https://www.youtube.com/watch?v=fhKBwe1wF2Y
ይህ ድክመት ከመሬታቸው የተፈናቀሉት ወንድሞች እይቶቻችን ጎረቤቶቻችንን ዞር ብለን አለማየት ነው። በመቶ ሺዎች «የብሎኬት ካሳ» ተሰጥተው ከቤታቸው ወደ ዳር ከተማ ባዶ የሆነ 70 ካራሜትር ተባርረዋል።
ሰፈር ከነ ማህበራዊ ኑሮ ተበታትነዋል። አብዮተኛ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ማለት ይቻላል። ይህ ለተፈናቃዮች ብቻ ሳይሆን ለመላው የአዲስ አበባ ህዝብ ምን ያህል ጎጂ እንደሆነ ይታወቃል። "Social capital" ከሰረ፤ መተባበር ጠፋ፤ መተዋወቅ ጠፋ፤ መደጋገፍ ጠፋ፤ ማህበራዊ ግብረ ገብ ጠፋ፤ ኢ-ማህበራዊነት በዛ፤ ወንጀል በዛ ወዘተ።
አንዱ ለችግሩ መፍትሄ የመሬት ፖሊሲውን መቀየር ነው።
1. ካሁን ወድያ መንግስት መሬት መውሰድ የሚችለው ለመንግስት ጥቅም እንደ መብራት፤ ውሃ፤ መንገድ ወዘተ ይሁን። ካሳውም የ«ብሎኬት ዋጋ» ሳይሆን የመሬቱ ከነቤቱ የገበያ ዋጋ መሆን አለበት።
2. መሬት ለግል ጉዳይ እንደ ኢንቬስትሜንት ከተፈለገ ኢንቬስተሩ በግል ከመሬት ባለቤቶቹ መሬቱን ተደራድሮ ይግዛ። መንግስት ጣልቃ አይግባ። ገዥ እና ሻጭ ከተስማሙ ሁለቱም ደስተኛ ይሆናሉ። ኢንቬስተሩ የገበያ ዋጋ ስለከፈለ በመሬቱ አይቀልድም አዋጪ ነገር ላይ ያውለዋል። ሻጩም ተበድያለሁ አይልም በራሴ የወሰንኩትን አገኘሁኝ ብሎ ያምናል።
የሚጠቀም ሶስተኛ ወገኖችም አሉ። መላው የአዲስ አበባ ህዝብ ከመፈናቀል የሚያመጣው ጠቅላላ ህምሞች ይተርፋል። የመንግስት ሰራተኞችም ከሙስና ፈተና ይድናሉ። ማፈናቀል ወይንም የመሬት ፖሊሲው በጠቅላላ ካድሬዎች በረካሽ አፈናቅለው በውድ ለኢንቬስተር በመስጠት ሙስና የጋበዘ ስርዓት ነበር። ፖሊሲው ከተቀየረ ሁላችንም ከዚህ ሁሉ እንተርፋለን።
No comments:
Post a Comment
ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!