊዜ የማጎልበት ነው እንጂ የጠላት መፍጠር አይደለም!! እነ ጠ/ሚ አቢይን ጓደኛ አድርጎ፤ የጎሳ ብሄርተኞችን ዝም ብሎ፤ ወሬ ሳናበዛ ለመደራጀት እና ለመጎልበት እራሳችንን ጊዜ መስጠት አለብን። ይህ ነው ብቸኛ አማራጭ።

Thursday, 18 October 2018

የአዲስ አበባ ህዝብ መደራጀት፤ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ

ትላንት ሁለት የአዲስ አበባ ሰዎች በማይሆን ክስ ታስረዋል። ከሱም እንደገባኝ ከሆነ ወጣቶችን በ«አዲስ አበባ በከተማው ተወላጅ ነው መመራት ያለበት» መፈክር ዙርያ ማደራጀት ነው። ለዚህም አደረጃጀት ከፍልስቴም ኮንሱሌት ጋር ተባብረዋል ነው ሌላው ክስ። እነዚህ ስራዎች በፍፁም ህገ ወጥ አይደሉም እና መታሰር እንደሌለባቸው ግልጽ ነው። ሆኖም ትላንት እነዚህ እስረኞች በጭለማ ቤት እየተሰቃዩ (torture) ይገኙ ነበር። ዛሬ ደህና ፍርድ ሳያገኙ አይቀርም። መከራ ለነሱ ቢሆንም መሻሻል ነው።

በዚህ ግዳይ በርካቶች አቤቱታ እያቀረቡ ነው። ጥሩ ነው፤ እንደዚህ አይነት የማይሆን እስርን መቃወም አለብን። ግን እንደምናውቀው ፖለቲካችን ከመቃወም ወደ መስራት መሻገር አለበት። Proactive politics beats reactive politics anytime።

መሰራት ያለበት ስልታዊ አደረጃጀት ነው። በመጀመርያ ለምንድነው «ወጣቶችን» የምናደራጀው? ሰራተኛው የት አለ? ወዝ አደሩ የት አለ? የቢሮ ሰራተኛው የት አለ? ወላጆች የት አሉ? ጡረተኞች የት አሉ? መከከለኛ መደቡ የት አለ? ሃብታሙ የት አለ? «የተማረው» የት አለ? ምሁራኑ የት አለ? ልሂቃኑ የት አለ? ለምንድነው «ወጣቱ» (እውነቱን ለመናገር ስራ የሌለው ወጣት) ሸክሙን መሸከም ያለበት?

ይህ «ወጣትን» ማደራጀት ዘላቂነት እንደሌለው ይታወቃል። ሁሉም ህዝብ መሳተፍ አለበት ለእውነተኛ የዜግነት ፖለቲካ ወይንም የሲቪክ አደረጃጀት። ወጣቱ ተሳትፎ ሌላው ከሸሸ ዋጋ የለውም ብቻ ሳይሆን ጎጂም ሊሆን ይችላል። እንደ ሜኪናን በአራተኛ ማርሽ ማስጀመር ማለት ነው።

ሌላው ችግር ገና መደራጀቱ በተገቢው ሁኔታ አይጀምር እራስን ለጥቃት ማጋለጥ ነው። እኔ እንደሚገባኝ የአዲስ አበባ መደራጀት አላማ «የአዲስ አበባ ህዝብ መብቱ እንዲከበር» ነው። ከንቲባው የአዲስ አበባ ትውልድ ይሁን አይሁን አይደለም። የአዲስ አበባ ህዝብ መብት ከተጠበቀ ምርጫ ይኖራል እና ህዝቡ የፈለገውን ይመርጣል። ግቡ እንዲህ ግልጽ ሆኖ ካየነው እና ግቡ ላይ ካተኮርን 1) ስራችንን በትክክሉ እንሰራለን እና ይሳካልናል 2) ለጥቃት እራሳችንን አናጋልጥም!

