Friday 15 March 2019

ለዘብተኛ ብሄርተኞቹን ወደኛ ማምጣት ግድ ነው

በጎሳ ብሄርተኝነት ችግር ያለበት የትም ሀገር የ«አንድነት» ኃይሉ ዋና ስልት (ስትራቴጂ) ለዘብተኛ የጎሳ ብሄርተኞጭኝ ወደሱ ማምጣት። በአንጻሩ ለዘብተኞቹ የጸንፈኞቹን ፕሮፓጋንዳ ተቀብለው ወደ ጸንፈኛው ወገን እንዳይሄዱ ነው። ይህን በዚህ ጽሁፍ (https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/07/understanding-ethnic-soft-nationalism.html) በሌሎች ሀገር ምሳሌ እየሰጠሁኝ አስረድችያለሁ።

ባጭሩ ለልምንድነው ለዘብተኞቹን መሳብ የሚያስፈልገው? አንድ ጎሳ ሙሉ በሙሉ ጸንፈኛ ብሄርተኛ ከሆነ ልታሸንፈው አትፈልግም ይዞህ ገደል መግባት ስለሆነ የፖለቲካ መንገዱ። ግን ግማሹን (ግማሽ ናቸው እንበል ለዘብተኞቹ) ካሳመንክ የጽንፈኞቹ ኃይል እና ማምጣት የሚችሉት ሀገራዊ ጉዳት እጅግ ይመነምናል። ይህ ከሞላ ጎደል basic ፖለቲካ ነው ዓለም ዙርያ።

ይህን ከተቀበልን በኋላ እንዴት ነው ለዘብተኞቹን ወደ አንድነት መሳብ የሚቻለው ብለን እንጠይቅ። ያው አንዱ መንገድ ፍላጎታቸውን በማሟላት ነው። ለምሳሌ ኦሮምኛ የፌደራል መንግስት ቋንቋ ይህን ስንል ይህ የለዘብተኛ የኦሮሞ ብሄርተኛን ትቅም እና ፍላጎት ለማሟላት ነው። ነገሩ ደግሞ ለሁሉም ጠቃሚ ነውና ሁሉም (ከጸንፈኞቹ በቀር) ተጠቃሚ ይሆናል። ይህ ለለዘብተኞች ፍላጎት መቆርቆር አንድ ስልት ነው።

ከስልት ሌላ ግን ወደ ታክቲክ ስንገባ ለዘብተኞች ወደ ጸንፈኝነት እንዳይሄዱ ማድረግያ አንዱ ዋና ታክቲክ ለዘብተኛ ውይይት ነው። ኃይለ ቃል፤ ዘለፋ፤ ስድብ ወዘተን ከንግግራችን እጅግ ማራቅ ነው።

ጸንፈኞቹ እንድንሳደብ እና ኃይለ ቃል እንድንጠቀም እጅግ ይፈልጋሉ! እጅግ እጅግ ይፈልጋሉ! ከአንድነት ኃይሉ እንደዚህ አይነት ንግግር ከመጣ ለዘብተኞች ተበሳጭተው ወደ ጽንፈኛው ጎራ እንደሚወስዳቸው ጽንፈኞቹ አበጥረው ያውቃሉ። ከላይ በጠቀስኩት ጽሁፌ እንደ ምሳሌ እንደሰጠሁት በካናዳ የቄቤክ ብሄርተኞች ከአንድነት ፖለቲከኛ ስድብ እና ዘለፋ ጓግተው ይጠብቁ ነበር። አንዱ ተሳስቶ ኃይለ ቃል ከተናገረ ደግሞ ወድያው ሚዲያውን ይሞሉበት ነበር! እንዲህ ነው የአንድነት እና ሀጎሳ ብሄርተኝነት የፖለቲካ ጨዋታ።

ለዚህ ነው ከላይ በምታዳምጡት የታማኝ በየነ ቃለ ምልልስ ታማኝ መጮህ እና መተቸት ቀላል ነው ግን አደጋ ነው የሚለው። በደምብ ባይገልጸውም ሃሳቡ ይህ ነው።

በሌላ በርዕዮት ዓለም ፖለቲካ መሰዳደብ እና መወንጀል አለ። አንዳንዴ መስደብ እና ማዋረድ ስለሚያዋጣ ነው የሚያደርጉት። መራጮች ስድቡን እና ትችቱን ተከትለው አምነው ሰዳቢውን ወገን ይመርጣሉ። ሆኖም ግን አንዳንዴ አድግራጊውን ጎድጦ ይሸነፋል። ግን ከዚህ አያልፍም።

ጎሰኝነት ያለው ፖለቲካ ግን የተለየ ነው። በጎሳ ፖለቲካ ኃይለ ቃል እና ስድብ ሰውን ከማሳመን ይልቅ ይገፈትራል! ኢሳት ለ24 ሰአት (ተገቢም ቢሆን) ስለ ኦሮሞ ብሄርተኞች ጽንፈኝነት ከተናገረ ማንንም ኦሮሞ ወደሱ አያመጣም፤ ችግራሽ ይገፈትራቸዋል። የጎሰኝነት ፖለቲካ ባህሪ እንዲህ ነው። ኃይለ ቃል ጸንፈኞቹን ነው የሚጠቅመው። ለዘብተኛ ንግግር ይጎዳቸዋል።

አላማችን ለዘብተኞቹን ወደኛ ለማምጣት ከሆነ ይህን ትጠንቅቀን ማወቅ አለብን። በንግግር በላቸው የሚለው አስተሳሰብ የተሳሳተ ነው። ፖለቲካን አለማወቅ ነው። የሚቀጥለው ጊዜ እንደ ግንቦት 7 አይነቶቹ ለምን «አልቾሃችሁም» ከማለት ይህን አስታውሱ።

No comments:

Post a Comment

ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!