እንደሚታወቀው መሬትን የግል ማድረግ ኤኮኖሚውን ይረዳል። አሁን ደግሞ በመጠኑ የኤኮኖሚ አጣብቅኝ ውስጥ ነን። ዛሬ መሬት የግል ቢሆን መቼ እና ምን ያህል ነው ኤኮኖሚው ላይ ውጤቱ የሚታየው?
መሬት የግል ማድረግ የፖለቲካ ችግር እንዳለው ይታወቃል ስለዚህም ዛሬ priority አይደለም። ሆኖም እንደ አማራ ክልል አይነቱ ዳር ዳሩን እያለ እንደሆነ ይታወቃል። ለምሳሌ የ25 ዓመት ኪራይ (ሊስ) በህግ እንዲስተናገድ አድርጓል። ይህን የ25 ዓመት ኪራይ ወደ 1000 ዓመት ድርስ እንዲፈቀድ ቢደረግ እና ቂራዩን መሸጥ መለወጥ ቢፈቀድ de facto መሬትን የግል አደረገ ማለት ነው። ይህ በአማራ ክልል ወይንም ማንኛውም ይህን አለ ብዙ ፖለቲካዊ ችግር ማድረግ የሚችል ችግር ምን ያሀል የኤኮኖሚ ጥቅም በቅርቡ ሊያመጣለት ይችላል?
አዲስ አበባ እንዲሁ መሬት ከግለሰብ ለ1000 ዓመት መከራየት ይቻላል ኪራዩም መሸጥ መለወጥ ይቻላል ቢባል ምን ያህል ይሆን ጥቅሙ? በመፈናቀል እና መጠቀም ያለው ሚና እሳ?
No comments:
Post a Comment
ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!