Showing posts with label complaining. Show all posts
Showing posts with label complaining. Show all posts

Thursday, 11 April 2019

የምኞት ፖለቲካ ሲቀጥል...

የኢሳት የኤላታዊ ተንታኞች ምኞጣጨው ጥሩ ነው፤ የጎሳ ጥላቻ በሀገራችን ያመጣው አደጋ እንዲቀረፍ ወደ ርዋንዳ መስመር ከመግባታችን በፊት። የባህል እና ቋንቋ ብዙሃነት ያለበት ግን የጎሳ አስተዳደር እና ፖለቲካ የሌለበት ሀገር ነው ምኞታቸው። ጥሩ ምኞት ነው፤ የኔም የብዙዎቻችን ነው።

ግን «ጠ/ሚ አቢይ፤ ጎሰኞቹን በአዋጅ አግታቸው፤ የመንግስት መዋቅርን በሹመት ተቆጣጠር፤ የክልል ጦሮችን በአዋጅ ህገ ወጥ አድርግ፤ ወዘተ» በማለት ይህ ምኞት ሊፈጸም አይችልም። የሀገራችን የፖለቲካ ነባራዊ ሁኔታ ይህን አይፈቅድም። የጎሳ ብሄርተኛ ጎራው የ«ፖለቲካ ኃይል» አለው። ይህ ጎራ የተዋቀረ እና የተቀነባበረ ኃይል፤ በመንግስት መዋቅሮች የተሰገሰገ ኃይል፤ የገንዘብ ኃይል፤ ወዘተ ኃይል አለው። ጠ/ሚ ዓቢይ የእለታዊ ተንታኞች የሰቡትን እርምጃዎች ልውሰድ ካለ የጎሳ ብሄርተኛው ጎራ ቀውስ ያስነሳል። ጠ/ሚ ዓቢይ እንደዚህ አይነት እርምጃዎች ከመውሰዳቸው በፊት በስልት እና ዘዴ የጎሳ ብሄርተኛውን ኃይል ማድከም አለበት። አለበለዛ ነባራዊ ሁኔታን የማይመጥን እርምጃ ይሆናል እና ሁኔታውን ያባብሳል።

የጎሳ ብሄርተኛ ጎራውን ከማድከም እና ማከፋፈል አልፎ ሌላ ዋና እርምጃ ያስፈልጋል፤ ይህ የ«መሃል ፖለቲካው» ወይንም የዜግነት ፖለቲካ ጎራው እጥፍ ድርብ መጠንከር አለበት። ይህ ጎራ መዋቅር፤ ቅንብር፤ የገንዘብ፤ የመንግስት መዋቅር ከውስጥ በኔትወርክ መአስር ኃይል ሊኖረው ይገባል። የዜግነት ፖለቲካ ጎራው እንደዚህ አይነት «የፖለቲካ ኃይል» ሲኖረው የጎሳ ፖለቲካን ለመቀነስ የሚወሰዱ እርምጃዎች ሲወሰዱ የጎሳ ብሄርተኞች የሚነሳውን ሁከቶች መቋቋም ይቻላል። የጠ/ሚ ዓቢይ መንግስት በጎሳ ብሄርተኞች ሲጫን የዜግነት ጎራው ይደፍገዋል። ቀደም ተከተሉ እንዲህ ነው መሆን ያለበት።

ግን አሁን የዜግነት ፖለቲካ ጎራው ገና በቂ አልተደራጀም። ለዚህ ነው የጠ/ሚ ዓቢይ መንግስት አሁንም ከባድ ሁኔታ ውስጥ ያለው። ለዚህ ነው «ከባድ እርምጃ ውሰድ» የሚለው ሃሳብ አጉል ምኞት የሆነው። መጀመርያ የዜግነት ፖለቲካ ጎራው ማለትም «መሃሉ» ጠንክሮ መገኝነት አለበት የጎሳ ብሄርተኞቹን ጫና ለመቋቋም።

ስለዚህ የእለታዊ ተንጣኞች በሙሉ ኃይላቸው ይህ የዜግነት ፖለቲካ ጎራ መደራጀት እና መጠንከር ዋና ተልዕኮአቸው ማድረግ አለባቸው። ለሀገራችን ሰላም ቀድመ ሁኔታ ነው። ማለት ይህ ካልሆነ ምንም አይነት የፖለቲካ መሻሻል ሊመጣ አይችልም።

Wednesday, 10 April 2019

"Make A Wish" Politics

RE: Ethiopia: A Country On The Brink (http://www.ethioreference.com/archives/17240), by Dawit Woldegiorgis.

