እንደሚታወቀው ኢህአዴግ ዘጠኝ ዓመት በፊት ባሳወጀው ህግ በሰባዊ መብት፤ የብሄር ብሄረሰብ ጉዳዮች፤ የጾታ ልጆች አካል ጉዳተኞች ጉዳዮች ወዘተ የሚሰሩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች (በአድ) ከ90% በላይ ገቢአቸውን ከሀገር ውስጥ ማግኘት አለባቸው። ህጉ ሲረቀቅ የተተቸው ምክንያት ኢህአዴግ የሰባዊ መብት ጥሰቶቹ በድርጅቶች እንዳይመረመሩ ኣና ዓለም አቀፍም ሀገራዊም አይን እንዳይበዛበት ነው። እውነትም ህጉ የተመሰረተው ዋና ምክንያት ይህ ነው።
ግን አሁን በመጣው የፖለቲካ ለውጦች መንግሥት የሰባዊ መብት መጣስን እየተወ ነው ለህብረተሰቡም ለድርጅቶችም የመተቸት እና የይግባኝ ማለት ነፃነት ሰጥቷል። እንደ ፍርድ ቤት አይነት መዋቅሮችም እየተሻሻሉ ነው። ፖለቲካውም ወደ ሰላም እየተቀየረ ነው። ስለዚህ ሀገር ውስጥ ያለው ህብረተሰብ ስለ ሰባዊ መብት ወይንም ሌላ ጉዳይ የሚሟገት ድርጅት በሰላም እና አለ ፍርሃት ማቋቋም ይችላል። የውጭ ሀገር ድርጅቶች ወይንም ገንዘባቸውን ከውጭ ሀገር የሚያገኙ ድርጅቶች አስፈላጊ አይደሉም።
አስፈላጊ ባይሆኑም ለምን ገቢያቸውን ከሀገር ውጭ የሚያገኙ ድርጅቶች ይከልከሉ፤ ህጉ ይቀየር እና ይፈቀድላቸው። በዛውኑ ውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊዎች የሚደጉሟቸው ድርጅቶች በነፃነት ማገልገል ይችላሉ። እንደዚህ የሚሉ አሉ።
ግን ይህ በዙ ሰው የማያስበውን ችግሮች ያመጣል። ብውጭ ገንዘብ የሚመሩ ድርጅቶች የሚያንጸባርቁት የለጋሾቻቸውን ፍላጎት እና አላማ ነው። የሚሰሩት ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ለለጋሾቻቸው ነው። የለጋሾቻቸው አላማ ደግሞ ከኢትዮጵያ ህዝብ ፈቃድ ውጭ ሊሆን ይችላል።
ለምሳሌ የውጭ ሀገር የፖለቲካ እና ባህል በኢትዮጵያ ሊያስፋፉ ይችላሉ። ጸረ ሃይማኖት ፍልስፍኖችን እና ርዕዮተ ዓለሞችን ሊያስፋፉ ይችላሉ። ጸንፈኛ ጎሰኝነትን ሊደግሙ ይችላሉ በኃይለ ሥላሴ ዘመን እንደተደረገው። ጸንፈኛ ሃይማኖትም እንዲሁ። በተለያየ መንገዶች የውጭ ሀገር ተጽዕኖ በሀገራችን ላይ እንዲጠነክር ማድረግ ይችላሉ። ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብን ሊከፋፍል እና ሊጎዳ ይችላል እና ኢትዮጵያን ከሌሎች ሀገር አንጻር ሊያደክማት ይችላል።
ማወቅ ያለብን በጎ አድራጎት ድርጅቶች በመጀመርያ ደረጃ የለጋሾቻቸው መሳርያዎች ናቸው እንጂ የበጎ አድራጎት ሰራተኞች አይደሉም። የውጭ ሀገር ድርጅቶች ወይንም ከውጭ ሀገር ገንዘብ የሚያገኙ ድርጅቶች የዛን ውጭ ሀገር መንግስት ወይንም ሌላ ለጋሽ ፍላጎት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ያንጸባርቃሉ። የዛን ሀገር የውጭ ጉዳይ መሳርያዎች ናቸው።
ግን እንደዚህ ቢሆንም የነዚህ ድርጅቶችን መልእክት መቀበል ፋንታ የኢትዮጵያ ህዝብ ይሁን እና ለምን ይከለከላሉ የሚሉ አሉ። እውነት ነው ህዝብ የመወሰን ነፃነት ሊኖረው ይገባል። ግን ጉዳዩ እንደዚህ ቀላል አይደለም። ለምሳሌ በፖለቲካ ውድድር አንዱ ፓርቲ የሌላው 10 እጥፍ ገንዘብ ካለው የገንዘብ ኃይሉ እንዲያሸንፍ ያደርገዋል። እያንዳንዱ ግለሰብ አንድ ምርጫ ያለው የህዝባ ምርጫ ቢሆንም ገንዘብ ታላቅ ሚና ይጫወታል። ይህ ገንዘብ ለማስታወቅያ እና ለጥቅም (ጉቦ) ይውላል እና በዚህ መንገድ የሰውን ምርጫ ይገዛል። ስለዚህ የገንዘብ ሚና በምርጫ ታላቅ ነው። የበጎ አድራጎት ድርጅቶችም ጉዳይ እንዲሁ ነው። ብር ያለው ህዝብ ላይ ይበልጥ ተጸዕኖ አለው። የሀገራዊ ድርጅቶችን ያፍኗቸዋል።
ሌላው ከውጭ ሀገር ወደ በጎ አድራጎት ድርጅቶች የሚመጣ ገንዘብ መከልከል ጥቅም የሀገሪቷ ህዝብ ድርጅት መደገፍ እና ማቋቋም እንዲለምድ ነው። ለምሳሌ ህዝቡ በልጆች አስተዳደግ ዙርያ ስራ ያስፈልጋል ድርጅት ያስፈልጋል ካለ እራሱ ከኪሱ አውጥቶ ድርጅት ይመስረት። ይህ ድርጅት ሙሉ ለ ሙሉ ህዝብን ይወክላል ማለት ይቻላል። ይህ ድርጅት ህዝብ የሚፈልገውን ያደርጋል እንጂ የውጭ ለጋሾች የሚፈልጉትን አያደርግም። ይህ ነው እውነት «ዴሞክራሲ» ተጠሪነት እና ሃላፊነት።
ስለዚህ በነዚህ ሁለት ምክንያቶች፤ 1) አላግባብ የውጭ ቅኝ ግዛት ተጽዕኖ እና 2) ሀገር በቀል ድርጅቶች እንዲጎለቡ እንዳይታፈኑ ያለው ህግ እንዳለ ይሁን። መሻሻል ካለበትም ሁሉንም በጎ አድራጎት ድርጅቶች ገንዘባቸው በሙሉ ከሀገር ውስጥ ማድረግ ነው።
የሰላም ክፍሌ ይትባረክ ብሎግ፤ ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለኝን ትናንሽ ሀሳቦች በትህትና አቀርባለሁ። ለስሕተቶቼም በቅድሚያ ይቅርታ እጠይቃለሁ
Thursday, 9 August 2018
Friday, 3 August 2018
የበታችነት ስሜት
