Friday, 13 July 2018

በረከት ስምዖን ይዙር!

በረከት ስምዖን አማራ ክልልን እየዞረ ገንዘብ እያደለም ድጋፍ እየሰበሰበ ነው ይባላል? ታድያ ምን አለ ይህን ቢአደርግ። ምንድነው የምንፈራ። ሰዎቻችንን ይገዛል ብለን ነው? ያሳምናል ብለን ነው?

በረከት በገንዘብ እና ሀሳብ የራሳችንን ሰዎች ከገዛ ካሳመነ ይህ ስለኛ ምን ይነግረናል። ምን አይነት ህዝብ ነን ማለት ነው? በገንዘብ እና ውሸት የምንገዛ ህዝብ ነን? እንዲህ ከሆነ ደግሞ መሰረታዊ እና መታረም ያለው ችግር የበረከት መዞር ነው ወይንም የኛ በገንዘብ እና በ ውሸት መገዛት ነው? 

ግልጽ ነው፤ ችግሩ እኛ ነን መፍትሄው እራሳችንን ማስተካከል ነው። አለበለዛ የኛ ህዝብ በገንዘብ እና ውሸት ሀሳብ ስለሚገዛ በረከትን እናባረው ከሆነ መሰረታዊ ችግራችንን አንፈታም። በርከት ቢጠፋ ሌላ ደግሞ ይመጣል። ሌላ ተቃዋሚ፤ ሌላ የ«አማራ ጠላት»፤ ሌላ ሽብርተኛ ወዘተ። የራሳችንን ችግር ካልፈታን ለአደጋ እና ክህደት ሁልጊዜ የተጋለጥን እንሆናለው። ልድገመው፤ የራሳችንን ችግር ካልፈታን ለአደጋ እና ክህደት ሁልጊዜ የተጋለጥን እንሆናለው።

ለኔ ስለ በረከት ዙረት መቸገር እጅግ እጅግ አሳፋሪ ነው። አንድ ህዝብ የማይወደው አማራ ነኝ ኤርትራዊ እየዞራ ሊበጠብጣችን ይችላል ማለት እኛ እጅግ ደካማ እና ቀሽም ነን ማለት ነው። ባሁኑ ጊዜ ያውም ሰፃነት የሰፈነበት በረከት ምንም ጡንቻ የሌለበት እንዴት ነው የምንፈራው? ያስንቃል። 

ወንድሞች እህቶች እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ያስንቃል። ያስንቃል። እንደዚህ ነው እነ ህወሓትን ያሞላቀቅናቸው። ትንሽ ሆነው በቀላሉ ሊገዙን እንደሚችሉ ያመኑት ገና አንዳቸውን ስናይ ሊበጠብጠን ነው ብለን ስንሸማቀቅ ሲያዩ ነው። ይህን ውሸት ማድረግ አለብን። በረከት ስምዖን እየዞረ ሰውን እያሳመነ ከሆነ እኛ ያን ሰው አንዳያምን ማድረግ አለብን። የክህደት መንፈስ፤ የመታለል መንፈስ፤ የመገዛት መንፈስ ከኛ እንዲጠፋ ማድረግ አለብን።

ድሮ ኩሩ ህዝቦች ነበርን። አንድ ሽፍታ ያጠፋናል ብለን አንፈራም ነበር። በራሳችን በራሳችን ህዝብ እንኮራ እንተማመን ነበር። አንድ ወቅት ግን እርስ በርስ መፈጃጀት ስንጀምር በራሳችን መተማመኑን ያቆምን ይመስለኛል። ከዛ ወዲህ በአንድ ክፍል ውስጥ 100 ሆነን ተግኝነት አንድ «ጠላት» ከመጣ ያንን አንድ ጠላት እንደ 100 ሃይል መፍራት ጀመርን። ይህን አስተሳሰብ ካልቀየርን ኢትዮጵያም አማራም አዲዮስ። በተዘዋዋሪ ለዚህ ነው እነ ሻ'ዕብያ እና ወያኔ አንዳችን የ10 አማራ ዋጋ አለው የሚሉት። ትንሽ ሆነን እናሸማቅቃቸዋለን የሚሉት።

ስለዚህ በረከት ስምዖን ይዙር። ከተማ ለከተማ ይዙር ጉቦ ይስጥ ወሬውን ያውራ። መብቱ ነው። እኛ ለህልውናችን ግዴታ የሆነውን ራሳችንን እናስተካክል እናስተምር አንድነት እናምጣ። ልድገመው፤ አንድነት እናምጣ። አንድ ከሆንን እንደ ብረከት አይነቱ 10,000 ሆነውም እየዞሩ ጉቦዋቸውን ቢያድሉ ዋጋ አይኖረውም። ይህ አይነት አንድነት ከሌለን ለዘላለም በቀላሉ የምንሸነፍ ሰዎች ነው የምንሆነው።

Thursday, 12 July 2018

የቤት ሰራተኛ

አንድ ጓደኛዬ «የቤት ሰራተኛዬን እንደ ቤተሰብ ነው የምቆጥራት። ካስፈለገ እንጀራ መጋገርም ቤት ማጽዳትም እረዳታለሁ። ግዴታ ትምሕርትቤት እንድትማር አደርጋታለሁ…» ብሎ ነገረኝ። ምን ነው ይህ ያልተለመደ እንክብካቤ ብዬ ስጠይቀው እንዴት ለልጆቼ እንጀራ ጋግራ የምታበላውን አልንከባከባትም አለኝ! እውነት ነው፤ ሌሎቻችን እንዲሁ ቢገባን።