With respect - and Dawit Woldegiorgis and I are on the same side of course - I cannot fathom how anyone with the least knowledge of politics can consider a transitional government without an opposition to speak of. For me, Ato Dawit's article is a continuation of 27 years of those opposing the TPLF complaining and discussing wild ideas without presenting a viable alternative. Viable.

Today, the only opposition with any real power are the ethnic nationalists (e.g. Qerro). The Ethiopianist opposition has no strong organization and little power. It has little ability to influence, exert soft or hard power, raise funds, mobilize masses, mobilize the elite, enforce its will within government institutions, etc. This weakness of the Ethiopianist political segment is, by the way, the main source of our political problems. PM Abiy Ahmed has to be careful in handling the ethnic nationalists, but he has no Ethiopianist organization to buttress him from the other side. Yes, G7, Addis Ababa,  and others are working on creating strong Ethiopianist organizations, but we are still a long way off. Maybe some months or a year from now, things will be different. But for now, the ethnicists have the upper hand - by far.

A transitional government by definition has to reflect political power, otherwise it cannot govern and enforce its edicts. If for example the EPRDF decides to create a transitional government with equal representation from the ethnic nationalists and the Ethiopianists, the ethnic nationalists can throw a fit and create real, tangible problems, from street riots to using their influence within current government structures to sabotage the transitional government. The Ethiopianist opposition, on the other hand, has no tangible way in which to express it's displeasure. It has no tangible way to project its power. Maybe more articles from the likes of Dawit and me is all it can do. Maybe a street protest that will easily be quashed, as we have little power inside government institutions to prevent this.

This is, by the way, the reason why Ethiopianists and the Amhara, who at the time were all Ethiopianists, were not represented in the transitional government of 1991. We had no real power! In the face of being excluded, we could do nothing except, again complain and write articles. Dawit Woldegiorgis, who was around at that time, ought to remember this well.

Both Ato Dawit's proposals - that Abiy resign and be replaced by someone who will not acquiesce to ethnic nationalists, and that Abiy form a transitional government - assume the existence of an Ethiopianist political segment with real power. Such an Ethiopianist organization does not exist. This is reality. So all the focus should be on strengthening Ethiopianist political institutions. Parties, civic organizations, etc. We need money, people, influence, people within government structures, etc. When this work is completed, then any option, a transitional government or Abiy himself, will have a good outcome.

Friday, 1 March 2019

የአዲስ አበባ ጉዳይ እና የሃላፊነት ፖለቲካ

በተለያዩ ጽሁፎቼ የኢትዮጵያ ፖለቲካ መሰረታዊ ችግር የ«ኢትዮጵያዊነት» ጎራው ለራሱ እጣ ፈንታ ሃላፊነት አለመውሰዱ ነው ብያለሁ። ላለፉት 50 ዓመታት ተደራጅቶ ፍላጎቶቹን አጣርቶ ከማስከበር ይልቅ ህልውናውን ለሌሎች ትቷል። ሃላፊነት ለሌሎች መታው ባህል አድርጎታል። ይህ አካሄድ የ«ለቅሶ ፖለቲካ» ብሄ ሰይምዬዋለሁ (https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/10/blog-post_16.html)።

ይህ ሁኔታ ምክንያት አለው፤ የኢትዮጵያዊነት ጎራው በአብዮቱ ጀምሮ እርስ በርስ ተገዳድሎ ልሂቃኑ እራሱን አጥፍቶ እስካሁን አላገገመም። (https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/10/1.html፤ https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/10/2.html፤ https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/10/3.html፤ https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/10/4.html)። ቢሆንም በዚህ አካሄድ መቀጠል አይቻልም። ሌሎችን «ፍላቶእ እና መብታችንን አስከብሩልን» ብለን እየለመንን መቀጠል አይቻልም።