ሰላሳ አርባ ዓመታት በፊት ከሀገሩ የሚሰደድ ኢትዮጵያዊ ወደ ምዕራብ ሀገር ሲሄድ ከሀገሩ ይበልጥ «የሰለጠነ» እና «የበለጸገ» ሀገር አግኝቻለሁ ብሎ ያስቡ ነበር። የምዕራብ ሀገሮች በሀብት፤ በብልጽግና፤ በግብረ ገብነት፤ በቅልትፍና (efficiency)፤ በንፅህና ወዘተ ከኢትዮጵያ የላቁ መሆናቸው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ያምን ነበር።
ሆኖም ግን ስደተኛው ምዕራብ ሀገሮችን ቢያደንቅም የሚተችባቸው ጉዳዮች ነበሩ። ለምሳሌ «ዘረኝነትን ያራምዳሉ» ይላል። በአዲስ ቅኝ ግዛት ታዳጊ ሀገራትን ያጠቃሉ ይዘርፋሉ። ኢትዮጵያ ለቅኝ ግዛት ስለማትመች እነ አሜሪካ ካዷት እና በደርግ አይነቱ አረመኔ መንግስት በማርክሲዝም እንድትገዛ አደረጉ። በተለያዩ ሀገራት ሕጋዊ የሆኑ መንግስታትን ይገለብጣሉ። ወዘተ። ኢትዮጵያዊ ስደተኛው ልሂቃኑም የምዕራብ ሀገሮችን በዚህ መልኩ ይከሱ ነበር።
በርካታ ስደተኞች እንደዚህ በማለት የምዕራብ ሀገሮችን ተችተው ሀገራቸው ኢትዮጵያ ችግሮች ቢኖሯትም ከነዚህ ሀገሮች በማንነት ደረጃ አታንስም ብለው ያምኑ ነበር። በዚህ ምክንያት የሀገር የማንነት የበታችንነት ስሜት (inferiority complex) ገና ብዙ አላደረባቸውም። በኢትዮጵያዊነቱ ያለው ኩራት ብዙ አልተቦረቦረም ነበር።
ግን ጊዜው ባለፈ ቁጥር ኢትዮጵያ «አልሻሻል» ስትል ባንጻሩ የምዕራብ ሀገሮች በብልጽግና እይናሩ እና አንዳንድ ልውጦች ሲያደርጉ የፕሮፓጋንዳ ስልታቸውም እየዳበረ ሲሄድ ኢትዮጵያዊ ስደተኛው በአሙሮው የምዕራቡን ዓለም እያበለጠ ሀገሩ ኢትዮጵያን እያሳነሰ ሄደ። ቀስ በቀስ የበታችነት ስሜት (inferiority complex) እያደረበት ሄደ። የህ የበታችነት ስሜት ወደ ሀገር ቤትም ገባ።
ወደ ምዕራብ ሀገር የተሰደደ ኢትዮጵያዊ ደህና ገቢ ማግኘት እና ሃብት ማከማቸት ቻለ። ስደተኛው ድሮ ቢገጥመውም ባይገጥመውም የሚያማርረው ዘረኝነቱ እየቀነሰ ሲሄድ አየ። ለነገሩ ዘረኝነቱ ድሮም ኑሮውን ከማሻሻል አልከለከለውም ነበር። አህን ግን ጭራሽ በጥቁርነቱ ስራ ከማጣት ማግኘት ጀመረ! ባሜሪካ ልጆቹ በጉብዝናቸው ብቻ ሳይሆን የጭቁን (ጥቅር) ዘር በመሆናቸው ስኮላርሺፕ ማግኘት ጀመሩ። የአሜሪካ ኑሮ ከድሮም ይበልጥ እየተመቸ ሄደ።
ይህ ስደተኛ ኑሮው «እየተሳካለት» በሄደ ቁጥር አሜሪካ በሱ አይን ይበልጥ እያማረች ሄደች። ፍትሐዊና መሐበራዊ ስነ ሥርዐቱን ከድሮም ይበልጥ ማደነቅ ጀመረ። ለሴቶች፤ ለልጆች፤ ለጥቁሮች ወዘተ ያለው «መብት» እና ጥንቃቄ ከኢትዮጵያ ጋር ሲያነጻጽረው ይገርመዋል። በፖለቲካ ደረጃ «ዴሞክራሲ» አምላኩ ሆነ «ሲኤንኤን» (CNN) መላዕክቱ ሆነ። በአንጻሩ ኢትዮጵያ በስደተኛው አይን እየቀነሰች እየወረደች ሄደች። አልሻሻል አለች እየባሰችም ሄደች። ስደተኛው ሀገሩን በጎበኛት ቁጥር ከአሜሪካ ጋር እያንጻጸረ ዘመዶቹን ያደነቁራል። በአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ያለውን ልዩነት ለማሳየት ያህል ዘመዱን ከ«ሀገር ቤት» ለመውጣት በርካታ አስር ሺዎች ዶላር ይከፍላል።
ዛሬ በኛ በኢትዮጵያውያን የዝቅተኘት መንፈስ በደምብ አድሮብናል ማለት ከእውነት የራቀ አይመስለኝም። ግን ይህ መንፈስ እውነትን ነው የሚያንጸባርቀው? እውነት ዝቅተኛ ህብረተሰብ ነን? ወይም ሀገራችን ዝቅተኛ ነው? ይበልጥ ታላቅ የሆነው ጥያቄ ሙሉ ሰው ለመሆን ወይንም በዘመኑ ቋንቋ «መሻሻል» ከፈለግን እንደ ምዕራቡ ዓለም መሆን ይኖርብናል? ምናልባት ዘፈናችን ጭፈራችን ምግባችንን ለትዝታ ብለን ጠብቀን በሌላው በሙሉ እንደነሱ እንደ ምዕራባዊያን መሆን ይኖርብን ይሆን?
እዚህ ላይ በቀለም ትምሕርት ከምንማረው በሚዲያ ከምንሰማው ፕሮፓጋንዳና ተራ «እውቀት» ወጥተን እናስብ። በአዲሱ ቅን ግዛት የተገዛውን አእምሮአችንን ነፃ እናውጣው የብዥታ መነጽራችንን እንጣል። በመጀመርያ እስቲ ምንድነው «ስልጣኔ» ብለን እንጀምር። ጥያቄውን በምሳሌ ኃይል ለመመርመር ታዋቂውን የሮሜን ስልጣኔን እንመልከት።
በክርስቶስ ዘመን በርካታ አይሁዶች ወደ ሀገራቸውን ወርሮ የገዛው ሮሜ ይፈልሱ ነበር። አንድ አይሁድ ወደ ሮሜ ሲሄደ ዛሬ ኢትዮጵያዊ ከሀገሩ ወደ አሜሪካ እንደመሄድ እናመሳስለው። ሮሜ ሀብታም ነበረች። «ስደተኞችን» መጤዎችን ትቀበላለች ታስተናግዳለች ታበለጽጋለች። ውጣ ውረድ ቢኖረውም መጤዎች የሮሜ ዜጋ የመሆን እድል አላቸው። የሮሜ ዜግነት አንደ ይሁዳ ዜግነት በጎሳ በብሄር በደም የተወሰነ አይደለም ማንም የሮሜ ዜጋ መሆን ይችላል። የሮሜ ፍርድ ቤቶች በደምብ ይሰራሉ በተለይ ለሮሜ ዜጎች እውነተኛ ፍትሕ ይሰጣሉ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ችግር ባጋጠመው ቁጥር አይሁዶች ሲገሱት ሲሉ የሮሜ ዜግነቱን ተጠቅሞ ፍርድ ይጠይቃል! በሮሜ ፍርድ ቤት ትክክለኛ የፍርድ ሂደት እንደሚጠብቀው ስለሚያውቅ ነው። የሮሜ መንግስታዊ አስተዳደር ፍፁም ባይሆንም ከሌሎች አንጻር «የሰለጠነ» ነበር። «ዴሞክራሲ» አይነት ከነ ምክር ቤት አለው። በሮሜ የማሕበራዊ ብረ ገብ አለ። የሴቶች «መብቶች» ከሌሎች ሀገሮች ከይሁዳ ይልቅ የተከበሩ ናቸው። በስነ ሥርዓት በኩልም ሮሜ የስለጠነች ናት። መንገዶቿ ንፁ ናቸው። መንገደኛ ለመንገደኛ ጎረቤት ለጎረቤት አገልጋይ ለባለጉዳይ ያለው ግንኙነት በጥቅም የተሳሰረ ሰላማዊና የተቀላጠፈ (efficient) ነው። የድሮ «ሮሜ» ስልጣኔ እንደዚህ ይመስላል።