አንድ ሰሞን የቤት ሰራተኛ ፍለጋ አዲስ አበባን ከደላላ ወደ ደላላ ዚርን! ደላሎቹ ምን እንርዳችሁ ብለው በጉጉት ይጠይቁናል። የቤት ሰራተኛ ስንላቸው ፈገግራቸው የጠፋል። ሹፌር ወይንም የቀን ሰራተኛ ወዛደር ብንላቸው ይሻላቸው ነበር ብዙ አላቸው። ግን የቤት ሰራተኛ የላቸውም፤ ለነሱም ብርቅ ሆነዋል።

ብዙ የማቃቸው ቤተሰቦች አዲስ አበባም ከገጠር ከተሞችም የቤት ሰራተኞቻቸው በየ ሁለት ሶስት ወር ይለቃሉ አዲስ መቅጠር ይሆንባቸዋል። ወይንም ለመቅተር የገንዘብ አቅም የላቸውም። ወይንም ከመቀቃየር ተስፋ ቆርጠው አለ ሰራተኛ ይኖራሉ።

ዛሬ በአዲስ አበባም በመላው ኢትዮጵያ የቤት ሰራተኛ ጠፍቷል። ወይንም በትክክለኛ አገላለጽ (እጅግ) ተወዷል። ለምን ይሆን? የ ኤኮኖሜ ምክንያቶች አሉ። የሰው ኃይል በጠቅላላው ተወዷል። ዛሬ የቀን የግንባታ ሰራተኛ በወር ወደ 3000 ብር ሊሰራ ይችላል። እንዲሁም የቤት ሰራተኛ ደሞዝ ጨምሯል። ሁለተኛ ምክንያት ዛሬ ሴት ልጆች ከድሮ ይልቅ በትምሕርታቸው ይገፋሉ። የገጠር ወይንም የድሃ ቤተሰብ ልጆቻችው እንዲማሩ ይፈልጋሉ እንጂ በልጅነታቸው ሰራተኛ እንዲሆኑ አይሰጧቸውም። ሶስተኛ ምክንያት ወደ አረብ ሀገር ሄዶ መስራት ነው። የአራብ ሀገር ክፍያ ይበልጣል ወደ «ውጭ» ሀገር መሄድም ምንም ችግር እንደሆነ መረጃ ቢኖርም ያጓጓል ይመስለኛል። በነዚህ ምክንያቶች የቤት ሰራተኞች ተወደዋልም አይገኙምም።

ከኤኮኖሚ ምክንያቶች በተጨማሪ ለቤት ሰራተኛ መጥፋት ማህበረሰባዊ ምክንያር አለ እና እዚህ ላይ ነው ማተኮር የምፈልገው። ዛሬ አንድ ሴት በህንጻ ጽዳት ስራ 2000 ብር በ ወር ታገኛለች። ከዚህ ብር የቤት ኪራይ፤ መጓጓዣ (ትራንስፖርት) እና የምግብ ወጪዎቿን ትከፍላለች። 1000 ከተረፋት ትልቅ ነገር ነው። ነይ በ2000 ብር የቤት ሰራተኛ ሁኚ የቤት ኪራይ፤ የመጓጓዣ እና የምግብ ወጪ አይኖርሽም ብንላት እምቢ ትላለች። ለምን ይሆን? ስራው ከባድ ስለሆነ አይደለም  እትፍ ከባድ አይደለም። ነፃነቱ ይሆን እሱም 1000 ብር የሚያዋጣት አይመስለኝም። ምንም አይነት የሚመች የስራ ሁኔታዎች ብትዋዋልም የቤት ሰራተኛ መሆን አትፈልግም። ታድያ ምንድነው ምክንያቱ?

እኔ እንደሚመስለኝ ዋናው ምክንያት በባህላችን የቤት ሰራተኝነት እንደ ዝቅተኛ የሚናቅ ስራ ስለምንቆጥረው ነው። ይህን የዝቅተኝነት እና የመንናቅ ስሜት እጅግ ብዙ ብር ካልሆነ ብር አይተካውም። ተጎድቼ ውጭ ብሰራ ይሻለኛል ለብዙ ብር ከሰው ቤት ከምሰራ ነው ያለን አስተሳሰብ።

እስቲ ወደ ኋላ ሄደን የቤት ሰራተኞቻችንን እንዴት እንደምንይዝ እንደነበር እናስታውስ። 16 ሰዓት በቀን ይሰራሉ ለሌላው 8 ሰዓት ተጠሪ ናቸው። በወር አንድ ቀን እረፍት ቢኖራቸው ነው ይህም ላይከበር ይችላል። ኦርቶዶክስ ክርስትያን ነን የምንለው እንኳን እሁድ ቀን እረፍት መስጠት ቅዳሴም እንዲያስቀድሱ አንፈቅም (ከዚህ በላይ አሳዛኝ ነገር አላቅም)። እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ባርያ እንጮህባቸዋለን እናጎሳቁላቸዋለን። እንደማንም ሰው አድገው ወደፊት ማግባት እና ቤተሰብ ማፍራት እንደሚፈልጉም አንገነዘብም ልንገነዘብም አንፈልግም። ከቤተሰቦቻቸው ርቀው በመኖራቸው እኛ እንደ ሁለተኛ ቤተሰባቸው መሆን እንዳለብን አናስብም። በጠቅላላ ለራሳችን የማንወደውን እናደርግባችዋለን ለራሳችን የምንወደውን አናደርግላቸውም።