አካሄዱ እንደሚመስለኝ እንዲህ ነው መሆን ያለበት፤

1) በጣም ሰፊ ተዕልኮ (vision and mission) ያለው ድርጅት ማቋቋም፤ ለምሳሌ «የአዲስ አበባ ህዝብ መብት እና ጥቅም ለማስከበር የሚሰራ» ድርጅት ማለት ነው። ሀ) ሰፊ ተዕልኮ ስለሆነ ለመጠቃት መጋለጡ አነስተኛ ነው የሚሆነው። ለ) ብዙ ሰዎችን በተለይም «መደራጀት» ሲባል የማይገባቸው ወይንም የሚፈሩትን ይጋብዛል። እናቶች፤ ወላጆች፤ መካከለኛ መደቡን። ሃብታሙን ወዘተ ይጋብዛል።

2) ከመፈክር በፊት መደራጀት። መጀመርያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከፋይ አባላት ይኖረው። ከዛ በኋላ ነው መንቀሳቀስ። እንቅስቃሴው ከአቅም ጋር አብሮ መሄድ አለበት! እንቅስቃሴው ከአቅም ጋር አብሮ መሄድ አለበት! አቅም ሳይጎለበት መራመዱ ጥቃትን መጋበዝ ነው። የቅንጅት ታሪክ ይህን ነው የሚያስተምርን። ቅንጅት በመቶ የሚቆጠሩ መሪዎች እና አባላት ነበረው ከዛ ቀጥሎ እስከ ብዙሃኑ ድረስ ከሞላ ጎደል ባዶ መዋቅር ነበር። ጥቂት መሪዎች እና ብዙ ብዙሃን። መሃሉ ባዶ ነው። እነዚህ ጥቂት መሪዎች ሲጠቁ እና እርስ በርስ ሲጣሉ ማን ይተካቸው። መዋቅሩ እስከ ታች ባዶ ነበርና። ስለዚህ መጀመርያ መጠንከር ከዛ ወደ ዋና ስራ መግባት ነው ትክክለኛ አሰራር። ይመስለኛል።

የአዲስ አበባ ህዝብ ወይንም ጠቅላላ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለያየ ወኪላዊ ድርጅቶች መደራጀት አለበት (በዜግነት ፖለቲካ ካመንን)። አለበለዛ ያው የጎሳ ፖለቲካ ማለትም የግጭት ፖለቲካ ነው የሚቀረን። ለሀገራችን ህልውና ቅድመ ሁኔታ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ይህን ዋና ስራ በሙሉ ተሳትፎ በሰከን ያለ ብልጥ መንገድ እንስራው። ህዝብ በሙሉ እንዲሳተፍ እናድርግ።

«እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።»

Monday, 15 October 2018

የአዲስ አበባ ወጣቶቻችን፤ Nameless and faceless

ዛሬ በመሃበራዊ ሚዲያ ለ«ታፈሱት የአዲስ አበባ ወጣቶች» ፍትህ መጠየቂአ ቀን ይመስላል። ጥሩ እቅድ ነው።

ግን ማናቸው እነዚህ «ወጣቶች»? መስላቸው የት አለ? ስማቸውስ? ቤተሰቦቻቸው የት አሉ? ልጆች አላቸው ይሆን? ወላጆቻቸው የት ናቸው? እየተፈለጉ ነው ወይ? ማን ስለነሱ በየቤቱ እያለቀሰ ነው?

እኔ እስከመቀው ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ የለንም። ለምን የለንም? እንዴት በመቶዎች ወይንም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታፍሰው ወደ ወታደራዊ ካምፕ ሲወሰዱ ምስላቸው፤ ስማቸው፤ ቤተሰቦቻቸው አይመዘገቡም? አዲስ አበባ የአምስት ሚሊዮን ህዝብ ከተማ ናት። ልጆቿ እንዲህ አይነት ነገር ሲደርስባት እንዴት ዝርዝሩን አናውቅም? ኤንዴንት ቤተሰቦቻቸው ወይንም ወኪሎቻቸው በተለያየ ሚዲያ ወጥተው እንዲታዩ ወይንም እንዲናገሩ አይደረግም? ለምንድነው faceless ሆነው የሚቀሩት?

ለነዚህ ጥያቄዎች መሰረታዊ ምክንያቱ የአዲስ አበባ እና የኢትዮጵያ ህዝብ እንደዚህ አይነት ጥቃቄዎችንም የሚያስተናግድ እና የሚመልሱ አቅም ያላቸው የፖለቲካ እና ማህበራዊ ተቋሞች ስለሌለው ነው! እነዚህ ወጣቶች ከተታፈሱ በኋላ ሁላቸውም ከነ ምስላቸው፤ ስማቸው እና ቤተሰቦቻቸው ተመዝግበው እንደ አግባቡ በሚድያ መቅረብ ነበረባቸው። ወጣቶቹን የሚመዘግብ፤ ሁኔታቸውን የሚከታተል፤ ሰለነሱ የሚሟገት እና የአዲስ አበባ ህዝብን ሰለ ጉዳያቸው የሚያሳውቅ ድርጅት ሊኖር ይገባ ነበር! የአምስት ሚሊዮን ከተማ ነው፤ ይህ ሊሳነው አይገባም።