ለዚህም ነው አይሁዶችም ሌሎችም ወደ ሮሜ የሚፈልሱት ሃብቱን እና ስልጣኔውን ፈልገው። ልክ እንደ ኢትዮጵያውያን ወደ አሜሪካ እንደምንፈልሰው «ህይወትን ለማሻሻል» ወደ በአድ ሀገር ይሄዱ ነበር። ግን ሮሜ የይሁዳ ቅኝ ገዥ ነበረች! አይሁዶች ወደ የሚገዛቸው ሀገር ነበር የሚሄዱት። ወደ ዓለምን በሙሉ በጉልበቷ የተቆጣጠረቹ ሮሜ ነበር ለተሻለ ኑሮ ብለው የሚሄዱት። ግን አይሁዶቹንም ሌሎች መጤዎችንም የሮሜ ስልጣኔ ክፋነቷን እንዳያዩ አድርጓቸዋል አሳውራቸው። ለነሱ ሮሜ የብልጽግና ሀገር እንጂ የክፋት ሀገር አልነበረትም። ሮሜ ሀገራቸው ይሁዳ የሌላት ነገሮች ሁሉ አላት። በዚህ ምክንያት በራሳቸው ባህልና ማንነት ዝቅጠኝነት ተሰማቸው እንደ ሮሜዎች መሆነ ፈለጉ ወደ ሮሜ ህብረተሰብ ተቀላቀሉ።
ይህ ምሳሌ ስለ «ስልጣኔን» ምን ያስተምረናል? ለብዙዎቻችን ስልጣኔ ሀብት ማለት ነው። ሀብት ካለ ሌሎች ጉድለቶች አያታዩንም። ስልጣኔ «ቴክኖሎጂ» ይመስለናል። የሮሜ የከተማው ቧምቧ እና ፍሳሽ ስራ አይሁዶችን ይገርማቸው ነበር። ስልጣኔ ቅልጥፍና (efficiency) ይመስለናል። የሮሜ የመነግስት መዋቅሮች በተለይ ጦር ሰራዊቱ ግቡን በቀላሉ ያስፈጽም ነበር። ስልጣኔ ፍትሕ ነው። ስልጣኔ ግብረ ገብ እና ስነ መግባር ነው።
እነዚህን ሁሉ ስንመለከት ግን ባጭሩ ስልጣኔ ማለት ነግ በኔን በደምብ ማወቅ ነው። አካባቢዬን አላቆሽሽም ሌሎችን መንገደኞችን ውድጅያቸው ሳይሆን ንፁ አካባቢ ስለሚበጀኝ እኔ ካላቆሸሽኩኝ ሌሎችም ስለማያቆሽሹ ነው። እኔ መኪና የማሽከረክረው ሕግ አክብሬ ነው ሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎችን ስለምወዳቸው ሳይሆን ሁላችንም በትክክል ካሽከረከርን ሁላችንም በፍጥነንት እና በሰላም የምንፈልግበት ቦታ ለመድረስ ስለሚያመችን ነው። መንግስቴ ለደሆች እርዳታ እንዲያደርግ እወዳለሁ ሰላምን ለመጠበቅ እኔም ነገ ብወድቅ እርዳታ እንዳገኝ። ወዘተ። ይህ ነው ስልጣኔ ባጭሩ። ሮሜም አሜሪካም የትም ህዝብ ሰላምና ሀብት እያገኘ ሲሄድ ለራሱ ለግል ምቾቱ የሚሆን አሰራሮች ስነ ምግባሮች እየገባው በተግባር መዋል ይጀምራል።
ግን ይህ ስልጣኔ ከጥሩነት፤ በጎነት፤ ሰላም ወዳድነት እና ከፍቅር ጋር አይገናኝም። ነግ በኔ በጎነትም ፍቅርም አይደለም። «የሰለጠነ» ራስ ወዳድነት ነው። ማንም ከጊዜ በሚያመጣው ልምድ በኋላ የሚደርስበት ነው። ማንም ደግሞ ችግሮች ሲያጋጥሙት ካልተመቸው የሚተወው ነው። ሮሜ ለራሷ የሰለጠነች ነበር ለሌሎች ሀገሮች ግን የክፋት መዓበል ነበረች። ዛሬ አሜሪካም አውሮፓም ሌሎችም ለራሳቸው የሰለጠኑ ናቸው ግን ከጠረፍ ውጭ አይደሉም።
ስለዚህ ይህ ሀገር የሰለጠነ ነው የኔ ሀገር አይደለም ብለን የበታችነት ስሜት ሊኖረን ይግባል? በፍፁም! ስልጣኔ ማንንነት አይደለም። ስልጣኔ ይመጣል ይሄዳል በዓለም ታሪክ በተለያዩ ቦታዎች ተገንብቷል ፈርሷል። ስልጣኔ ከፍቅርና በጎነት አይገናኝም። የሰው ማንነት ግን በጎነት፤ ፍቅር፤ ሰላም ወዘተ ነው። ስለዚህ የሰው ልጅ እነዚህን የሚሽህ እስከሆነ መቼም የበታችነት ሊሰማው አይገባም! ከፍቅር ይልቅ «ብልጭልጭን» ሲያመልክ ነው ችግሩ የሚመጣው።
ይህን ተክትሎ እንደ ምዕራቡ ዓለም መሆን አለብን ብሎ ማሰቡም ተገቢ አይደለም። ለምን ብትሉ የምዕራባዊያን ርዕዮት ዓለም ከኢትዮጵያዊነት ትውፊትና ማንነት 180 ዲግሪ የተቃረነ ነው። የምዕራባዊ አስተሳሰብ የሰው ልጅ የዓለም ቁንጮ አድርጎ ያስቀምጠዋል። እግዚአብሔር የለም ወይንም ምንም ሚና አይጫወትም ይላል። ኢትዮጵያዊ ግን በትውፊታችን ፈጣሪ ነው በአምሳሉ የፈጠረን ብለን እናምናለን ሁሉ ነገራችንም ከዛ ይከተላል። ለዚህም ነው የጠ/ሚ አብይ አህመድ የይቅርታ፤ ፍቅር እና ሰላም መልዕክቶችን በደስታ እና ጉጉት የምንቀበለው። እንደዚህ አይነቱ መልዕክት የተም ምዕራብ ሀገር እንደ ህፃንነት ነበር የሚታየው። ስለ ልማት፤ ነፃነት፤ መብት ነው የምዕራብ ሀገር ውይይት። እግዚአብሔር የለምና።
ታሪክ ረዥም ነው። 500 ዓመት በፊት ቻይና ከሁሉም «የሰለጠነች» ነበር። 60 ዓመት በፊት ቻይና ወደ 40 ሚሊዮን ህዝቦቿን ገደለች ግማሽ ሀገሪቷ በርሃብ እየተሰቃየ ነበር። 2000 ዓመት በፊት ስሜን አውሮፓ በሮሜዎች ዘንድ የያልሰለጠና የአረመኔ ስፍራ ነበር። ዛሬ ደግሞ ከዓለም በሙሉ የሰለጠው ጎራ ይባላል። 60 ዓመት በፊት ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ ታላቅ ክብር ነበራት። ዛሬ እንደ ለማኝ ትታያለች። እኛ ኢትዮጵያዊያን ይህንን ብናስታውስ ጥሩ ይመስለኛል።