አሁን የሚያስፈልገን ከ«ለቅሶ ፖለቲካ» ወጥተን፤ ከህጻንነት እና ብሽተኝነት ወትጠን ወደ «ሃላፊነት ፖለቲካ» መግባት አለብን። ግድ ነው፤ አማራጭ የለም። እነ ለማ ይሁን አቢይ ይሁን ህወሓት ይሁን ግንቦት 7 ይሁን አብን ወዘተ እንዲህ አድርጉልን ብለን መለመን አይቻልም። ካሁን በኋላ ሁላችንም «ይህ ይሁን»፤ «ይህ ይደረግ»፤ «እከለ ይውደም» ወዘተ ከማለት ወደ «እኔ ይህን አደርጋለው» የሚለው አመለካከት መግባት አለብን። ልመና በቃ፤ የራሴን እጣ ፈንታ እራሴ ወስነዋለው ወደሚለው መግባት አለብን።

የአዲስ አበባ ጉዳይ የዚህ የአስተሳሰብ እና ተግባር ለውጥ አስፈላጊነት በደምብ ይገልጻል (https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/09/blog-post_97.html)። ልሂቃኖቻችን እስካሁን እነ ኢህአዴግን፤ ህወሓትን፤ ኦዴፓን፤ የኦሮሞ ብሄርተኞችን፤ አዴፓን፤ ጥ/ሚ አቢይን፤ ፕሬዚደንት ለማን፤ ወዘተ እባካችሁ እንዲህ እንዲያ አድርጉ አታድርጉ እያሉ ለው ዓመት ይጮሃሉ። ግን አንድ የሚባል የአዲስ አበባ ህዝብን ጥቅም የሚያንጸባርቅ እና ለማስከበር የሚሯሯት ድርጅት የለም? የአዲስ አበባ ህዝብ ህልውናውን ለሌሎች ሰጥቶ ሌሎቹ የሚፈልጉትን ሲአደርጉ ልሂቃኑ ያለቅሳል! ይህ ምን ማለት ነው? የአዲስ አበባ ህዝብ እራሱን አደራጅቶ ፍላጎቱን እና መብቱን ዘርዝሮ ማስከበር ካልቻለ እነዚህ የማይወክሉት ተቋሞች የፈለጉትን ያደርጋሉ። ይህ እኮ እጅግ basic የሆነ ነገር ነው።

እስከ ዛሬ የኛ ልሂቃን እና ሚዲያ ይህን መሰረታዊ ጉዳይ ትተው በማልቀስ እና መለመን ነው የዋሉት። የራሳችንን ጥፋት (አለመደራጀት) ላለማየት ትብሎ ህልውናችንን አደጋ ውስጥ ከትተናል! ይህ ሁሉ ችግር ስላልተደራጀን ነው እና እንደራጅ ከማለት ሌሎች ስለሚያደርጉት እናለቅሳለን። ይህ ለቅሶ ምንም ለውጥ አላመጣም አያመጣምም። ህዝባችን በንዴት እንዲደራጅ አላደረገም። ይባስ ሌሎች ላይ ጣት በመጠቆም የራሳችንን ጥፋት እንዳናይ ስበብ ሆኖናል። ጉርጓዳችንን ይበልጥ እንድንቆፍር አድርጎናል።

አሁን ግን አንዳንዶች መራራ የሆነውን መድሃኒት ውጠን ወደ ፊት መራመድ እንዳለብን የገባቸው ይመስላል።


ከዚህ ከኢሳት ዝግጅት የአዲስ አበባ ህዝብ መዋናነት መደራጀት አለበት ትባለ። ያለመደራጀታችን ጥፋታችንን አመንን ማለት ነው፤ ይህን ማመን ነው መራራው መድሃኔት። ካመንን በኋላ ሙሉ አቅማችንን ወደ መደራጀት ስራ ማሰለፍ ነው ያለብን። ካሁን ወድያ አንዳች የልሂቃን እና ሚዲያ ደቂቃ በእሮሮ፤ ለቅሶ፤ እና ልመና መጥፋት የለበትም። ሙሉ አቅማችን ወደ መደራጀት።