ይህ ስር የሰደደ ባህል ሆኖ የቤት ሰራተኛ እጅግ ዝቅተኛ ስራ መሆኑ ሁላችንም አሰሪዎችም ሰራተኞችም እናውቃለን። በዚህ ምክንያት ይመስለኛል በርካታ ሴቶች ከቤት ሰራተኛ ስራ የሚርቁት። ብዙ ብር ቢከፈላቸውም ከገንዘብ አንጻር ቢያዋጣቸውም «ዝቅተኛነቱን» «ውርደቱን» አይፈልጉትም።

የቶሎ የስራ መቀያየር ጉዳይሳ? ለምንድነው ብዙ የዘመኑ የቤት ሰራተኛዎች ገና ወር ሁለት ወር ሳይቆዩ ለቀው ወደ ሌላ ቤት የሚሄዱት። አንዱ ምክንያት የኤኮኖሚው ነው። ብዙ ስራ ስላለ የደሞዝ ጭማሬ ቶሎቶሎ ያገኛሉ። ሌላው ምክንያት ግን እንደሚመስለኝ የቤት ሰራተኝነት የማይፈለግ ስራ በመሆኑ ብዙ ችግር እና የማመዛዘን ድክመት ያላቸውን ሴቶች ናቸው ወደዚህ ስራ የሚገቡት። ይህ ምክንያት የስራ መቀያየራቸውን ብቻ ሳይሆን ሌሊችን ችግሮች እንደ ሌብነት ወዘተ ያስረዳል።

ለረዥም ዘመን የቤት ሰራተኞቻችንን ጎድተናል። በተዟዟሪ ሙሉ መሃበረሰባችንን ጎድተናል። የጎጂ የአሰሪ እና የንቀት ባህላችን ከትውልድ ወደትውልድ አስተላልፈናል። የአሁኑ የሰራተኛ እጥረት እስኩመጣ ድረስ ጥፋቶቻችን አልታዩንም ይሆናል ግን አሁን ጎልተው ሊታየን ይገባል። ጥፋታችንን አይተን አምነን መጸጸት፤ ንስሃ መግባት እና ይቅርታ መጠየቅ የሚኖርብን ይመስለኛል ይህን ጎጂ ባህላችንን በቋሚነት ለማስወገድ። ይህ ለህላችንም ለጠቅላላ ህብረተሰባችን ሰላም እና ፍቅርም አስፈላጊ ይመስለኛል።

Wednesday, 11 July 2018

Towards an Integrated Ethiopia

Decades ago we used to be presented with a stark choice between a "unitary" state speaking Amharic, assimilating all other ethnic groups, and with nearly everything controlled by the central government, and approximately 85 separate nations, one for each of our ethnic groups! And unfortunately all debate revolved around these caricatures, and we never got anywhere.

Today, thankfully things have changed. We have, fortunately or unfortunately, data from 27 years of the radical experiment called ethnic federalism, where as much as was realistically possible, regions were drawn along ethnic lines and ethnicity ("nations, nationalities, and peoples") became the foundation of the Ethiopian state. I would say that these 27 years have shown us conclusively that this formula is one of ethnic strife, conflict, war, ethnic competition, ethnic-motivated mass dislocations, etc.

Some would say that what we have had is fake or bastardized ethnic federalism in which the TPLF ruled as a dictatorship and never really implemented the constitution in practice. This is certainly true to some extent, but enough was implemented to see the results. Ethnic based regions were created, ethnic based identity cards were encouraged in many regions, and there was some degree of self rule in the regions. Moreover, most of the ethnic conflicts throughout Ethiopia have not been related to TPLF dominance. Instead, they have been occurring between non-Tigrean ethnic groups. Take for example Amharas and other "non-locals" being evicted from various regions, or being hunted down and murdered in the name of retribution for historical injustices. Or conflicts between Gedeo and Guji, or Oromo and Somali, or Qemant and Amhara, or Agew and Amhara, etc. There are plenty of examples. It is clear that the placement of ethnicity at the centre of political life resulted in conflict and ethnic political competition, which is always a recipe for disaster. Despite the fact that the ethnic federalism experiment was not perfectly tried out, we have seen enough to know that it cannot work for Ethiopia.

As I say this, I have to add that the even EPRDF itself recognized a couple of years ago that this was the case. The main catalyst for this recognition was that the ethnic hatred inculcated by ethnic federalism started to target Tigreans more and more. The combination of ethnic federalism and the EPRDF's beloved developmental state was proving untenable. The public's resentment against the ruling class, as represented by the EPRDF, was not only based on politics and class, but on ethnicity - on anti-Tigrean sentiment. The resentment became virulent, and the EPRDF knew that things could not continue as is without full blown ethnic war. Hence the beginning of the opening of the EPRDF, and in particular the TPLF, to changes that eventually brought about Prime Minister Abiy Ahmed and his team to power.