እውነት ስልጣኔ ፍቅር እና ሰላም ነው። የኛ የኢትዮጵያዊያን በዚህ ረገድ ከማንም ልናንስም ልንበልጥም እንችላለን የኛ ፋንታ ነው። ግን የሰው ልጅ በመሆናችን ከማንም አናንስም አንበልጥምም። የዝቅተኛ ስሜታችንም በምንም መለክያ ተገቢ አይደለም። እጅግ ጎጂም ነው። ሌላውን ምዕራባዊያንም ለመገልበጥ መሻህ ዋጋ የለውም ጎጂ ነው። ማንነታች ከፈጣሪያችን የተሰጠን ነውና ምንም የምናፍርበት ሊሆን አይገባም። እርግጥም ለሌሎች ምሳሌ ሆነን መገኘት ነው ያለብን ድሮ ሆነን እናውቃለን አሁንም የማንሆንበት ምክንያት የለም።

Wednesday, 1 August 2018
ስለ አማራ ብሄርተኝነት አንድ የውይይት ምዕራፍ
1. አማራ የተጠቃው በብሄር ስም ስላልተደራጀ ነው ከሆነ የጎሰኝነትን ፍልስፍና አምነንበታል ማለት ነው። አማራ 60 ዓመት በፊት በተለየ መልኩ እየተጠቃ ነበርን? አይደለም ከሆነ መልሱ ጥቃቱ የተጀመረው የጎሳል ፖለቲካ ሀገር ውስጥ ሲገባ ነው ማለት ነው። ይሄውን ያጠቃንን ፍልስፍና መቀበል ሽንፈት እና ይበልጥ ጥቃት ነው።
2. አማራ በብሄር መደራጀቱ የአማራን ጥቅም አያስከብርም ብዬ ነው የማምነው። ለምን? በብሄር ተደራጀን ማለት ክልላችንን አስከበርን ማለት ነው በዛሬው ፖለቲካ ሌላ ትርጉም የልውም። ከአማራ ክልል ውጭ ያለውን አማራ አዲስ አበባም ላለው አማራ ምንም ልናደርግለት አንችልም። ነገ በኦሮሚያ የአማርኛ ትምሕርትቤቶች ሁሉ ይዘጋሉ ቢባል (በዴሞክራሲያዊ ምርጫ በድምጽ ብልጫ ማለት ነው) አማራው ምን ሊያደርግ ነው። ኦሮምኛ በአማራ ክልል መከልከል?! በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ሶማሌ ተናጋሪ በመንግስትም ሌሎችም ስራዎች ቀድሞ የሚቀጠረው ቢባል አማራው ምን ያደርጋል። ድምጽ ብልጫ የለውም። አዲስ አበባ አተሰፋም ቢባል አማራው ድርጅት ምን ያደርጋል? ከአማራ ክልል ውጭ ያሉት አማሮች የአማራ ድርጅቱ አባል ቢሆኑ ምን ይጠቅማቸዋል ጥቃት ብቻ ይሆናቸዋል እንጂ። ግን አማራው በስመ ኢትዮጵያዊነት ቢደራጅ ከሌሎች (የዘር ቅልቅሎች እና ሌሎች ብሄሮች) ስምምነት ( alliance) እያደረገ ይበልጥ ኃይል ይኖረዋል። ይህ ይበልጥ መላው ሀገር ውስጥ ያለውን አማራ መብት ያስከብራል።
3. «ውሸት አንድነት ይብቃ፡፡ ስንቴ እንታለል፡፡» ይህ በትክክል የጎሰኞቹ አቋም ነው። አቋማቸው እንዲህ ነው 1) ኢትዮጵያ ስለካደችን ወደ ጎሳችን እንመለስ 2) ኢትዮጵያ የካዳችን የፈረሰችበት ምክንያት መጀመርያውኑ ሀገር ሳይሆን የጎሳዎች እስር ቤት ስለሆነች ነው። መፍረስዋ ይህን ነው የሚያመለክተው ነው አቋማቸው። አሁንም የአማራ ብሄርተኝነት እንዲህ ነው የሚለው። እራስህን መጠየቅ ያለብህ «አንድነት» እንደምትለው «ውሽት» ወይም ውድቅ የሆነው በኛ በአስፈጻሚው ድክመት ነው ወይንም «አንድነት» የሚለው ጽንሰ ሀሳብ ከመጀመርያ ውሸት ስለሆነ ነው? የመጨረሻው ከሆነ መልስህ መጀመርያውኑ ያጠቃህ የጎሰኝነትን ፍልስፍና ጠቀብለሃል ማለት ነው። የመጀመርያ ከሆነ መልስህ ማድረግ ያልብን አንድነትን መተው ሳይሆን መትክክሉ ማስፈጸም ነው። «አንድነት» የተበላሸው እኛ የአንድነት ደጋፊዎች ከነ ሁሉም አማራ (በዛን ጊዜ) እርስ በርስ በፈረንጅ ፍልፍና ተለክፈን ስለተከፋፈልን ነው እንጂ አንድነቱ ራሱ ችግር ኖሮት አይደለም። አይደለምን?
4. ለላይ ጠቅሼዋለሁ እንጂ የራሱ ነጥብ ይገባዋል፤ በስመ አማራ መደራጀት ከሌሎች «ኢትዮጵያዊ ነን» ከሚሉ ጋር ለመጋራት ያለንን እድል ይቀንሳል። ለምሳሌ አዲስ አበባ ወይንም ናዝረት የህብረ ብሄር ድርጅት በቀላሉ ምርጫ ያሸንፋል ግን የአማራ ድርጅት አያሸንፍም። የህብረ ብሄር ድርጅቱ ያአማራውን መብት በደምብ ያስከብራል። የሚበጀን ምን እንደሆነ ግልጽ ነው።
5. መጠቃት ስሜትን ይነካል ይገባኛል። ግን ስሜታዊ ሆኖ ላለ ችግር ወደ ተሳሳተ መፍትሄ መግባት ጎጂ ነው ባለፉት 60 ዓመት የሀገራችን ታሪክ ነው። «መሬት ላራሹ» ብለን መሬትን ለመንግስት ሰጥተን። አንባገንነት ብለን ወደ ጎስኝነት ገባን። ወዘተ። አሁንም አማሮች ተጠቃን እንላለን መፍትሄው ግን በኢትዮጵያዊነት መደራጀት ነው።
6. በኢትዮጵያዊነት መደራጀት ያልቻልንበት ምክንያት እንደጠቀስኩት ከ60 ዓመት በፊት በፈረንጅ ፍልስፍና ተወክፈን እርስ በርስ መፋጀታችን ነው። ይህ የሆነው በኢትዮጵያዊነት ስለተደራጀን አይደለም። አሁንም በስመ አማራ እንደራጅ በኢትዮጵያዊነት ከመደራጀት ይቀላል የሚለው እጅግ የተሳሳተ ነው። በርካታው አማራ በስመ አማራ መደራጀት አይፈልግም። ምናልባት ከመቂ ፕሮፓጋንዳ በኋላ ቁጥሩ ይጨምር ይሆናል ግን ዛሬ የአማራ ብሄርተኝነት ከፋፋይ ሀሳብ ነው። ባሁኑ ወቅት አንድ በመሆናችን ጊዜ ከፋፋይ አቋምን መግፋት ምን ማለት ነው። የግቡን ተቃራኒ ነው።

Tuesday, 31 July 2018
ከኢትዮጵያ ብሄርተኞች (አንድነት ኃይሎች) የእርስ በርስ መጠፋፋት ታሪክ እንማር!