ምን ማለት ነው የመደራጀት ስራ (https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/10/blog-post_18.html)? ብዙ ሚስጥር የለውም፤ የህዝብ የማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መደራጀት ለሺዎች ዓመታት የተደረገ ነገር ነው። የአዲስ አበባ ህዝብ «የአዲስ አበባ ህዝቦች ድርጅት» ያስፈልገዋል። የዚህ ድርጅት (ድርጅቶች) ተእልኮ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ጥቅም ማስከበር ነው። ቀላል ተእልኮ ነው፤ ሌላ ጣጣ አያስፈልገውም። ድርጅቱ በርካታ (በመቶ ሺዎች የሚቆጠር) አባላት ያስፈልጉታል። ባለ ሃብቱ በደምብ መሳተፍ አለበት። ስብሰባ፤ ሰርቬ፤ ምርጫ፤ ወዘተ የሚያካሄድ መሆን አለበት። አባላቶቹ በየ ማህበራዊ ዘርፍ፤ በየ መስርያቤት፤ በዬ ሰፈሩ የሚሰሩ እና የሚኖሩ መሆን አለባቸው። ድርጅቱ ሰፊ ኔትወርክ ኖሮት «የሚፈራ» ማለትም አቅም ያለው መሆን አለበት። በተለያዩ የከተማው ጉዳዮች፤ መብራት፤ ውሃ፤ መንገድ፤ ደህንነት፤ ጤንነት፤ መፈናቀል፤ ውክልና፤ ወዘተ የሚሰራ መሆን አለበት። በዴሞክራሲያዊ መልኩ የአባላቱን ፍላቶ የሚያውቅ፤ የሚያስከበር እና የሚወክል መሆን አለበት።

ይህ ድርጅት ሲኖር፤ ዛሬ ቢኖር ስለ አዲስ አበባ ያለው ጭቅጭቅ አይኖርም ነበር። ሁሉም ተሳታፊዎች የአዲስ አበባ ህዝብ ፍላጎትን አበጥረው ያውቃሉ። የሁሉም አቋም ሰልሚታወቅ የፖለቲካ ድርድሮች በግልጽ እና በጽጋ ይካሄዱ ነበር። የለገጣፎ ሰዎች አይፈናቀሉም ነበር። ጉዳዩ ገና ሲነሳ ድርጅቱ ተሳትፎበት ድርድር ተደርጎበት በሰላም በሁሉም የሚያስማማ መልኩ ይፈታ ነበር። የኦሮሚያ «ልዩ ጥቅም» ጉዳይም እንዲሁ። ወካይ ድርጅት ቢኖርን «ልዩ ጥቅም» ብለን አናለቅስም ነበር። ድሮውኑ ተደራድረን የልዩ ጥቅም ትርጉም ላይ ተስማምተን ነገሩ በሰላም ይወሰን ነበር። ወዘተ።

የአዲስ አበባ ችግር የመጣው በህወሓት ምክንያት አይደለም። በኦሮሞ ብሄርተኞች ምክንያት አይደለም። መሰረታዊ ችግሩ የአዲስ አበባ ህዝብ እርስ በርስ ተስማምቶ አለመደራጀቱ ነው። ይህን አምነን አንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለቅሶ እና ልመናችንን ትተን ሙሉ አቅማችንን ወደ መደራጀት ማዋል አለብን። አለበለዛ በየበታችንነት እና ተገዥነት ስሜት እንደተገዛን እንቀጥላከን። መገዛት ማለት የራስን እጣ ፈንታ ለሌሎች መተው እና በራስ ህይወት ሃላፊነት አለመውስውድ ነው። ይህ ላለፉት በርካታ ዓመታት ጉዞአችንን ይገልጻል።

Monday, 19 November 2018

በባንክ ዘራፊዎች ሽፍቶች ነበር ሀገራችን የተገዛው

የሃብታሙ አያሌው እና ኤርሚያስ ለገሰ ውይይትን አዳምጡት፤

https://www.youtube.com/watch?v=A78Tet3GCms

አንዱ ከሚወያዩበት ነጥቦች ስለ ኤፎርት (EFFORT) ድርጅት ነው። ሁላችንም የምናውቀው የህወሃት መንግስትን ከመቆጣጠሩ በፊት ሃብት በመዝረፍ ነበር የሚያካመቸው። የእርዳታ እህል/መድሃኔት ወዘተ በመሸጥ፤ ባንክ በመዝረፍ ወዘተ። ደምበኛ የሽፍታ ስራ። ሁላችንም የምናውቀው ታሪክ ነው። አልፎ ተርፎ የሚደንቅ ታሪክም አይደልም ህወሓት በመሰረቱ ሽፍቶች ነበሩና።

ይህን ብለን ጉዳዩ ከሌላው ዝርፊያ እና ሙስና ክስተቶች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው ብሎ መደምደም በቂ አይደለም! ይህ የውሸት ወይንም የማይበቃ መደምደምያ ነው።

