Tuesday, 12 March 2019

«ዓቢይ ከዳን» የሚለው ትርከት ይጠቅመናል ወይ?

የኢሳት ተንታኞች ኤርሚያስ ለገሰ እና ሃብታሙ አያሌው አቢይ እየዋሸላቸው ኦዴፓ የክህደት ስራ ሰሩ የሚል ትርክት ጀምረዋል። ይህ ትርክት ለኢትዮጵያዊነት ኃይሉ እና ለአዲስ አበባ ህዝብ ትግል ይጠቅማል ዋይ ነው ጥያቄው?

እንደሚገባኝ ይህ ትርክት ሁለት አላማ አለው፤

፩) የአዲስ አበባ ህዝብ እና ሌላው የኢትዮጵያዊነት ጎራውን ለማስነሳት
፪) የዓቢይ መንግስት (እና ለማ እና ኦዴፓ) ላይ ጫና መፍጠር

እስቲ «ዓቢይ ከዳን» የሚለው ትርከት እነዚህን ግቦች ሊያሳካ ይችላል ወይ ብለን እንመልከት...

፩) «ጠላቶችን» በኃይል በመተቸት ህዝቡን ማነቃቃት እና ማስነሳት ኢሳት እና ሌሎች ለረዥም ዓመታት የሞከርነው ስልት ነው። አልሰራም ነው የምለው። የፖለቲካ ለውጡ የመጣው ህዝቡ የትግሬ የበላይነት እና የህወሓት ጭቆና ስለበቃው ነው። የበቃው ደግሞ «እየተቆንክ ነው» ስለተባለ አይደለም፤ የለት ኑሮው ስለሆነ ነው። ይህ የሚያሳየን የ«ለቅሶ ፖለቲካ» ማለትም ጨቋኝን መተቸት እና ስለ ጨቋኝ ማልቀስ ህዝቡን አያስነሳም። ስለዚህ አሁንም «አቢይ ከዳን» ማለት ህዝቡን አያስነሳም። ህዝቡ አሁን የሚያስፈልገው ጠላት አይደለም፤ ጠላቱን ያውቃል።

፪) የዓቢይ መንግስት ይህን አይነት ጫና አይመልስም። መንግስቱ/ኦዴፓ ጸንፈኞቹን የሚያስተናግደው አምኖበት ነው፤ ተገዶ ነው፤ ወይንም የረዥም እቅድ ስልት ይህን የወረ ጫና ምንም አይቀይረውም። በጸንፈኝነቱ አምኖበት ከሆነ ከኃይል በቀር ምንም አይመልሰውም። ተገዶ ከሆነ አሁንም ኃይል ነው አስገድዶ የሚመልሰው። ስልት ከሆነ ደግሞ አሁንም የኛን ጫና ignore ማድረግ ግድ ይሆንበታል ግቡ እስኪሳካ።

ሰልዚህ «ዓቢይ ከዳን» የሚለው ትርክት ግቦቹን አያሟላም። እርግት ለስሜታዊ ጩኸት እና እሮሮ ይመጫል። ግን ሰከን ብለን ካሰብነው ጥቅም የለውም።

አልፎ ተርፎ ጉዳት አለው። እንደተለመደው ገመደራጀት ስራችን distract ያደርገናል። ለ27 ዓመት እየጮህን ችግራችንን ህወሓት ላይ እያሳበብን መደራጀት አልቻልንም። እነ ዓቢይ መጥተው ህወሓትን አባረሩልን። አሁንም የመደራጀት አለምቻል በሽታችን ላይ ከማተኮር ፋንታ የ«አቢይ ከዳን» ትርክት ላይ ካተኮርን የትም እንቀራለን።

ሌላው ጉዳት ለፖለቲካዊ የዋህነት/ጅልነት እጃችንን መስጠት እና ትክክለኛ ግንዛቤ ማጣት ነው። የዓቢይ መንግስት የህወሓትን አገዛዝ ለመድገም ነው ከመጀመርያ የተነሳው ማለት እጅግ የተንሸዋረረ አመለካከት ነው። ፖለቲካ የalliance ጉዳይ ነው። ከማን ጋር ነው የምንጋራው እና ጥቅማችን የሚመሳሰለው የሚለውን ነገር አብጥረን ማወቅ አለብን። እና ዓቢይን ከነ ኦነግ ጋር መቀላቀል አደገኛ የዋህነት ነው።

ስለዚህ ሰከን እንበል። ይህ ሁሉ ችግር የመታው ባለመደራጀታችን ነው። የአንድ ዓመት እድል አልፎናል። እስካሁን የኢትዮጵያዊነት ኃይሉ እና/ወይንም የአዲስ አበባ ህዝብ 100 ሚሊዮን ብር በጄት ያለው እና ሚሊዮን አባል ያለው ድርጅት መፍጠር ነበረበት። የፓርቲ አባላትን አሰልጥኖ ቢያንስ አዲስ አበባን በአንድ ለአምስት መቆጣጠር ነበረበት። በየመዋቅሩ ሰው ነአ ድር መዘርጋት ነበረበት። ይህን ሁሉ አላደርገንም። ባልማረጋችን ነው ችግሮች የቀጠሉት። አሁንም «ዓቢይ ከዳን» ብለን ማልቀስ ይህንን ግብ አያመጣም። ዋና ግባችን ላይ ብናተኩር ይሻላል።

No comments:

Post a Comment

ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!