ኢትዮጵያዊነትን የምናራምድ የኢትዮጵያ ብሄርተኞች ባለፉት 60 ዓመታት በተደጋጋሚ እርስ በርስ መጣላት ሀገራችንን አደጋ ላይ መጣላችን ይታወቃል (http://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/07/blog-post_15.html)። መቼም በዚህ እፍረታችን ምክንያት የሀገራችንን ችግሮች በሌሎች (ጎሳ ብሄርተኞች፤ የውጭ ኃይሎች ወዘተ) ማሳበብ ሱስ ቢሆብንም እውነቱ የኛ ጥፋት መሆኑን መቀበል ግዴታችን ነው። ለሀገራችን ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ የኛ የኢትዮጵያ ብሄርተኞች አንድነት እና ታላቅ ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑ የታወቀ ነው።
ከዚህ ጽሁፍ ትምሕርት እንዲሆነን እና ወደ ፊት ስህተቶቻችንን እንዳንደግም ዘንድ ወደ ኋላ ሄጄ እኛ የኢትዮጵያ ብሄርተኞች እርስ በርስ የተፋጀንበት ታሪኮችን ማስታወስ እወዳለሁ። ዛሬ በሀገራችን ፖለቲካ ታላቁ ጉዳይ የጎሳ ብሄርተኝነት ስለሆነ እኛ የኢትዮጵያ ብሄርተኞች ከታሪካችን ተምረን ለሚመጣው የፖለቲካ ሂደት በደምብ መዘጋጀት አለብን። አሁን ያለንን የታሪክ እድል መጠቀም ግድ ነው። እግዚአብሔር ከዚ በኋላ ሌላ እድል ላይሰጠን ይችላልና።
እንሆ ላለፉት 60 ዓመታት የኢትዮጵያ ብሄርተኞች እርስ በርስ መጣላት ታሪክ ዝርዝር፤
1. የነ መንግስቱ ነዋይ እና ግርማሜ ነዋይ የመንግስት ግልበጣ ሙከራ (1953)፤ አስፈላጊ ለውጦችን ለማምጣት ባለው መዋቀር ውስጥ በትእግስት ከመስራት ፋንታ ግርማሜ በውጭ ሀገር በተማረው «ማርክሲዝም» ፍልስፍና ተመስርቶ ወደ «ስር ነቀል ለውጥ» ወይንም አብዮት አመራ። ይህ የተከሰተው ኃይለ ሥላሴ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ገና 18 ዓመት ካላፈ በኋላ ነው። ኢትዮጵያ ገና አቅም የሌላት ደሃ ሀገር ነበረች። ግርማሜ እና ደጋፊዎቹ ኃይለ ሥላሴ ወደ ውጭ ሀገር እንዲማሩ ከላኳቸው ተማሪዎች ነበሩ። ይህ ነበር የመጀመርያው ጊዜ የኃይለ ሥላሴ የፈረንጅ ትምሕርት ፖሊሲ በራሳቸው ላይ ጥቃት ያመጣባቸው። የኃይለ ሥላሴ መንግስት ከዚህ ተምሮ አስፈላጊ ለውጦችን ከማድረግ ፋንታ ስልጣንን ይበልት ሰበሰባ ለሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሄ ከፍተቶችን ዘጋ።
2. የተማሪዎች ንቅናቄ፤ ከነመንግስቱ ነዋይ ግልበጣ ሙከራ በኋላም የኃይለ ሥላሴ መንግስት ተማሪዎችን ለትምሕርት ወደ ውጭ ሀገር መላክ አላቆመም። የኢትዮጵያን ባህል እና ትውፊት ከማስተማር ፋንታ የምዕራባዊ ፍልስፍና እና ሶሺያል ሳየንስ እንዲማሩ አደረገ። እነዚህ ተማሪዎች ኢ-ኢትዮጵያዊ አስተሳሰቦች ይዘው ወደ ኢትዮጵያ መንግስት እና ሌሎች መስርያቤቶች ገቡ። የቀለም ትምሕርት አለአግባብ በመደነቁ ምክንያት «የተማረ ይግደለኝ» የሚለው አባባል ተፈጠረ (http://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2016/12/blog-post_7.html)። ይህ እሳት እየተለኮሰም መንግስት በትምሕርትም ደረጃ በፍትህ በተለይም በመሬት ፍትህ ዘርፍ ምንም አላደረገም። የኃይለ ሥላሴ መንግስት የኢትዮጵያ ለረዥም ዓመታት መርዝ የሚሆናት ትውልድ እና ባህል ፈጠረ። የ«ጨቋኝ ተጨቋኝ» አስተሳሰብ እንዲሰፍን አደረገ። የመደብ እና የጎሳ ጦርነት እንዲጀምር አደረገ። ዛሬ የዚህን "legacy" ነው የወረስነው።
3. የደርግ አብዮት፤ በኃይለ ሥላሴ መንግስት ተሃድሶ የሚፈልጉ በርካቶች ነበሩ ግን እድሉ ሳይደርሳቸው የተማሪዎች ንቅናቄ የሚፈልገው ስር ነቀል አብዮት መጣ እና ሀገሪቷን አፈነዳ። በርካታ ልሂቃን ተገደሉ ተሰደዱ። ለኢትዮጵያ ብቻ ስያሆን ለማንም ሀገር የማይሆን የፖለቲካ ፍልስፍና ሰፈነ። መሰረታዊ ነገር እንደ «መሬት ለአራሹ» ወደ «መሬት ለመንግስቱ» ሆኖ ቀረ። ኢትዮጵያ በደምብ ቁልቁል መውረድ ጀመረች። የደርግ በኃይል የተመሰረተ ጨቋኝ አገዛዝ ለጎሳ ብሄርተኞች በንዚን ሆናቸው እና በደምብ መንቀሳቀስ ጀመሩ። ድሮ በቀላሉ በትናንሽ ሰላማዊ ለውጦች መስተካከል የሚችሉት የጎሳ ጉዳዮች ወደ ጦር ሜዳ ገቡ።
4. የኢዲዩ መፈራረስ፤ ማርክሲስት ያልሆኑት የደርግ ተቃዋሚዎች በኢዲዩ ድርጅት ስር ለመታገል ወደ ሱዳን ገቡ። ከሞላ ጎደል አንድ አቋም እና አንድ አመጣጥ ኖሯቸውም እርስ በርስ መስማማት ባለመቻላቸው ከትንሽ ጊዜ በኋላ ተበታተኑ። ይህ በአንድ አቋም ያላቸው ኢትዮጵያ ብሄርተኞች መካከል እርስ በርስ መጣላት ታሪክ እስካሁን እየተደጋገመ ነው።
5. የኢህአፓ፤ መኢሶን፤ ደርግ ግጭት፤ እንዴ ማንኛውም የማርክሲስት አብዮት አብዮተኞ የፍልስፍና፤ የጥቅም እና የስልጣን ልዩነቶቻቸውን በተብ መንጃ ነው እነ ኢህአፓ፤ መኢሶን፤ ደርግ እና ሌሎች የተወጡት። የእነዚህ ድርጅቶች አብዛኛው አባላት በ«አንድ ኢትዮጵያ» የሚያምኑ የኢትዮጵያ ብሄርተኞች ነበሩ። እነ ኢህአፓ በመገንጠል እናምናለን ቢሉም ብዙ ኤርትራ እና ትግራይ ብሄርተኞች ቢኖሯቸውም አብዛኞቻቸው ኢትዮጵያ ብሄርተኞች ነበሩ። መኢሶንም የኦሮሞ ብሄርተኞች ቢኖሩትም አብዛኛው በአንድነት ያሚያምን ነበር። ደርግም እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄርተኞች ስፍራ ነበር። ሆኖም የነዚህ ድርጅቶች መፋጃጀት ለጎሳ ብሄርተኞች ታላቅ ድል ሆነ። የኢትዮጵያ ብሄርተኛው እርስ በርስ ሲተላለቅ የጎሳ ብሄርተኛ እየቀረ ሄደ ካስፈለገ ወደ ሻዕብያ፤ ህወሓት እና ኦነግ ገባ። ቀይ ሽብሩ ካበቃ በኋላ የተቆሳሰለች ኢትዮጵያ ናት የቀረችው። በጎሳ ብሄርተኞች ለመገዛት ዝግዱ የሆነች ደካማ ኢትዮጵያ ናት የቀረችው። ደርግ ከስልጣን ሲወርድ የኢትዮጵያ ብሄርተኛ ልሂቃን ራሱን አጥፍቶ ርዝራዡ ብቻ ነው የቅረው። ብዙሃኑም የፖለቲካ ልቡ ተስብሮ እየተንገዳገደ ነበር። የኢትዮጵያ የወደፊት የጎሰኝነት ዘመን ተወሰነላት።
6. የመላው አማራ እና መላው ኢትዮጵያ ፓርቲዎች ግጭት፤ ደርግ ኤኮኖሚውን ገድሎ፤ ህዝቡን አጥፍቶ፤ የሶቪየት ህብረት ሲፈርስ ገንዘብ አጥቶ እነ ሻዕብያ እና ህወሓትን ወደ መንግስት አስገባ። የኢትዮጵያ ብሄርተኛው ጎራ እራሱን አትፍቶ ሜዳውን ሙሉ በሙሉ ለጎሳ ብሄርተኞቹ ተወ። እነሱም ደንግጠውም ቢሆን ያልጠበቁትም ቢሆን ሜዳውን ለመቆጣጠር ቶሎ ስራ ጀመሩ። የኢትዮጵያ ብሄርተኛ ጎራው ከድንጋጤው በኋላ ልደራጅ ሲል የለመደው አብሮ መስራት አለመቻል እርስ በርስ መጣላት በሽታው እንደገና ተነሳበት። «መላው ኢትዮጵያ» ይህን ወይንም «መላው አማራ» ይሁን አውራ ፓርቲአችን በሚለው ጥያቄ የኛ «ወታደሮች» በ«ጠላት ሜዳ» ላይ እርስ በርስ መጣላት ጀመሩ! ላለመስማማት መስማማት እና በጋራ ጥቅም አብሮ መስራት ፋንታ አንዳችን ብቻ ነው የሚቀረው ብለው እርስ በርስ ተፋጁ እና ሁለቱንም ድርጅቶች («መላው ኢትዮጵያም» «መላው አማራም») አደከሙ። የጎሳ ብሄርተኞች ከዳር ሆነው በሳቅ ሞቱ። ግን አሁንም እኛ የኢትዮጵያ ብሄርተኞች ጥፋታችንን ከማመን እነ ከመፍታት ፋንታ የጎሳ ብሄርተኞች ጥፋት ነው እነሱ ናቸው ያከፋፈሉን ብለን እንደ ህጻናት አሳበብን። እንሆ ችግራችንን ስላላመንን አልፈታነውም። አልፎ ተርፎ ይህን ስህተትን ወደፊት ለመድገም እራሳችንን አዘጋደን!