ለኔ ዋናው መደምደምያ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጥቂት ሽፍቶች ለ27 ዓመት ተገዝቶ ነበር ነው! ይህ እውነት በመጀመርያ ደረጃ የሚያስከሥሠው እኛን ነው! እንዴት ነው በነዚህ ትንሽ ቁጥር ያላቸው ሽፍቶች የተገዛነው የሚለውን ጥያቄ መመለስ አለብን። ይህን ጥያቄ ካልመለስን ወደ ፊት ይህ መትፎ ታሪካችንን እንደግማለን።

ጣት መጠቆም ብቻ ያብቃ። እንደገና እንዳንወድቅ እራሳችን ላይ ስራ እንስራ።

Tuesday, 16 October 2018

የለቅሶ ፖለቲካ አሳፋሪ ነው፤ ያብቃ!

ኢሳት ለበርካታ ስዓት ስለ የታፈሱ የአዲስ አበባ «ወጣቶች» ዜና እና አስተያየት እያቀረበ ነው (https://www.youtube.com/watch?v=4KugoBLSfFY)።

እኔ እስካየሁት ድረስ ኢሳት አንዲት ደቂቃ ስለ መሰረታዊ ችግሩ ውይይት አላቀረበም። መሰረታዊ ችግሩ የአዲስ አበባ ህዝብ እና በመላው ኢትዮጵያ በኢትዮጵያዊነት የምናምነው የኢትዮጵያ ብሄርተኞች በበቂ ደረጃ አለመደራጀታችን ነው።

አስቡት… የአምስት ሚሊዮን ህዝብ ከተማ አንዳች ይሄ ነው የሚባል ህዝብ ወኪል ተቋም የለውም! ይህ ነው ጉዱ።

ይህን ጉድ አምነን ወደ መፍትሄ ከመሄድ ወደ መደራጀት ከመሄድ ጊዜአችንን «በለቅሶ ፖለቲካ» እናጠፋለን። እንደ ክብር የሌለን ሰዎች የራሳችን ገበና ሳናስተካክል ሌሎችን «አትግዱን» ብለን 24 ሰዓት እንለምናለን። በራሳችን ድክመት ስለምናፍር ይመስለኛል ሁል ጊዜ ጣታችንን ወደ ሌሎች የምንጠቁመው። እነሱ ደግሞ እኛ እራሳችንን ካላልጎለበትን ምንም አያደርጉልንም።

አንድ ምሁራን እንዲህ ብልዋል፤  “When people realize things are going wrong, there are two questions they can ask. One is, ‘What did we do wrong?’ and the other is, ‘Who did this to us?’ The latter leads to conspiracy theories and paranoia. The first question leads to another line of thinking: ‘How do we put it right?’”

የኛ የኢትዮጵያ ብሄርተኞች ምሁራን እና ልሂቃን አሁንም «ማን ነው የሚያጠቃን» የሚለው ላይ ነን። በጃንሆይ ዘመን በ«አለመተባበር ብሽታችን» ምክንያት በየቀኑ ለዳኝነት ወደ ጃንሆይ እንሄድ ነበር። ከዛ አድሃሪ/ተራማጅ እየተባባልን ተገዳደልን። የተረፉት «አድሃሪዎቹም» ኢዲዩ መስርተው አብሮ መስራት አቅቷቸው ፈራረሱ። ማርክሲስቶቹ ከመተባበር እርስ በርስ ተፋጁ። ኢህአዴግ ስልጣን ሲይዝ እራሳችንን «ተቃዋሚ» ብለን ሰይመን ይሄ ነው የሚባል ተቋም ማደራጀት አቃተን። ወዘተ። የኢትዮጵያ ብሄርተኞች ደጋግሞ መውደቅ ረዥም ታሪክ ነው። ግን አሁንም ይህን ድምከት ላይ ከማተኮር ይልቅ ሌሎችን እባካችሁን አድኑን ብለን እንለምናለን!

Thursday, 11 October 2018

መልዕክት ለኢሳቶች…

አቤቱታ፤ ማማረር፤ ማልቀስ፤ complaining ህዝብን ተስፋ እንዲቆርት ያደርጋል። ይህ ከኢሳት ተዕልኮ የሚጻረር ነው።

እንደ አንድ ተራ ዜጋ ምክሬ እንዲህ ነው፤ ስለ ችግሮች ለ10 ደቂቃ ካወራችሁ ስለ መፍትሄ እና አማራጭ መንገዶች ለ20 ደቂቃ ተወያዩ። አዋጪው መንገድ ይህ ይመስለኛል።