So I think today it is clear that the ethnic federalism formula as we have it, even if implemented 'perfectly', is not a good solution for Ethiopia because it brings about conflict. Not because it is inherently unjust, but because we have evidence that it does not work and it results in concrete strife and misery. Why has it not worked? A few reasons... First, there is in many parts of Ethiopia ethnic resentment and historical baggage. Ethnic-based governance only exacerbates this. Second, a significant portion of our incapable political elite wish to use ethnic competition as a way to political power and have no qualms about encouraging ethnic conflict. Third, there has been over hundreds or thousands of years significant integration and even assimilation in Ethiopia, resulting in a large constituency not interested in ethnicity, but nevertheless persecuted by ethnic politics for historical grievance reasons and for not signing on to the ethnic ideology. For these and other reasons, and given the evidence we have, the current ethnic federalism formula should, in time, be abandoned.

Abandoned for what? For many of us, the choice today is between 1) an integrated and synthesized Ethiopianism or 2) an Ethiopia divided on ethnic lines - a nation of disparate nations. 2) is more or less what we have now, the recipe for ethnic strife and conflict. The first choice is, I think, our only choice. What is integrated and synthesized? It means reflecting as much is realistically possible and in keeping with the wants of the population everyone's identity in Ethiopianness. An obvious and often stated example of this: making the Oromo language a national language of Ethiopia, in addition to the current Amharic, integrates into Ethiopianness the use of the Oromo language. It moves it from the periphery, or from a single region, to the national level. Another example: integrating elements of the Gadaa political structure into the nation's political structure. And so on. What about other ethnic groups and their identities? What about the level of regional and local autonomy? These and several other questions can be answered via discussion and evolution. But the point is that integration and unity is the only way to peace and prosperity. A single Ethiopian identity must be cultivated, not to the exclusion of ethnic identity, but to ensure that it always supersedes ethnic identity, thereby reducing the temptation of ethnic politics and ethnic conflict.

What about the transition from ethnic based politics to this new "Ethiopian" politics? It should probably be slow since we have a generation schooled under the ERPDF's ethnic politics and we have a perhaps worse older political class schooled under Marxism and democratic socialism. The first step is to implement integrative policies such as the language policy I mentioned above. One of the goals of this policy is to increase inter-ethnic integration and increase the non-ethnicized population. After some years (or decades) of this, the proportion of non-ethnicized Ethiopians will be such that a transition to non-ethnic politics will be easy.

That is the plan. There are two hindrances that I see. First, the obvious, are the ideological and cynical ethnic politicians who would stand to lose from an abandonment of ethnic federalism. The second is the group against ethnic politics but which does not have the political savvy and empathy needed to relate to and hold discussions with ethnic federalists. The ethnic politicians we will always have with us - I don't think there is anything we can do but marginalize them. But the second group we should work on as if this group - I call it the Ethiopianist group - gets its act together, then we will have a smooth transition from today's combustible ethnic federalism to an integrated and synthesized Ethiopia.

ንቀት

እኛ ኢትዮጵያዊዎች እንደ መንናቅ የምንጠላው ነገር የለም። ከአንዳንድ ቦታዎች ንቀት እና የተደጋገመ ዝልፍያ እስከ መገዳደል ያደርሳል! መንናቅ እየጠላን ግን መናቅን እንወዳለን  አያስችለንም። ይህ ነውረኛ የንቀት ባህላችን ለበርካታ ሀገራዊ፤ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮቻችን  አስተዋጾ አድርጓል። በቀላሉ ለመከፋፈል አጋልጦናል። እርስ በርስ መናናቅን ብናቆም እነዚህ ችግሮችን ለመፍታት ይረዳናል።

«ንቅት» ስል ሰውን ወይንም ማህበረሰብን ወደ ታች አድርጎ ማየት ማለቴ ነው። «ምቀኝነት» ሌላውን በመጉዳት ራስን መጥቀም የሚቻል እንደሚመስለው ንቀትም ሌላውን ወደታች በማየት ራስን ከፍ ማድረግ ይቻላል የሚል የውሸት አስተሳሰብ አለው።

ማንን ነው የምንንቀው? ከኛ «ዝቅተኛ» ስራ የሚሰሩትን፤ (ለምሳሌ) የቤት ሰራተኞቻችንን፤ ከኛ ድሃ የሆኑትን፤ ያነሰ ትምሕርት ያላቸውን፤ አማርኛ በደምብ የማይችሉትን፤ እንግሊዘኛ በደምብ የማይችሉትን!፤ ገጠሬዎትን፤ ቀጥቃጭ፤ ቆዳ ፋቂዎች ወዘተ የሆኑትን፤ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ወዘተ። ዝርዝሩ ረዥም ነው!

ተናቅን የሚል ስሜት ያላቸው ከሚንቋቸው ጋር አንድነት ሳይሆን ልዩነት ይሰማቸዋል። ልዩነት ብቻ ሳይሆን ቂም እና ጥላቻ አከማችተዋል የናቋቸውን ቢበቀሉ ደስ ይላቸዋል። ይህ ማለት ህብረተሰባችን ተከፋፍሏል ነው። እርስ በርስ ጥላቻ አለው ማለት ነው። ታድያ ለረዥም ዓመታት በከፋፍሎ መገዛት ፖለቲካ ብንመራ ለምን ይገርማል። በ«ብሶት ፖለቲካ» መቆየታችን ለምን ይገርመናል? ፖለቲካችን በመጣላት የተመረዘ መሆኑን ምን ይገርማል? የፖለቲካ ውይይቶቻችን በጥይትነና በጡንቻ መካሄዳቸውን ምን ይገርማል?