7. የቅንጅት ግጭት፤ ወደ ምርጫ 97 ስንገባ ጠ/ሚ መለስ ዘናዊ በተለያዩ ምክንያቶች ነጻ ምርጫ እናሸንፋለን ዓለም ያከብረናል ብለው ነጻ ምርጫ አወጁ። ድንቅ ውሳኔ ነበር አሁንም ይደንቃል። ግን በዛን ግዜ የኢትዮጵያ ብሄርተኛ ጎራው በራሱ ካመጣው ቁስሎቹ ገና አልዳነም ነበር። ጠንካራ ድርጅት ከሀገር ውስጥም ውጭም አልነበረም። የእርስ በርስ ጥሉ እንዳለ ነበር። በዚህም ምክንያት ነው የኢትዮጵያ ብሄርተኛው ወደ አንድ ስምምነት (ቅንጅት) የገባው በመጨራሻው ደቂቃ ከምርጫው ሶስት ወር በፊት! ግን አርፍዶ ቢዘጋጅም እንደምንም አድርጎ የኢትዮጵያ ብሄርተኛው ጎራ በምርጫው ተሳትፎ በሚደንቅ ሁኔታ አሸነፈ። ካሸነፈ ብኋላ የምናውቀው ፈተናዎች አጋጠሙት። እነዚህን ፈተናዎች በደምብ አድርጎ ወደቀ። በሰው የተፈጥሮ ባህሪ ጓዶች አብረው ሲታሰሩ ፍቅራቸው እና ትብብራቸው ይጨምራል። የቅንጅት መሪዎች ሲታሰሩ ጭራሽ እርስ በርስ ተጣሉ!ድርጅቱም ምን ያህል ባዶ እንደነበረ ታየ። ከላይ የተወሰኑ መሪዎች በ100 የሚቆጠሩ ነበሩ ከዛ በታች ግን መዋቅር የሚባል ነገር አልነበረም። መዋቅር ስል በይፋ ብቻ ሳይሆን በልብም አልነበረም። ስለዚህ መንግስት ቅንጅትን ሲያጠቃ በምርጫው 70% እንዳሸነፈ ድርጅት ጥቃቱን ጠንክሮ ከመቋቋም ይልቅ እንደ ምንም ድጋፍ የሌለው ድርጅት ቀለጠ። ቅንጅት አሸዋ ላይ የተገነባ ቤት መሆኑን አየን። ግን ለዚህ ሽንፈት ምክንያት እንደነበረ እንገንዘብ። የኢትዮጵያ ብሄርተኞች ልሂቃን ከዛ በፊት ለ30 ዓመታት እርስ በርስ መፋጀት ታሪክ ምክንያት በጣም ሳስቶ ነበር። ለዚህም ነው ቅንጅት በተንሽ ግፊት የፈራረሰው። መሪዎቹ "cream of the crop" ሳይሆኑ ካለፈው 30 ዓመት የኢትዮጵያ ብሄርተኞች ጎራ እርስ በርስ መጨራረስ የተራረፉ ነበሩ። ታሪካችን ምን ያህል እንደ ጎዳን አየን።
8. ዛሬ፤ አሁንም የኢትዮጵያ ብሄርተኞች ጎራ እጅግ ደካማ ነው። አሁንም ሀገር ውስጥም ውጭም ብዙሀኑን በሚገባው የሚወክል ድርጅት የለውም። ግን ብዙሃኑ አለ ልሂቃን እየታገለ እንደሆነ የሚያሳየው እንደ ጠ/ሚ አብይ አህመድ አይነቱን ሰዎች ከዚህ ብዙሃን መውለዳቸው ነው። እንጂ ከ27 ዓመት የጎሳ ብሄርተኝነት በኋላ ኢትዮጵያ እውነትም የብሄር ብሄረሰቦች እስር ቤት ብትሆን እና በርካታ የሀገር ብሄርተኛ ባይኖራት እንደ አብይ አይነቱ አይፈጠርም ነበር እንቋን ወደ ስልጣን መግባት። ግን ይህ ብዙሃን ልሂቃን ያስፈልገዋል። እነ ጠ/ሚ አብይ በርካታ እገዛ ያስፈልጋቸዋል። ቢያንስ እንቅፋት አያስፈልጋቸውም!
አንድ እንቅፋት ሊሆን የሚችለው አዲሱ የ«አማራ ብሄርተኝነት» (https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/06/blog-post_14.html) ነው። የአማራ ብሄርተኝነት በኢትዮጵያዊነት አምናለው ይላል ግን የኢትዮጵያ ብሄርተኛውን ጎራ የመከፋፈል እና የማድከም አዝማምያ አለው። የአስተያየት ልዩነት መልካም ነው በአንድ አንድ ነገር ሳይስማሙ አብሮ መስራት ይቻላል። ግን አሁን የሚታየው የአብሮ መስራት አዝማምያ ሳይሆን የጥሎ ማለፍ መንፈስ ነው። የአማራ ብሄርተኛው ጎራ አንዱ መፈከሩ የኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ድርጅቶች ዋጋ የላቸውም ነው። ከኢትዮጵያ ብሄርተኛ ድርጅቶች ጋር አብሮ ከመስራት ያጣጥልዋቸዋል። ያው የነ ሻዕብያ፤ ህወሓት፤ ኦነግ ፎቶኮፕይ ማለት ነው። የህዝብን ብሶት በጎሳ ቤንዚን ለኩሶ የፖለቲካ ኃይል ማግኘት ነው። ልክ ህወሓት በመጀመርያ ነባር የጥግራይ ልሂቃንን እንዳጠፋ አንድ አንድ የአማራ ብሄርተኞች የኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ድርጅቶችን ማጥፋት ይፈልጋሉ። እንደነ ኢህአፓ/መኢሶን/ደርግ የማርክሲስት ዜሮ ድምር ፖለቲካ ማለት ነው።
ይህ የሚመስልኝ ታሪክን መድገም ነው። የኢትዮጵያ ብሄርተኞች እንደገና እርስ በርስ ሲፋጁ የጎሳ ብሄርተኖች ስልጣን ይቆጣጠራሉ የኢትዮጵያ ብሄርተኛ ብዙሃን እንደገና መሪ አልባ ሆኖ ይጠቃል። ከታሪካችን ብንማር ይበጀናል። በዛሬው የፖለቲካ ለውጥ እግዚአብሔር የማይገባንን እድል ሰጥቶናል። እኛ የኢትዮጵያ ብሄርተኛ ልሂቃን ምንም የሚጠቅም ነገር ሳናደርግ ከኢህአዴግ መሃል የለማ ቡድን ተነስቶ ለአንድነት መንፈስ ቆሟል። ታላቁ «ኢትዮጵያዊ» ዶናልድ ለቪን ደጋግመው እንዳሉት በርካታ እድሎቻችንን አበላሽተናል (https://scholarworks.wmich.edu/ijad/vol1/iss1/3/)። ይህን እድል ደግሞ ካበላሽን ታሪክ ለዘለዓለም ይወቅሰናል።

Monday, 30 July 2018
የብሶት ፖለቲካ
የብሶት (grievance) ፖለቲካ በተማሪዎች ንቅናቄ ዘመን ከ«ጨቛኝ እና ተጨቛኝ» ፖለቲካ አብሮ ወደ ሀገራችን ገብቶ እንሆ ወደ 60 ዓመት ቆይቷል (http://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/02/blog-post_16.html)። ምንድነው የብሶት ፖለቲካ? ባጭሩ በብሶት፤ ንዴት፤ ቂም፤ ጭቆና፤ በደል ዙርያ የተመሰረተ ፖለቲካ ነው። በአሉታ (negativity) የተመሰረተ ፖለቲካ ነው። በሰለባ ወይንም ተጨቛኝ አስተያየት (victim mentality) የተመሰረተ ነው።
