እኛ ኢትዮጵያ ብሄርተኞች ለ27 ዓመት ወያኔን ከመውቀስ ሌላ ስራ ባለመስራታችን የወያኔን ለሩብ ክፍለ ዘመን እንዲገዛ አደረግን። በቂ ጸረ-ወያኔ ፕሮፓጋንዳ ካሰራጨን ህዝቡ በአመጽ ይነሳል ብለን ገምተን ይሆናል ግን አልሆነም። በመጨረሻ አመጹን ያስነሳው ህዝቡ በእውን የትግሬ አድሎ በዝቶበት ነው። የትግሬ አድሎ አለ ብሎ በነ ኢሳት ስለተነገረ ሳይሆን ህዝቡ በለት ኑሮው ስላየው ነው (https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2016/10/ethnic-federalism-kills-meles.html)።
ስለዚህ የወሬ ፖለቲካ እንደማይሰራ የ27 ዓመት ማስረጃ አለን። እኛ ኢትዮጵያ ብሄርተኞች 100% ጊዜአችንን ስለ ወያኔ በማልቀስ ከማዋል ፋንታ 50%ኡን ህዝብ እና ልሂቃንን በማደራጀት ብናውለው የት ደርሰን ነበር።
አሁንም አንዳንድ ጓዶቻችን የወሬ ዘመቻ በጎሳ ብሄርተኞች እና አሁን በ ጠ/ሚ አቢይ ማካሄድ ጠቃሚ ይመስላቸዋል። የድሮውን ስህተት መድገም። ለ27 ዓመት ያልሰርዋን መቀጠል። ምን ማለት ነው የማይሰራን ነገር መደጋገም?
ምን አልባት ውስጣችን ማደራጀት እና ሌሎች የእውነት የፖለቲካ ስራዎች ከባድ እንደሆኑ ስለምናውቅ ወሬ ላይ በማተኮር ማምለጥ እንፈልግ ይሆን። ወይንም ሻዕብያ እና ህወሓት ግዙፍ በህዝባቸው ጽናት ግዙፍ ድርጅቶች ሆነው ሲገኙ እኛ ኢትዮጵያ ብሄርተኞች የነሱን 1% የሚያክል ድርጅት መመስራት ስላቃተን አፍረን ይህንን ላለማየት ይሆን ወደ ወሬ ፖለቲካ የምንሸሸው። የዝቅተኛ ስሜት አድሮብን ይሆን 6% ድጋፍ ያለው ወያኔ ለ27 ዓመት ሲገዛን አንድ ጠንካራ ድርጅት መፍጠር ባለመቻላችን?
ምክንያቱ ምንም ቢሆን የወረ ፖለቲካ አይሰራም እና ካሁኑኑ አቅማችንን ከዛ ወደ ከባድ ስራው ወደ መደራጀት ማሸጋሸግ አለብን። ይህ ማለት ካሁን ወድያ ወሬ ሳይሆን ስራ መስራት። መሳደብ ሳይሆን ብልጥ ሆኖ ትብብሮችን መፍጠር ለጊዜውም ቢሆን እስከንደራጅ። ድልዲዮችን ከማቃጠል መጠቀም። እንደ ጠ/ሚ አቢይ አይነቱን ከማራቅ ማቀፍ እና መጠቀም። ይህ ነው ፖለቲካ። እንጂ ዝም ብሎ ማውራት መገዛት ማለት ነው።
የሰላም ክፍሌ ይትባረክ ብሎግ፤ ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለኝን ትናንሽ ሀሳቦች በትህትና አቀርባለሁ። ለስሕተቶቼም በቅድሚያ ይቅርታ እጠይቃለሁ
Showing posts with label grievance. Show all posts

Friday, 19 October 2018
Monday, 20 August 2018
ከሰው ማንነት ጋር መከራከር ያስቸግራል
ድሮ ከኤርትራዊያን፤ ትግራይ፤ ኦሮሞ ብሄርተኞች ጋር ስንከራከር እንዲህ አይነቱ ነጥቦችን እናነሳ ነበር፤