ስለዚህ ይህ ነው መሰረታዊ ችግሩ/ችግራችን። አልተደራጀንም። መደራጀት ለህልውናችን ግድ ነው። ይህ መሰረታዊ ችግር ካልተፈታ ህመሞቻችን ይቀጥላሉ! (If we don't address the fundamental cause we'll keep running after the symptoms and never catch up)።

ስለዚህ ጉዳይ ሌላ ነገር ላንሳ። እስቲ ስንቶቻችን ነን የነዚህ ወጣቶችን ቤተሰቦች አይዝዋችሁ እያልን የምንገኘው? የሚያስፈልጋቸው እርዳታ ካለ የምናረግላቸው? ለባለንጀራዬ ካላሰብኩኝ ለምን ሌላው ያስባል ብዬ አስባለሁ። በችግር ጊዜ ካልደረስኩለት ምን አይነት መተማመን እና ትብብር ይኖረናል? ይህ ሌላ መሰረታዊ ችግር ነው። የእርስ በርስ ግንኙነታችን (social capital) መንኗል። ፍትህ እና ሰላም ከፈለግን ይህ መታደስ አለበት።

https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2016/09/blog-post_14.html

https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/09/blog-post_97.html

Sunday, 7 October 2018

የ«ኢትዮጵያዊነት» ጎራው በቂ አለመደራጀቱ ነው የሀገራችን ፖለቲካ መሰረታዊ ችግር!

የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ ገደል የገባው በኃይለ ሥላሴ ዘመን አስፈላጊ ለውጦች ባለመደረጋቸው ማርክሲዝም እና አብዮት በሀገራችን መስፈኑ ነው። በዚህ ሂደት በሀገራዊ ብሄርተኝነት የሚያምነው የፖለቲካ ልሂቃን ተከፋፍለው እና እርስ በርስ ተፋጀተው የሀገራችን ፖለቲካ በጎሳ ብሄርተኞች እንዲወረር ተው።

ይህ የፈጠረው ሁኔታ ይህ ነው፤ የጎሳ ብሄርተኝነትን የሚከተለው ብዙሃን በፖለቲካ ድርጅት፤ ኃይል እና ልሂቃን ደረጃ በአግባቡ ተወክሏል። በአንጻሩ በኢትዮጵያ ብሄርተኝነት የሚያምነው ብዙሃን አልተወከለም ማለት ይቻላል። ከ100 ሚሊዮን ህዝብ ቢያንስ ግማሹ ጠንካራ ኢትዮጵያ ብሄርተኛ ነው። ግን ይህ ግዙፍ የሆነው ህዝብ ብዛቱ የሚገባው ድርጅት የለውም። ግንቦት 7 ነው ያለው አቅሙ ግን የ50 ሚሊዮን ህዝብ የሚወክል ድርጅት ያህል አይደለም። ቅርቡም አይደለም።

ይህ ነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዋና እና መሰረታዊ ችግር። በታም ግዙፍ የሆነ የብዙሃኑ ክፍል የልሂቃን፤ ምሁራን፤ እና የፖለቲካ መደብ ውክልና የለውም። ይህ የተዛባ (distorted) ሁኔታ ፖለቲከኞቻችን የተዛባ ውሳኔዎች እንዲወስዱ ያደርጋል እና ሀገሪቷን ግጭት በግጭት የደርጋል።

አልፎ ተርፎ በአግባቡ ያልተወከለ ግዙፍ ብዙሃን አንድ ቀን ይፈነዳልና ወደ አብዮት ያመራል። የአማራ ብሄርተኝነት ማደግ ይህን ያመለክታል። በዜግነት መደራጀት ስላቃተን በጎሳ እንደራጅ ነው የአማራ ብሄርተኝነት መሰረታዊ ግፊቱ። ይህ ሁኔታ በዚ አቅጣጫ ከቀጠለ ምሃል ሀገሩ (centre) ባዶ ቀርቶ የፖለቲካ ኃይል በሙሉ ከጠረፎቹ (periphery) ይሆናል። ይህ ደግሞ እንደምናውቀው የጎሳ ውድድር፤ ከዛ ግጭት፤ ከዛ ጦርነት ያመጣል። ለዚህ የ27 ዓመት መረጃ አለን።