እስቲ አንዳንድ ተጨባጭ የንቀት ምሳሌዎች ልስጣችሁ፤ በኃይለ ሥላሴ ዘመን ሁላችንም እንደምናውቀው ከመሳፍንቱ እና ባላባቱ መካከል ብዙዎቻችን ገበሬውን፤ ጪሰኞውን፤ ሰራተኞቻችንን ወዘተ እንንቅ ነበር እንደ በታቾቻችን እናያቸው ነበር። አዲሱ «የተማረው» መደብም ራሱ የሚንቀው ቡድን ነበር ይህም ያልተማረውን፤ ሃይማኖታዊውን ወዘተ። ይህ ንቀት ህዝባችንን ከፋፈለ የአንድነት ስሜታችንን ቀነሰ። ሀገራችንን ለኮምዩኒዝም የሚያስተምረው «ጨቋኝ ተጨቋኝ» የክፍፍል ፖለቲካ አጋለጠ። መናናቃችን ለደርግ አብዮት ታላቅ አስተዋጾ አደረገ። አብዮተኞቹ የህዝቡን የመንናቅ ብሶትን እንደ ቤንዚን ተጠቅመው ነው አብዮቱን ያራመዱት። ወዛደሮችን፤ አርሶአደሮችን፤ ሴቶችን፤ «ጭቁን ዘሮችን» ወዘተ እረደሃለሁ እበቀልሃለሁ ብለው ነው ኮምዩኒስቶቻችን የተነሱት። ተናቅን የሚሉትን በሙሉ አቅፍያለሁ እያለ ነው ደርግ የሰበከው። ግን ንቀቱ ባይኖር ብሶቱም አይኖርም ነበር አብዮቱም አይነሳም ነበር።

የኢህአዴግ ዘመንም እንዲሁ ምሳሌ ይሆነናል። ኢህአዴግ ስልጣን ስይዝ የሚናናቅ የተከፋፈለ እርስ በርስ ቂም የያዘ ህብረተሰብ ነው የጠበቀው! ይህን ህብረተሰብ ከፋፍሎ መግዛት እንደሚችል ቶሎ ተረዳ። ልክ እንደ ደርግ ግን በተሻለ ብልጠት ተንቀናል ሊሉ የሚችሉትን ቡድኖች ማፈላለግ እና ማቀፍ ጀመረ! እዚህ ላይ አንድ አስፈላጊ ነጥብ አለ። ኢህአዴግ የተጠቀመበት ክፍፍል አይነት የጎሳን ብቻ አይደለም። ሁሉንም ከላይ የጠቀስቋቸው ክፍፍሎችን፤ ሃብታም እና ድሃ፤ የተማረ ያልተማረ፤ ገበሬ ከተሜ፤ አሰሪ ሰራተኛ፤ ወንድ ሴት፤ ትልቅ ሰው ወጣት ወዘተ ተጥቅሞባቸዋል። እነዚህ ክፍፍሎች አልፈጠራቸውም ተተቀመባቸው እና አስፋፋቸው እንጂ። ስለዚህ ለኢህአዴግም አገዛዝ የንቀት ባህላችን ሙና እንደተጫዋወተ ግልጽ ነው።

ለማጠቃለል ያህል ያለፉት 60 ዓመት ፖለቲካችንን «የብሶት ፖለቲካ» ብለን መሰየም እንችላለን። ቂም እና መከፋፈል የሰፈነበት ፖለቲካ ነው። በ«ጨቋኝ ተጨቋኝ» አስተሳሰብ ተመርዟል። ስለዚህም ነው አብሮ አለመስራት፤ ውግያ፤ ጸብ፤ ቅራኔ አለመፍታት ወዘተ የሰፈነው። ንቀት እና ውጤቶቹ ብሶት እና ቂም ለዚህ ማህበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ ችግር ትልቅ ሚና የተጫወቱ ይመስለኛል።

ከ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ዋና መፈክሮች አንድነትን ወይንም አለመከፋፈል ነው። አንድ የሆነ ማህበረሰብ ጤነኛ ነው የተከፋፈለ ማህበረሰብ በሽተኛ ነው። የሚናናቅ ማህበረሰብ አንድ ሊሆን አይችልም ስለዚህም ይህ የ«ንቀት» ባህላችንን እንዋጋ እና እናሸንፍ!

አንድ የመጨረሳ ነጥብ ፍቀዱልኝ። ንቀት «አንተ የማትወደውን ለባለእንጀራህ አታድርግ» ስለሚሽር መጥፎ ስነ መግባር መሆኑ ሁላችንም ይገባናል። መንናቅ ስለማንፈልግ መናቅ የለብንም ነው። ግን ይህ ሙሉው ታሪክ አይደለም። ንቀት ኢተፈጥሮ ነው። የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አምሳል ስለተፈጠረ ሰውን መናቅ ማለት የሚወደን ፈጣሪአችን እግዚአብሔርን መናቅ ነው። እንደዚህ ስንመለከተው ንቀት እጅግ ከባድ ማጣት ነው።