የብሶት ፖለቲካ መፈክሮች እንዲህ ናቸው፤
1. ተበድያለሁ ተጨቁኛለሁ (ማንንም በድዬ አላውቅም)
2. በዳዮቼ ሊክሱኝ ይገባል (እኔ ማንንም ልክስ አይገባም)
3. ዛሬ ላለሁበት ሁኔታ እና ችግር ሙሉ ጥፋተና ሃላፊነት የበዳዮቼ ነው (ዛሬ ላለሁበት ሁኔታ እና ችግር እኔ ምንም ሃላፊነት የለብኝም)
4. የበደሌኝን ማጥፋት ቢቻል ለሁላችንም ይበጀን ነበር
5. መበደሌን ያላመነ እንደ በዳይ ይቆጠር ሊወገዝ ሊጨቆን ይገባዋል
የብሶት ፖለቲካ ምንጭ ምንድነው? በመጀመርያ ደረጃ ምንጩ እውነተኛ ብሶት ነው። የሰው ልጅ በተለያየ ምክንያት ብሶት አለው፤ ይህን መካድ አይቻልም። ለምሳሌ ጭሰኛው መሬቱ ከሱ ወይንም ከአባቱ ወይንም ከአያቱ ተወስዶበት መሬቱን ለወሰደው እንዲገብር ተደርጎ ብሶት ይኖረዋል። ተጨቁኛለሁ ቢል ይገበዋል። የቤት ሰራተኛዋ አለአጋባብ ስራ ሲቆለልባት እንደ ባርያ ስትነዳ ቤተ ክርስቲያንም ለመሄድ ሳይፈቀድላት ሲቆይ ብሶት እየተጠራቀምባት ይሄዳል። ኦሮምኛ ተናጋሪው በቋንቋ ሲቀለድበት እንደ ዝቅተኛ ሰው ሲታይ ብሶት ይይዘዋል።
ግን በኢትዮጵያ የነበረው ያለው ብሶት እንደዚህ አይነቱ ብቻ አይደለም። ሁሉም ሰው በተለያዩ መልኩ ብሶት አለበት። በጎረቤት መካከል ግጭት፤ ቅራኔ እና ብሶት አለ። በአለካ እና ሰራተኛ፤ በአዛዥ እና ታዛዥ፤ በባልደረባዎች መካከል፤ በቤተሰብ መካከል (ምናልባትም ይህ ከሁሉም ይበልጣል) ወዘተ። በሰው ልጅ መካከል ግጭት እስካለ ድረስ ብሶት አለ። ግጭት ደግሞ በተለየዩ መልኩ አይቀርም።
ስለዚህ ጥያቄው ይህን የማይቀረውም ብሶት እንዴት ነው የምናክመው ነው። በርግጠኝነት ይህን ብሶት ወደ ፖለቲካ ምድር ማምጣት ብዙ ጊዜ አደገኛ ነው ፍትሃዊም ላይሆን ይችላል። የኃይለ ሥላሴ ተማሪዎች የተመረዙበት የማርክሲስት ኮምዩኒዝም ፖለቲካ ይህን ነው በመጀመርያ ደረጃ ያደረገው። ዓለምን ወደ «ጨቋኝ እና ተጨቋኝ» ከፋፍሎ ብሶትህን ተወጣ የሚል ፖለቲካ ነው። በዳይህን አጥፋው በማለት ነው። ታላቁ የደቡብ አፍሪካ መሪ ኔልሰን ማንዴላ እንዳሉት "dialectical materialism" (የብሶት ወይንም ጨቋኝ ተጨቋኝ ፖለቲካ መሰረት) ለነፃነት ታጋይ እንደ ፈንጅ ነው»። ይህ ማለት ኃይለኛ መሳርያ ነው ችግሩን የሚፈታ ብቻ ሳይሆን ዙርያውን በሙሉ ድምጥማጡን የሚያጠፋ። የፈንጅ ወርዋሪውይንም፤ ጠቅላላ ህብረተሰቡንም፤ ሌሎች ሀገራትም ሊያጠፋ የሚችል መሳርያ ነው! መቆጣጠር የማይቻል መሳርያ ነው። ያለንን ብሶት ወደ ፖለቲካ አምጥተን በጨቛኝ ተጨቛኝ የብሶት ፖለቲካ እናስተናግደው ከሆነ ሁላችንም ፉንጂ አፈነዳን ማለት ነው። ይህን ነው በሀገራችን ባለፉት 40 ዓመታት ያየነው። ሀገራችንን አፈንድደናል።
በሀገራችን ይህ የብሶት ፖለቲካዊ አሰተሳሰብ በመደብ፤ በጎሳ፤ በሃይማኖት ወዘተ ታይቷል። ዛሬም በሚያሳዝን ሁኔታ እየታየ ነው። አሳዛኝ ነው የምልበት ምክንያት ሁለት ነው፤ 1) ውሸት ነው፤ የሰው ልጅ እራሱን በዋናነት «ተበዳይ» ብሎ ከገለጸ ማንነቱን አጥቷል ማለት ነው። የሰው ልጅ ሊበደል ይችላል ገን «ተበዳይ» ማንነቱ ሊሆን አይገባም። 2) ይህ አስተሳሰብ ቅራኔን፤ ግጭት፤ ማፈናቀል፤ ግድያ ወዘተ ያሰፍናል ሀገርን ያፈርሳል እና ታላቅ እልቂት ያመጣል። እንዴት?
በመጀመርያ የብሶት ፖለቲካ ሁሉንም አቅመቢስ እና ተበዳይ ያደርጋል (victim)። ሁሉም ተበድያለሁ ይላል ማንም በደልኹኝ አይልም። ሁሉም ካሳ ይገባኛል ይላል ማንም የሚክስ አይኖርም። ሁሉም መቀየም ይገባኛል ይላል ማንም ይቅርታ አይልም። ሁሉም እራሱን አቅመ ቢስ (disempowered) አድርጎ ይቆጥራል ማንም እራሱን እንደ ጎለበተ (empowered) ሰው አይቆጥርም። ይህ ማለት ሁሉም ፈላጊ ሆኖ ሰጭ ወይም አቅራቢ የለም። ይህ አስተሳሰብ ግጭትን ያሰፍናል። ተበድያለሁ ሲል አዎን ብሎ ይቅርታ የሚለው ሲያጣ፤ ካሳ ይገባኛል ሲል የሚክሰው ሳይኖር፤ ሰለባ ነኝ ሲል ፍትህ ሳያገኝ፤ አቅም የለኝም ሲል የሚያጎለብተው ሳይኖር፤ ይህ መሬት የኔ ነው ሲል ሌላውም የኔ ነው ሲል ወዘተ የብሶት እሽቅድድም እና ግጭት ይሰፍናል።
ላለፉት 27 ዓመት ከኢትዮጵያ የሰፈነው የጎሳ አስተዳደር ይህን ክስተት በደምብ ያንጸባረቃል። ሁሉም ብሄሮች ተበድያለሁ አሉ። ለምሳሌ ኦሮሞ ብሄርተኛው ለ150 ዓመት ተበድያለሁ አሁን ቢሻሻልም ገና ዴሞክራሲ ያስፈልገናል፤ ካሳ ያስፈልገናል፤ ታሪክ መስተካከል አለበት፤ አዲስ አበባ የኛ ናት ወዘተ ይላል። ትግሬ ብሄርተኛውም እስካሁን በኢትዮጵያ የብሄሮች እስር ቤት ታስረን ነበር አሁን ነው ነፃ የወጣነው ግን አሁንም በነፍጠኛ እና ጠባብ እንጠቃለን ይላል። በደርግ እና ኃይለ ሥላሴ ዘመን የደረሰብን በደል ምክንያት ካሳ ያስፈልገናል ይላሉ። አዲሱ አማራ ብሄርተኛውም በአቅሙ ተበድያለሁ ለ27 ምናልባትም ለ40 ዓመት የተለያዩ ብሄሮች ሰለቦች ሆነናል ይላል። የሀገራችን ችግር በሙሉ በኛ ይሳበባል ያላል። ዘራችን እየጠፋ ነው "genocide" በኛ በተለየ መጠን ተፈጽሟል ይላል። ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ነፍጠኛ እያሉ በየ ቦታው ያሳድዱናል ያፈናቅሉናል። ካሳ ይገባናል ይላሉ አማራ ብሄርተኛው።