ስለዚህ የፖለቲካችን ችግር ለመፈታት ዘንድ የኢትዮጵያ ብሀኢርተኝነት ጎራው በአግባቡ መደራጀት ግድ ነው። ቅድመ ሁኔታ (necessary precondition) ነው። በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠረው የኢትዮጵያ ብሄርተኛ ብዙሃኑ ቁጥሩን የሚመጥን ፖለቲካዊ ውክልና ያስፈልገዋል። የመሃል እና ጠረፍ (centre and periphery) ሚዛን መስተካከል አለበት። ይህ ከሆነ የፖለቲካ መደቡ በእውነታ የተመሰረተ ድርድር ማድረግ ይችላል። ሁሉም ህዝብ በተወከለበት ማለት ነው።

ይህን ነጥብ እንዴት አጠንክሬ ማስደምደም እንደምችል አላውቅም! የኢትዮጵያዊነት ጎራው በአግባቡ አለመደራጀቱ ነው እስካሁን ያለውን የፖለቲካ ችግር የሚቀጥለው። ካሁን በኋላም ካልተደራጀ ፖለቲካችን ወደ ቀውስ እና ሁከት መሄዱ አይቀርም።

Thursday, 27 September 2018

ተጨማሪ ሃሳቦች ለግንቦት 7 የህዝብ ግንኙነት ስራ

1. በተቻለ ቁጥር በየቀኑ ወይም ቢያንስ በየ ሁለት ቀኑ ቃሚ  አውንታዊ መልዕክቶች (አጭር ድርጅታዊ መግለጫዎች) ወደ መገናኛ ብዙሃን አስተላልፉ። እነዚህ መግለጫዎች ስለ ግንቦት 7 ስራ፤ አባል ምልመላ፤ ስብሰባ፤ ስለ ወቅታዊ ሁኔታ፤ ትምርታዊ ስለ ግብረ ገብ እና ስነ መግባር፤ ስለ ፖለቲካ፤ ወዘተ ሊሆን ይችላል። ግን ህዝቡ ከግንቦት 7 ማለትም ከ«ኢትዮጵያዊነት» ድርጅት አውንታዊ መልዕክቶች መስማት ይልመድ።

2. ለተለያዩ የግጭት ሰለቦችን በተልትይም በተለምዶ የሚከሰቱት የጎሳ ግጭት ሰለቦች እርዳታ ማሰባሰብ። በቀላሉ ግሎባል አላያንስ የሚያደርገውን ስፖንሶር ማድረግ ነው። ይህ የኢትዮጵያዊነት ስሜትን በትክክሉ ያንጸባርቃል። አውንታዊነትንም ያንጸባርቃል።

Tuesday, 25 September 2018

ግንቦት 7 የህዝብ ግንኙነቱን ያጎልብት

ግንቦት 7 የ«ኢትዮጵያዊ ብሀርተኝነት» ዋናው (እክካሁን) የፖለቲካ ድርጅት በመሆኑ ለሀገራችን ህልውና ታላቅ ሚና መጫወት ይኖርበታል። ግን የሚገባውን ሚና ለመጫወት አንድ አንድ ድክመቶቹን ማስተካከል ይኖርበታል።

በሰሞኑ የእውን (real)፤ የዜና እና ማህበራዊ ሚዲያ ግርግር የግንብቶ 7 የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ድክመቶች ጎልተው የታዩ ይመስለኛል። ድክመቶቹ፤

1. ምንም መልዕክት አያስተላልፍም
2. መልዕክቶች ካስተላለፈም ከተለያዩ ሰዎች ዥንጉርጉር የሆኑ መልዕክቶች ናቸው
3. የሚመጡት መልዕክቶች የድርጅቱን አላማ የሚያደናቅፉ ናቸው
4. አጄንዳ መሪ ከመሆን አጄንዳ ተከታይ ይመስላል (instead of setting the agenda, always in reaction mode)