Tuesday, 10 July 2018

የብሄር ጥያቄ ዛሬ

ዛሬ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ ተገለባብጦ ቢሆንም አሁንም «የብሄር ብሄረሰብ ጥያቄ» ዋና ጉዳያችን ነው። በዚህ ዙርያ ያሉት ጥያቄዎች ናቸው ዋና የሀገራችን የክፍፍል እና የግጭት ምንጭ። ይህ አሳዛኝ ሁኔታ በዋናነት የተፈጠረው በጎሳ ብሄርተኞች ሚና ሳይሆን በሀገር ብሄርተኛ ጎራው ነው። እኛ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ብሄርተኞች ደጋግመን በሰራናቸው ስህተቶች እና ሀገራችንን በሚገባው ማስተዳደእር ስላልቻልን ነው የብሄር ጥያቄው እንደዚህ የሰፈነው። ለምሳሌ ያህል ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በማያሻማ አገላለጽ አስቀምጠውታል፤ ኢህአዴግ ደርግን አላሸነፍም፤ ደርግ እራሱን አሸነፈ እንጂ። እኛ የሀገር ብሄርተኞች አድሃሪ፤ ተራማጅ፤ ኢህአፓ፤ ምኤሶን ወዘተ እየተባባልን አሳፋሪው ደርግን ፈጠርን ደርግ ሀገሪቷን አጥፍቶ ለኢህአዴግ፤ ኦነግ እና ሻዕብያ ስልጣን አስረከበ።

ለምንድነው ይህ ነጥብ ላይ የማተኩረው? ለምንድነው ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮች እንደ ኢህአዴግ አይነቱ የጎሳ ብሄርተኞችን ጥፋተኛ ከማድረግ የአንድነቱን ጎራ የሀገር ብሄርተኞችን ጥፋተኛ የማደርገው?

1. ሁለት አይነት ሰዎች አሉ። አንዱ ችግር ሲደርስበት ማንነው ይህን ያመጣብኝ ብሎ የሚአማርር
ሌላውን አድራጊ እራሱን ሰለባ በማድረግ እራሱን አቅሜ ቢስ ያደርጋል። ሌላው ሰው ምን አድርጌ ነው ይህ የደረሰብኝ ብሎ እራሱን በመገምገም እና ሃላፊነት በመውሰድ እራሱን አቅም እንዲኖረው ችግሩን መፍታት እንዲችል የሚያደርግ ነው። እኔ በአንድነት የማምን የሀገር ብሄርትኛ ነኝ እና ጥፋቴን ማምን ሃላፊነቴን መቀበል እፈልጋለሁ። ጣቴን በሌሎች ላይ በማተቆር የራሴን ጥፋቶች መካድ አልፈልግም። በተጨማሪ ሃላፊነት በመውሰዴ የችግሩ ምንጭ እኔ ነኝ በማለት የመፍትሄው ምንጭም እኔው ነኝ ማለት ነው። መፍትሄውን ከሌላ ሰው አልጠብቅም። ይህ ተመልካች ሳይሆን አስፈጻሚ ያደርገኛል። ይህ አቅሜን ከመመንመን ያጎለብተዋል።

2. እውነት ነው፤ እኛ የሀገር ብሄርተኞች ነን የኢትጵያ የፖለቲካዊ ችግሮች ያመጣነው። በጃንሆይ አገዛዝ ሀገሪቷን በተቆጣጠርን ጊዜ አስፈላጊ ለውጦች ባለማድረግ የመደብ እና የጎሳ ጥያቄዎችን አስነሳን። የሀገሩን ትውፊት የሚንቅ የተማሪ እንቅስቃሴን ወለድን። ደርግ የኃይለ ሥላሴን መንግስት አልገለበጠም የኃይለ ሥላሴ መንግስት ነው አስፈላጊ ለውጦች ባለማድረግ እራሱን ለአብዮት ያጋለተው። አብዮቱን የአንድነት ጎራውን ለሁለት ለ«አድሃሪ» እና «ተራማጅ» ከፋፈከው ተራማጁ አድሃሪውን አጠፋ። ከዛ ደግሞ ተራማጆቹ እርስ በርስ ተጨራረሱ። አልፎ ተርፎ ደርግ በ«ኢትዮጵያ ብሄርተኝነት» ስም «ነግዶ» ህዝብን ጭቆነ እና ለሀገር ብሄርተኝነት መጥፎ ስም ሰጠ። ይህ መጥፎ ስም የጎሳ ብሄርተኞችን እንቅስቃሴን አበረታታ። ደርግ ሲወድቅ የሀገር ብሄርተኝነት ጎራ እራሱን አጥፍቶ አልቋል። የጎሳ ብሄርተኞቹ ሙሉ በሙሉ ስልጣን ተቆጣጠሩ። በኃይለ ሥላሴ ምንም አቅም ያልነበርው የጎሳ ብሄርትኝነት አሁን ሀገራችንን ገዝቶ ኤርትራን አስገነጠለ። ይህ በአጭሩ እኛ የሀገር ብሄርተኞች ዛሬ ያለብንን የጎሰኝነት ችግር እንዴት እንዳመጣን ይገልጻል።

