Showing posts with label ADP. Show all posts
Showing posts with label ADP. Show all posts

Tuesday, 19 March 2019

የግንቦት ፯፤ አዴፓ እና አብን ግብ የዜግነት ፖለቲካ ነው፤ አሁኑኑ ይተባበሩ

የመጨረሻ ዸቂቃ እየደረሰ ስለሆነ ጸጉር ቅንጠሳችንን ትተን ወደፊት እንራመድ።

የግንቦት ፯፤ አዴፓ እና አብን ግብ ከሞላ ጎደል አንድ ነው። ግንቦት ፯ የዜግነት ፖለቲካን ነው ማስፈን የሚፈልገው። በሌላ ቋንቋ ህገ መንግስቱን ከጎሳ አስተዳደር ወደ ብዝሃነት ያለው የዜጋ አስተዳደር መቀየር ነው።

አዴፓ በይፋ አይናገረው እንጂ ወደ ዜግነት ፖለቲካ ማምራቱ የታወቀ ነው። ህገ መንግስቱ በዚህ መንገድ ይቀየር ቢባል አዴፓ ይደግፈዋል።

አብን ደግሞ አንዳንድ መሪዎቻቸው ምንም ቢደነባበሩ ሁለት አላማ አለኝ ብሎ በይፋ ተናግሯል። እነዚህን ፩) የአማራ ህዝብ ጥቅምን ማስከበር እና ፪) ህገ መንግስቱን ወደ ዜግነት አስተዳደር መቀየር።

ስለዚህ ሶስቱ ድርጅቶች፤ ግንቦት ፯፤ አዴፓ እና አብን፤ የዜግነት ፖለቲካ በኢትዮጵያ እንዲሰፍን ይታገላሉ። ታባባሪ ናቸው እና እንደ ታባባሪ አብረው ሊሰሩ ይገባል።

ግቡ የዜግነት ፖለቲካ ነው። የግቡ ምክንያት የጎሳ ፖለቲካ የግጭት መንስኤ ስለሆነ የባህል ብዝሃነት ያለው የዜግነት ፖለቲካ ብቻ ነው ሰላም የሚያመጣው ነው።

ይህን ግብ ለመምታት ሶስቱ ፓርቲዎች የተለያየ መንገድ ይጠቀሙ ይሆናል። ግን ሶስቱም በአንድ አቅጣጫ እየሄዱ ስለሆነ ከመጠላለፍ ተቆጥበው ወደ መደጋገፍ ሊገቡ ይገባል። ለሶስቱም የሚጠቅም ነገር ነው።

በመቸረሻ ግንቦት ፯ ጠንክሮ ድርሻውን ማሟላት አለበት። አዴፓ ጠንካራ ነው፤ አብን አባላትን በደምብ እየሰበሰበ ነው። ግን ግንቦት ፯ ከብዙሃን ድጋፉ አንጻር ገና ነው። መፍጠን አለበት፤ አማራጭ የለም።

ብራቮ ለአዴፓ፤ ከ600 ሚሊዮን በላይ ብር ለተፋናቃይዎች በመሰብሰቡ

እንኳን ደስ አለን። ብራቮ አዴፓ! ብራቮ ለጋሾች! ትብብርን እና ድርጅትን ማጠንከር እንዲህ ነው።

ለጋሾች ግን በዚህ አታቁሙ። አዴፓ ግዴታውን እንዲወጣ ተከታተሉ። ካልተወጣው ደግመን አንሰጥም ብላችሁ አሳስቡ።

አዴፓ ይህን እንደ ጅምር እንጂ እንደ ግብ አትመለከቱ። ስራችሁን በአግባብ ሰርታችሁ ይበልጥ የሆነን መዋቅር እና አቅም ገንቡ!

ግንቦት 7 እና ሌሎች የኢትዮጵያ ብሄርተኞች እና የአዲስ አበባ መሃበራት፤ ከዚህ ድል ተማሩ። እንደዚህ አይነት አስፈላጊ ስራ መስራት ከባድ አይደለም! ይቻላል! እኛም እንደዚህ አድርግን ግዙፍ የአንድነት ድርጅታችንን እናቋቁም። አሁን ምንም መዘግየት አይቻልም። ለ40 ዓመታት በመዘግየታችን ሀገራችንን እጅግ ጎድተናል። አሁኑኑ በአስቸቋይ የግዙፍ ድርጅት ምስረታ ስራችንን ጀምረን እናጠናቅቅ።

Monday, 10 December 2018

አዴፓ እና የመሬት ይዞታ ፖሊሲ


አቶ ንጉሱ ጥላሁን በዚህ ቃለምልልስ ዛሬ ያለው የመሬት ፖሊሲ አንዱ «ምሶሶአችን» ነው ብለዋል።

ይህን እሳቸውም ድርጅታቸውም ሌሎች አቋሞቻቸውን እንደፈተሹት እንዲፈትሹ እጠይቃለሁ። መሬት የግል ይሁን ይሉ አልልም የፖለቲካ ሁኔታው ለዛ አይነት ድምዳሜ ዛሬ የሚመች አይሆንምና። ግን አቋሙ ምሶሶ ነው አይበሉ። እየፈተሹት እየተዉት ይሄዱ።

የአማራ ገበሬ እራሱን ማሻሻል ያልቻለው እና ዝቅተኛ እስረኛ ሆኖ የቀረው ከጎረቤቱ መሬት ገዝቶ መስፋፋት እና በራሱ ላይ ኢንቬስት ማረግ ባለመቻሉ ነው። በተጨማሪ መሬት የመንግስት ይሁን የሚለው ፖሊሲ ጸንፈኛ የሆነ ዓለም ዙርያ ከአንድ ሁለት ሀገር በቀር የማይታይ ፖሊሲ ነው። አዴፓ ለዘብ ያለውን መካከለኛ መንገድ በዚህም ጉዳይ እንዲከተል እጠይቃለሁ።

https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/03/blog-post_47.html

https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/10/blog-post_94.html