1. በአሁኑ ዘመን ማንኛውም የለህዝብ አስተያየት የሚያገባው ተቋም ለህዝብ መልዕክቶች ቶሎ ብሎ ማሰራጨት አለበት። በኦነግ አቀባበል ግርግር፤ በቡራዩ ክስተት፤ በአዲስ አበባው የህዝብ አፈሳ ወዘተ ግንቦት 7 በፍጥነት አጫጭር የሆኑ የድርጅቱን አስተያየት እና ግብ የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ነበረበት ግን አላደረገም። ባለማድረጉ ህዝብ ለመረጃ ወደ ሌሎች ምንጮች እንዲሄድ አድርጓል። ሌሎች ደግሞ በደስታ የማይሆን ፕሮፓጋንዳ ለህዝቡ ያንሰራጫሉ። ይህ ለግንቦት 7 አደጋ ነው።

2. ግንቦት 7 የሚያንስተላለፉት መልዕክቶች ደግሞ የተለያዩ ናቸው። ለምሳሌ እኔ ያነበብቋቸው ከአንዳርጋቸው ጽጌ እና ከነአምን ዘለቀ ትንሽ ተመሳሳይ የሆኑ አለ። ግን ደግሞ ሙሉነህ እዮኤል ስለ ስልክ ጠለፋ የሚያተኩር መልዕክት አስተላለፈ። አንድ official መልዕክት ሊኖር ይገባ ነበር ከዛ ሌሎቹ ያንን ቴማ የሚከተሉ መሆን ነበረበት። ለምሳሌ ዋና ቴማ «ስራችንን በደምብ እየሰራን ነው ተረጋግቶ ስራችንን መቀጠል ነው» ከሆነ ሁሉም መልዕክቶች ይህንን ማንጸባረቅ አለባቸው።

3. የሙሉነህ እዮኤል መልዕክት ጥሩ ነገሩ የድርጅቱ አመራር የተሰሩትን የግንቦት 7 አባላትን ጠየቁ የሚለው ነው። ግን ስለ ስልክ ጠለፋ ያስተላለፈው መልዕክት ከግንቦት 7 አላማ ተጻራሪ ይመስለኛል። አሁን የግንቦት 7 ዋና ስራ አቅም ግንባታ (capacity building) የሆነ ይመስለኛል። ድጋፍ፤ አባላት፤ ገንዘብ እና የሰው አቅም ማጎልበት ነው። ለዚህ ደግሞ ሰውዉ እንዲረጋጋ እና ፖለቲካውን እንዳይፈራ ማድረግ ያስፈልጋል። ሁሉን የጊዜያዊ ክስተቶች (short term events) በቀላሉ እንደወሰዱ እና ከዋና አላማ እንዳያዘናጉ ማድረግ ነው ያለበት። ለምሳሌ ስለ ስልክ ጠለፋ፤ መንግስት ስልክን እንደሚጠልፍ የታወቀ ነው። በተለይም የተቃዋሚ ስልኮችን። ግንቦት 7 ሀገር ውስጥ ሲገባ ይህንን ጠንቅቆ ያውቃል። ገና በርካታ የነባር ኃይል ደጋፊዎች አሉ በመንግስቱ። እነሱም አዲሶቹም ለድህንነት እና ፖለቲካቸው የስልክ ጠለፋን ይፈልጉታል። ስለዚህ የተቃዋሚ ስልክ ተጠለፈ ብሎ መአስደንገጥ አያስፈልግም። ይህ ህዝብን ያስፈራራል መፍራቱ ደግሞ ከግንቦት 7 ፍላጎት የሚጻረር ነው። ግንቦት 7 ከሁሉም ነገር በላይ ዛሬ ህዝቡ ፖለቲካን እንዳይፈራ እና ከሱ ስር እንዲሳተፍ ነው የሚፈልገው። «የሁሉም ስልክ ይጠለፋል እንኳን የነኦነግ ስልክም ተጠለፈ» ማለት ነው። አሁን ወደ ስራችን እንመለስ ነው።

4. ምንም አዲስ ወይንም አስደናቂ ዜና ባይኖርም ግንቦት 7 በየቀኑ የሚዲያ አጄንዳ የሚመራ መልዕክት ማስተላለፍ አለበት። በተለይም ስለ ሰላም፤ ፍቅር፤ መደራጀት፤ ስብሰባ፤ አቅም ግንባታ ወዘተ። እንደዚህ አይነት አካሄድ ግንቦት 7 በህዝቡ እምኔታ እንዲያገኝ ይረደዋል (it breeds familiarity and trust)። ይህ ደግሞ አባላት እና አቅም ለመሰብሰብ አስፈላጊ ነው።