3. አሁንም ዋናው የሚያሳስበኝ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጎራ የሀገር ብሄርተኛው ነው። በህዝብ ደረጃ ይህ ጎራ ቢንገዳገድም ደህና ነው። እንደ አብይ አህመድ አይነቱን መሪዎች እየወለደ ነው። ገን በልሂቃን (elite) ደረጃ ችግር እንዳለ ነው። አንድ ሆነን ሀገራችንን ማዳን እንችላለን ወይንም እንዳለፉት 50 ዓመት እርስ በርስ ተከፋፍለን እንደገና የጎሳ ብሄርተኝነት እንዲሰፍን እናደርጋለን? ዋና ጥያቄ ነው። የቅርብ ታሪካችን ጥሩ አይደለም። ይሄው ለኢህአዴግ የ27 ዓመት አገዛዝ አንድ ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅት ሀገር ውስጥም ውጭም ማቋቋም አልቻልንም። አሁንስ አንድ ሆነን ከ«ለማ ቡድን» ጋር እየሰራን ሀገራችንን ማዳን እንችላከን? ወይንስ እንደልማዳችን እንከፋፈላለን እና ሀገራችንን ለቀውስ እና ግጭት የሚፈጥረው ጎሰኝነት እንደገና አሳልፈን እንሰአለን? ቁም ነገር ከማድረግ አቅሙ አለን ትያቄ የለውም። ግን ፍላጎቱ አለን ወይ ነው ጥያቄው።

በነዚህ ምክንያቶች ነው በዚህ ወቅት ከሁሉም የፖለቲካ ጎራዎች የሀገር ብሄርተኛ ጎራው የሚያሳስበኝ። እንደ ህወሓት ምናልባትም ኦፌኮ አይነቱ የጎሳ ብሄርተኞች ምንም አያሳስቡኝም። የታወቁ ናቸው በልመና ልንቀይራቸው አንችልም። በስልት፤ በዘዴ እና በውይይት ከነሱ ጋር እንደራደራለን። ግን ለመደራደር እና ውጤታማ ለመሆን የአንድነት ጎራው አንድ እና ጠንካራ መሆን አለበት። ድርድር የሚሳካው እራስን መጀመርያ እራስን ጎልብቶ ነው አለበለዛ ደካማ ከሆንን አይሳካልንም። እርግጠኛ ነኝ የአንድነት ጎራው አንደና ተንካራ ከሆንን በነዚህ ድርድሮች እርግጥ ውጤታማ እንሆናለን የጎሳ ብሄርተኞችን በጥሩ መልክ እንይዛቸዋለን። ግን ከተከፋፈልን የበፊቱ 60 ዓመት ችግሮችን እንቀጥላለን።

Monday, 9 July 2018

«ይቅር እንባባል»

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ የእውንተኛ የይቅርታ ሰባኪ መሆናቸውን ሁላችንንም አይተናል። ለበደሉንን ሁሉ ይቅርታ በማድረግ በሰላም እና ፍቅር አብረን መኖር እንደምንችልም እንዳለብንም እያሳመኑን ነው። በዚህ ምክንያት ፖሊሱን፤ መርማሪውን፤ ፍርድ ቤቱን፤ ካድሬውን፤ ሰአላዩን፤ ጎረቤቴን፤ ወያኔን፤ ኦነግን፤ ሻዕብያን፤ ነፍጠኛውን፤ ጠባቡን ወዘተ በደሉን የምንለውን ሁሉ ይቅር ለማለት እራሳችንን እያሳመንን ነው። የበደሉን የመሰለንን ይቅር እንድንል በማሳመናቸው ጠ/ሚ አብይ ታላቅ ስራ ነው የሰሩት።

ሆኖም ጠ/ሚ አብይ እኮ ማንንም ይቅር አላሉም። ይቅርታ ነው የጠየቁት! ንስሃ ነው የገቡት! እባካችሁን እንደ መንግስት ላደረግነው እንደ መንግስት አካል ላደረግኹት ይቅር በሉን በሉኝ ነው ያሉት። ከይቅር ማለት አልፎ ይህንን ንስሃ መግባት እና ይቅርታን መጠየቅን ነው በመጀመርያ ደረጃ ከአብይ አህመድ መማር ያለብን!

ንስሃ መግባት እና ይቅርታ መጠየቅ ለሁላችንም የሰው ልጅ እጅግ ከባድ ነገር ነው። የማንፈልገው የምንሸሸው ነገር ነው። ጥፋታችንን ማመን ቁስላችንን በተለይም ህፈራትችንን በደምብ እንድንመለከት ስለሚያደርገን አንፈልገውም። ግን ለጤናማ እና እውነተኛ ኑሮ ግድ ነው። 

አንዳንዶቻችሁ እንደ አንድ ግለሰብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዙርያ ምን ኃጢአት አለብኝ ትሉ ይሆናል። 
ጥሩ ጥያቄ ነው። ብዙ ጊዜ የኛ «ትናንሽ» ኃጢአቶች ታላቅ ጉዳት እንደሚፈጽሙ አይታየንም እንደናየውም አንፈልግም። ስለዚህም አንዳንዴ ንስሃ ለመግባት እና ይቅርታ ለመጠየቅ ትንሽ ግፊት ያስፈልጋል። እስቲ እኔ ልሞክር። የአብይ አህመድን ምሳሌ ተከትዬ እስቲ እንደ አንድ በአንድነት የሚያምን የኢትዮጵያ ብሄርተኛ ንሰሃ ልግባ ለነዚህ የፖለቲካ ኃጢአቶቼ ይቅርታ ልጠይቅ፤