እነዚህን አይነት ፍሬአማ ነጥቦች ላይ ከተወያየን ብኋላ ሁልጊዜ መጨረሻ ላይ ወደ አንድ ነጥብ እንመለሳለን። ኤርትራዊያኖች «እኛ ኤርትራዊያን ነን ኢትዮጵያዊ አይደለንም» ትግራዮውቹ «እኛ መጀመርያ ትግራይ ነን» ኦሮሞ ብሄርተኞች «እኛ ኦሮሞ ነን ኢትዮጵያዊ አይደለንም» ብለው ውይይታችንን ያቆማሉ። የአባባላቸው ትርጉም ግልጽ ነበር፤ ማንነታችን ይህ ነው እና ስለ ማንነታችን ምንም ማለት አይቻልም ነው። ጉዳዩ ሌላ አይደለም፤ ጥቅም እና ጉዳትም አይደለም፤ «ማንነት» ነው።
እንዲሁም አሁን ከአማራ ብሄርተኝነት ደጋፊዎች ይህንን ነው የማየው። ባለፉት 45 ዓመት የፖለቲካ ችግሮቻች (http://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/07/blog-post_15.html) ምክንያት የተወሰነው የአማራ ህብረተሰብ ውስጥ አዲስ የአማራ ማንነት (http://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/08/blog-post_17.html) ተፈጥሯል። ይህ ማንነት የአማራ ብሄርተኝነት ንቅናቄ መሪ @ የጻፉት በደምብ የሚገልጸው ይመስለኛል፤
«አማራ ነኝ ፣ አማራ ነን ፤ እንደአማራነት የተሰነዘረብኝን ጥቃት በአማራነት ተደራጅቼ እመክታለሁ ፤ በዚህም ህልዉናዬን፣ ፍላጎቶቸንና ዘላቂ ጥቅሞችን አስከብራለሁ»
(https://www.facebook.com/photo.php?fbid=1934811083224914&set=a.308423195863719&type=3)
ጉዳዩ የማንነት ስለሆነ ምንም አይነት «ሎጂካል» ሙግት ማንነትን እንደሚያጣጥል ሊቆተር ይችላል። ውይይት ቶሎ ወደ ቅራኔ ይወሰዳል። ለምሳሌ እንደ እኔ አይነቱ በኢትዮጵያዊነት መደራጀትን የሚያምን «የአማራ ጥቅምን የሚያሟላው በኢትዮጵያዊነት መደራጀት ነው» ብል ለአማራ ብሄርተኛው ማንነቱን የተቸትኩኝ ይመስለዋል እና መልሱ ከጉዳዩ ጋር ሳይሆን ከማንነቱን መከላከል ጋር የተያያዘ ይሆናል። «ይህን ሁሉ ጥቃት ደርሶብን እንዴት በአማራነት አትደራጁ ትላለህ» ይባላል። «ድሮስ እናንተ በኛ ትነግዱ ትጫወቱ ነበር አህን ያበቃል» ይባላል። «ሌሎች የጎሳ ብሄርተኞችን ለምን አትተቹም?» ይባላል። ወዘተ።
የነ ጃንሆይ፤ ደርግ፤ ኢህአፓ፤ መኢሶን፤ መላው አማራ/ኢትዮጵያ፤ ቅንጅት፤ ግንቦት ሰባት ወዘተ ኃጢአቶች በሙሉ በ«አንድነት ድርጅቶች» እና በ«ኢትዮጵያዊነት» ርዕዮተ ዓለም ላይ ይለጠፋሉ! ይህ ሁሉ የማይሆኑ («ኢሎጊካል») መልሶች የሚሰነዘሩት ጉዳዩ በዋናነት የማንነት ስለሆነ ነው።
አንዴ በበሶት እና «ጭቁንነት» የተመሰረተ ማንነት ስር ከሰደደ በሎጂክ የተመሰረተ ሙግት ምንም መቀየር አይቻልም። ወይ ከነሱ ጋር ነህ ወይንም ጠላት ነህ።
