Tuesday 19 March 2019

የግንቦት ፯፤ አዴፓ እና አብን ግብ የዜግነት ፖለቲካ ነው፤ አሁኑኑ ይተባበሩ

የመጨረሻ ዸቂቃ እየደረሰ ስለሆነ ጸጉር ቅንጠሳችንን ትተን ወደፊት እንራመድ።

የግንቦት ፯፤ አዴፓ እና አብን ግብ ከሞላ ጎደል አንድ ነው። ግንቦት ፯ የዜግነት ፖለቲካን ነው ማስፈን የሚፈልገው። በሌላ ቋንቋ ህገ መንግስቱን ከጎሳ አስተዳደር ወደ ብዝሃነት ያለው የዜጋ አስተዳደር መቀየር ነው።

አዴፓ በይፋ አይናገረው እንጂ ወደ ዜግነት ፖለቲካ ማምራቱ የታወቀ ነው። ህገ መንግስቱ በዚህ መንገድ ይቀየር ቢባል አዴፓ ይደግፈዋል።

አብን ደግሞ አንዳንድ መሪዎቻቸው ምንም ቢደነባበሩ ሁለት አላማ አለኝ ብሎ በይፋ ተናግሯል። እነዚህን ፩) የአማራ ህዝብ ጥቅምን ማስከበር እና ፪) ህገ መንግስቱን ወደ ዜግነት አስተዳደር መቀየር።

ስለዚህ ሶስቱ ድርጅቶች፤ ግንቦት ፯፤ አዴፓ እና አብን፤ የዜግነት ፖለቲካ በኢትዮጵያ እንዲሰፍን ይታገላሉ። ታባባሪ ናቸው እና እንደ ታባባሪ አብረው ሊሰሩ ይገባል።

ግቡ የዜግነት ፖለቲካ ነው። የግቡ ምክንያት የጎሳ ፖለቲካ የግጭት መንስኤ ስለሆነ የባህል ብዝሃነት ያለው የዜግነት ፖለቲካ ብቻ ነው ሰላም የሚያመጣው ነው።

ይህን ግብ ለመምታት ሶስቱ ፓርቲዎች የተለያየ መንገድ ይጠቀሙ ይሆናል። ግን ሶስቱም በአንድ አቅጣጫ እየሄዱ ስለሆነ ከመጠላለፍ ተቆጥበው ወደ መደጋገፍ ሊገቡ ይገባል። ለሶስቱም የሚጠቅም ነገር ነው።

በመቸረሻ ግንቦት ፯ ጠንክሮ ድርሻውን ማሟላት አለበት። አዴፓ ጠንካራ ነው፤ አብን አባላትን በደምብ እየሰበሰበ ነው። ግን ግንቦት ፯ ከብዙሃን ድጋፉ አንጻር ገና ነው። መፍጠን አለበት፤ አማራጭ የለም።

No comments:

Post a Comment

ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!