ግልጽ ነው፤ ሁሉም ተበዳይ በመሆኑ እርስ በርስ ያጋጫል። ለስልጣን፤ ለጥቅም፤ ለመሬት ወዘተ በብሄር ደረጃ ይወዳደራል፤ ይጣላል፤ ይዋጋል፤ ይገዳደላል። የፖለቲካ ውድድሩ በጎሳ እና በብሶት ብቻ የተመሰረተ ነው። እንደዚህ አይነቱ ውድድር ደግሞ ከርዕዮት ዓለም ውድድር ይልቅ ቶሎ ወደ ግጭት እና ጦር ያመራል። እነዚህ ግጭቶች ደግሞ ሀገሪቷን ወደ መፈረካከስ ይወስዳሉ። መረጃውን ላለፉት ቢያንስ 27 ዓመት አይተነዋል። ልደገመው፤ የምለው «ቴኦሪ» አይደለም የብዙ ዓመት ማስረጃ አለን።
መፍትሄው ምንድነው ታድያ? አንዳንድ የጎሳ ብሄርተኞች ይቅርታ ብንጠየቅ፤ ታሪክ ቢስተካከልልን፤ መሬት ቢመለስልን ሁሉም ያበቃል ይላሉ! ግን እንደማይበቃ እናውቃለን፤ የሰው ልጅ አንዴ የሰለባ አስተያየት (victim mentality) ከሰፈነበት ከራሱ ውጭ የሚመጣ ነገር መቼም ከዚህ እስር አስተሳሰብ አይፈታውም። ከውስጡ ከልቡ ብቻ ነው ከሰለባ ወደ አቅም እና ሃላፊነት ያለው ሰው መቀየር የሚችለው። ምንም ይቅርታ እና ካሳ ይህንን ለውጥ ሊያመጣ አይችልም። የልብ ለውጥ ነው የሚያስፈልገው።
ይህንን የልብ ለውጥ እንዴት ይመጣል? ምሳሌ 1። የተበደኩኝ ጭሰኛ ከሆንኩኝ በዳዬን ማጥፋት አይደለም ማሰብ ያለብኝ። መበደሌንም ማቆም አይደለም ማሰብ ያለብኝ። ግቤ መሆን ያለበት ፍትሃዊ የሆነ ኑሮ እና ሁኔታ መፍጠር ነው። ግቤ አሉታዊ ሳይሆን ገምቢ መሆን አለበት። እንዲህ ቢሆን ኖር 40 ዓመት በፊት የጭሰኛ ችግር በ«መሬት ለመንግስት» (አሉታዊ - negative) ሳይሆን በ«መሬት ለአራሹ» (ገምቢ - positive) ይፈታ ነበር። ግን በብሶት ፖለቲካ አሉታዊ አስተሳሰብ ለእውነት የሆኑ ችግሮች የውሸት መፍትሄ ያቀርባል።
ምሳሌ 2። በጎሳ ወይንም ቋንቋ ደረጃ እኔ በቋንቋዬ እና ባህሌ መሰረት ነው መኖር የምፈልገው ከሆነ ያንን ነው ግብ ማድረግ። ሌላውን ጨቋኝ ብሎ መሰየም እና ለማጥፋት መነሳት የብሶት ፖለቲካ አካሄድ ነው። የኦሮሞ ብሄርተኛ ኦሮሚያ ለኦሮሞ የሚለው መፈከር አሉታዊ አካሄድ ነው። ኦሮሚያ ለኦሮሞ ማለት ሌላውን ማስወጣት ወይንም ሁለተኛ ዜጋ ማድረግ ስለሆነ። ሌላውን መጉዳት ስለሆነ። ግን ኦሮምኛ ሀገር ዙርያ ይነገር የሀገር ቋንቋ ይሁን ኦሮሞነታችን ሁሉም ውስጥ ይግባ ማለት ገምቢ የሆነ አመለካከት ነው። የብሶት ሳይሆን የገምቢ ፖለቲካ ነው። ይህ አስተሳሰብ ደግሞ ግጭት ሳይሆን ትብብር የሚጋብዝ ነው።
ስለዚህ ያሉንን በሙሉ ማሀበረሰባዊም ግለሰባዊም ብሶቶች በብሶት ፖለቲካ ሳይሆን በ«ገምቢ ፖለቲካ» ማካሄድ ነው ያለብን። (ጠ/ሚ አብይ «መደመር» ሲሉ ይህን ማለታቸው ይመስለኛል)። የብሶት ፖለቲካ የግጭት እና ህምም ምንጭ በመሆኑ ምክንያት ማስወገድ አለብን። ይህ ማስወገድ የሚጀምረው ከላይም ጠ/ሚ አብይ እንደሚያረጉት ከታችም እኛ ብዙሃን ማደረግ እንዳለብን። ከሁሉም ትምሕርት ደረጃ ይህ የብሶት እና የጨቋኝ ተጨቋኝ አስተሳሰብን አጥፍቶ ወደ ግምቢ አስተሳሰብ መቀየር አለበት። ከአሉታዊ ወደ ገሚቢ መሄድ አለብን። ይህን መልእክት ከሃይማኖት ተቋማትም መንሰራጨት አለበት። የህዝባችን አስተሳሰብ መቀየር አለበት። ወደ ገምቢ ፖለቲካ መምጣት አለብን።

Thursday, 26 July 2018
ጉዞው ረዥም ነው
የዛሬው ግድያ የመጀመርያው አይደለም ግን በቅርብ ስለሆነ የተወሰነ ነፃነት የሰፈነው ስለ በፊቶቹ ገና ብዙ አልሰማንም። እኔ እንደ አብዛኛው ብዙሃን ከመንግስት ነክ ነገር ሩቅ ብሆንም በቅርቤ እንደዚህ አይነት ግድያ አጋጥሞኛል።
ያለፈው ነሐሴ ከጎተራ አዲስ አበባ ያለው ሃለሉያ ሆስፒታል ሆኜ አንድ ሰው እንደዚሁ በታቀደ ግድያ በጥይት ተመትቶ ሆስፒታሉ ገባ። ከተወሰነ ቀን በኋላ ሞተ። ከዘዶቹ እንደሰማሁት ምዋቹ ከኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ከጓደኞቹ ጋር ሆነ ሲመለስ ተኳጾች መቱት አንድ ጓደኛው ተጎድቶ አመለጠ።
ማን ሊገለው ይፈልግ ይሆን ሲባል ሟቹ በሙስና ጉዳይ ለመንግስት አካል መረጃ ሰጥቷል አሁንም ሊሰጥ ነበር አሉ። ቢሆንም ለኔ እንደዚህ አይነት "professional" ግድያ መኖሩ አስገረመኝ ምናልባትም አስደነገጠኝ። ብሀገራችን ያልተለመደ ነው በተለይ ፖለቲከኛ ባልሆነ ሰው ላይ።
ይህ ታሪክ ከዚህ በፊት ስላጋጠመኝ የዛሬው ግድያ በጣም አላስደነገጠኝም። ብዙዎች እንዳሉት ወደሽር ወቅት ገብተን ይሆናል ከዚህ ለመውጣት ጊዜ ይፈጃል። አዲሱ አመራር ስለ ደህንነት ነክ ጉዳዮች ከሁላችንም በላይ አውቂ ስለሆኑ መደረግ ያለበትን አበጥረው የሚያውቁ ይመስለኛል። ማድረግ መቻሉ ግን ሌላ ጉዳይ ነው።
ከኛ ከብዙሀኑ የሚጠበቀው አንድነት ነው። በፊትም ችግራችን አንድ አለመሆን ነው አሁንም እንዲሁ። በፊትም ችግራችን ሳር በመቀንጠስ እርስ በርስ መጣላት ነው አሁንም እንደዚሁ። የተከፋፈለ ቤት ይፈርሳል ወይንም በዚህ ጉዳይ አኳያ ለሽብር የተጋለጠ ነው። ስለዚህ ሰከን ያለ የፖለቲካ አካሄድ ለሁላችንም ይበጃል። እንበርታ፤ ጉዞው ረዥም ነው።
ግን ከሁሉም በላይ ለአቶ ስመኘው ነፍስ ይማር ቤተሰቡን ጽናት ይስጣቸው።

Subscribe to:
Posts (Atom)