እዚህ ላይ አንድ መናገር የምፈልገው ነገር አለ። በነዚህ የአማራ ብሄርተኞች ምንም ምንም አልፈርድም። ያወረስናቸው ኢትዮጵያ እጅግ ህመምተኛ እና ደካማ ናት (አሁንም እንዳ አብይ አህመድ አይነት ጀግና መውለድ ብትችልም)። ያወረስናቸው የፖለቲካ ባህል ጥላቻ የቶሞለው ስልት-ቢስ የሆነ ነው። በጃንሆይ ዘመን በሰላም ነገሮችን ከማስተካከል ሀገሪቷን ወደ ገደል ወሰድናት (http://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/07/blog-post_15.html)። ለዚህ ማንም ላይ ጣቴን አልጠቁምም። እንደ በኢትዮጵያዊነት የሚያምን ኢትዮጵያዊ ብሄርተኛ የኔ ጥፋት ነው ብዬ ሃላፊነት እወስዳለሁ። ይቅርታም እተይቃለሁ።
ይህን ካልኩኝ በኋላ የአማራ ብሄርተኞችን እንደ ኦርሞ ብሄርተኞች ተጠንቅቆ መያዝ ያስፈልጋል እላለው። እርግጥ የአማራ ብሄርተኞች በአብዛኛው በጎሳ ብሄርተኝነት አናምንም ስትራቴጂ ነው ወይንም ሌሎቹ በጎሳ ስለተደራጁ ግዴታ ሆኖብን ነው ይላሉ። በኢትዮጵያዊነት እናምናለን ይላሉ። ነገ ህገ መንግስቱ ቢቀየር እኛም በጎሳችን መደራጀት እናቆማለን ይላሉ። አቃፊ ብሄርተኞች ነን ይላሉ።
ሆኖም የጎሳ ማንነት በደምብ ገብቶባቸዋል። መጀመርያ አማራ ነን ቀጥሎ ኢትዮጵያዊ የሚሉ አሉ። ኢትዮጵያዊነት ጠፍቷል የሚሉ አሉ። አንቀጽ 39 ጥሩ ነው የሚሉ አሉ። በመታወቅያ ላይ ጎሳ ቢኖር ጥሩ ነው የሚሉ አሉ። አማራ ብሄርተኛ ያልሆነ አማራ አይደለም የሚሉ አሉ። ወዘተ።
ስለዚህ ይህን ማንነት በዘዴ መያዝ ይኖርብናል። ከሙግት ይልቅ empathy ወይን መቆርቆር ነው የሚያስፈልገው። ከሙግት በፊት መተማመንን መፍጠር ያስፈልጋል (አንድ የሆንን እና የምንተማመን መስሎኝ ነበር ግን ለካ የማላውቀው ብዙ ግጭት እና ቁስል አለ በአምራ ብሄርተኞች እና «አንድነት ኃይሎች»)። ትክክለኛ መተማመን ጋር ከደረስን በኋላ ብቻ ነው ወደ ውይይት እና ሙግት መግባት ያሚቻለው።
የ27 ዓመት ጥቃትን አናጣጥል። የብዙ አማራ «ሞራል» ተሰብሯል። ጥቂት ትግሬ ገዝቶን ነበር ብለው የሚያስቡ ብዙ አሉ። ትክክለኛውን ሚዛናዊውን ግንዛቤ ላይ ከመድረስ በራስ አለመተማመን እና የ«ጭቁን» ስሜት ብዙዎቻችን ላይ አድሯል። ይህን እኔ በበኩሌ አልተገነዘብኩትም ነበር። ምን ያህል ስር እንደሰደደ አልገብኛም ነበር። ድሮ ኩሩ የነበረው አማራ ምን ያህል ሞራሉ እንደተጎዳ እና ወደ ጎሳ ብሄርተኝነት ማዘንበል እንደሚችል አልገባኝም ነበር። አሁን ግን ትንሽ የገባኝ ይመስለኛል። ከተሳሳትኩኝ አርሙኝ።
- ሁላችንም ኢትዮጵያዊ ነን ማንም ከማንም በላይ አልተጠቀመም አልተጨቆነም
- መንግስት በጎሳ ወይም ብሄር አድሎ አድርጎ አያውቅም
- ከሁሉም ጎሳ የፖለቲካ መሪዎች አሉ ታላላቅ መሪዎቻችን ብዙ የተለያየ የጎሳ ደም አላቸው
- የሁላችንም ጥቅም አብሮ ከመሆን የተያያዘ ነው
- ጎሰኝነት የጋራችንንም የያንዳንድ ጎሳችንንም ጥቅም ይጎዳል ግጭት እንዲሰፍን ያደርጋል
ወዘተ

Subscribe to:
Posts (Atom)