1. በጃንሆይ ዘመን ልጆቼን ወደ ውጭ ሀገር ትምሕርትቤት ልኬ እራሳቸውን እንዲንቁ የምዕራባዊ አስተሳሰብ ከነ ኮምዩኒዝም ይዘው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እና እንዲበጠብጡ በማድርጌ ይቅር በሉኝ

2. ልጆቼን እትዮጵያዊ እንዲሆኑ ፈንታ ታሪካቸውን እንዳያውቁ ፈረንጅ እንዲያመልኩ የራሳቸውን ወግ እና ትውፊት እንዲጠሉ በማድረጌ ይቅርታ

3. አለአግባብ የወረስኩትን መሬት ለጪሰኞች መልሼ በሚቀረኝ (ሰፊ) መሬት ተደላድዬ ከመኖር በመስገበገቤ ይቅርታ

4. ሰራተኛዬን፤ ጎረቤቴን፤ እንደኔ ያህል ያልተማረውን፤ «ያልሰለጠነውን»፤ ገበሬውን ወዘተ ስለ ናቅኩኝ ይቅር በሉኝ

5. የፖለቲካ ለውጥ በጊዜው ባለማምጣቴ አቢዮትን እና የሁከት እና ግድያ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ለተጫወትኩት ሚና ይቅርታ

6. አድሃሪ፤ ኢህአፓ፤ መኢሶን፤ ደርግ፤ ሻዕብያ፤ ወያኔ ወዘተ እያልኩኝ «ግደሏቸው» በማለቴ ይቅርታ

7. ከሰው ልጅ ይልቅ የፖለቲካ ጦርነት ይበልጣል እያልኩኝ በጦርነት የሚሞቱትን እንደ ምንም ባለመቁጠሬ ታላቅ ይቅርታ

8. ሻዕብያ፤ ወያኔ እና ኦነግ ስልጣን ሲይዙ ወደ ስልጣን የገቡበት ምክንያት በኔ ጥፋት ባዶ የፖለቲካ ሜዳ ስላገኙ ነው ብዬ ባለማመኔ ይቅርታ

9. ኢትዮጵያን በሽብር፤ በጦርነት እና መጥፎ አስተዳደር እጅግ የማይመች ሀገር እንድትሆን  በማድረጌ የኤርትራ ህዝብን ወደ መገንጠል በመገፋፋቴ ይቅርታ አድርጉልኝ

10. ለትግራይ ህዝብ እንዲሁም ፖለቲካውን በአግባብ ማስተናገድ ባለመቻሌ ወደ ትውፊትና ሃይማኖታችሁን የሚጠላው ህወሓት እንድትሸገሸጉ በማድረጌ ይቅርታ

11. ለ27 ዓመት ለችግራችን ያለኝን አስተዋጾ በመካድ ለመፍትሄው ያለኝን ሃላፊነት በመካድ ቁም ነገር ሳላደርግ ለሁሉ ችግሬ እንደህጻን «ወያኔ ነው» ብዬ በማልቀሴ ይቅርታ

ይህን የንስሃ መግባት እና ይቅርታን መጠየቅንም አንብባችሁ እኔ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዙርያ ምንም ይቅርታ የምልበት ነገር የለም የምትሉ ትኖራላችሁ። ከጎረ ቤቱ ጋር የተጣላ በተዟዋሪ የፖለቲካ ኃጢአት ፈጽሟል ማለት እንደሆነ አናውቅምን (http://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2016/09/blog-post_14.html)? እስካሁን ያሉን የፖለቲካ ችግሮቻችን ከማህበረሰባዊ ክፍፍል የመነጩ ናቸው። ስለ ህወሓት የምንለው «ከፋፍሎ ገዛን» አይደለምን? ታድያ ከጎረቤታችን ጋር የተጣላን፤ ሰውን የናቅን፤ ሰው ላይ የፈረድን፤ ባለንጀራችንን ያልደገፍን ሁሉ ኃጢአተንኛ መሆናችንን ማመን ያለብን ይመስለኛል። «ህዝብ (አንዳንዴ) የሚገባውን መንግስት ያገኛል» ይባላል።

አዎን ይቅርታን መጠየቅ ከባድ ነው። ሁላችንም ኃጢአተኞች እንደሆንን ልባችን ያውቃል። ግን ይህን ማመኑ የሚያገልጠውን ህፍረት እና ቁስል እንፈረዋለን። ስለዚህ ኃጢአቶቻችንን  ለመሸፈን እንወዳለን። ይህንን በማወቅ ነው ቅዱስ ጳውሎስ ሲያስተምርን ዘንድ እራሱን «የኃጢአተኞች ዋና» ብሎ የሰየመው። ታድያ ሃዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ማለት ከቻለ እኛ እጅግ ኃጢአተኞች የሆንነው ምን እንበል?

ንስሃ መግባት ነፃ ያወጣል ከአቅመ ቢስነት ወደ አቅም መጎልበት ያሻግራል። ሰው ላይ ጣትን መጠቆም ሽንፈት እና እራስን አቅመ ቢስ ማድረግ ማለት ነው። የኢትዮጵያ ችግሮች የራሴ ናቸው መፍትሄውም ከራሴ መጅመር አለበት ብዬ አምናለሁ። ይህንን ነው ጠቅላይ ሚኒስቴ አብይ ሊያስተምሩን የፈለጉት።