ስለ ዴሞክራሲ ብዙ ተጽፏል። በንደፈ ሐሳቡ ደረጃ ምንም መጨመር አልፈልግም። በዚህ ጽሁፍ አሁን ባለን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳይ ዙርያ ስለ«ዴሞክራሲ» ያለን አመለካከት ምን ቢሆን ይበጀናል የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ነው የምወደው።
እንደ እስክንድር ነጋ አይነቶቹ በርካታ (ጀግና) የነፃነት ታጋዮቻችን የችግራችን መፍትሄ ዴሞክራሲ ነው ይላሉ። በአንድ ወቅት እኔም እንደዚሁ ይመስለኝ ነበር። ግን ጉዳይ ከዛ እጅግ ውስብስብ እንደሆነ ተረድችያለሁ።
ዛሬ ባለን ህገ መንግስትና ጠቅላላ የመንግስታዊ አወቃቀር የነፃ ምርጫ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ቢካሄድ ችግሮቻችን ይፈታሉ ብለን እንገመታለን? አሸናፊዎቹ፤ ተሸናፊዎቹ፤ ጦር ሰራዊቱ፤ የክልል መንግስታት ወዘተ ውጤቱን ተቅብለው ተስማምተው ይሰራሉ ብለን መገመት ኢንችላለን? አዲሱም መንግስት ሰላምና ፍትህ ያመጣል ወይም የፓርላማ ስልጣንና ኃይሉን ተጠቅሞ ግፍና ጭቆና ያሰፍን ይሆን? ህገ መንግስቱን ይቀየር የምንለውሳ? በቂ ድምጽ ካለን አናሳ ድምጽ ያላቸውን የራሳችሁ ጉዳይ ብለን በዚህ ድምጽ ኃይል እንቀይረውና አዲስ ህገ መንግስት እንጭንባቸው ይሆን? ዛሬ እነዚህ አይነቶቹ ከባድ ጥያቄዎች ጥሩና የተሟላ መልስ አላቸው ብዬ እርግጠኛ መሆን አልችልም። ለእነዚህ ጥያቄዎች በሚገባው መልስ ሳይኖረን ወደ ዴሞክራሲ የምንለው ምርጫ ከገባን ደግሞ አደጋ ነው የሚሆነው።
ስለዚህ እንደኔ እንደኔ በመጀመርያ ሰፊ ውይይት በተለያዩ ደረጃዎች ያስፈልጋሉ። የዚህ ውይይት ግብ በርካታ ባለጉዳዮቹ ከብዙሃን እስከ ልሂቃን የአገራችን ማንነትና ፖለቲካ ምን መምሰል አለበት በሚለው ጥያቄና መልስ አንድ ገጽ ላይ እንዲሆኑ ነው። ሰፊ ስምምነት እንድውል ነው። አሁን ያለንበት ደረጃ አገር መገንባት ላይ ነው። በህዝቡም በልሂቃኑም የፖለቲካ መተማመንና መሰረታዊ ስምምነት የለምና። ከላይ የጠቀስኳቸው አይነቶች መሰረታዊ የሆኑ ጥያቄዎች እንኳን ሊመለሱ አልተጠየቁም አልተወያየንባቸውም። ይህን የውይይት ሂደት ሳንጨርስና መሰረታዊ ስምምነት ላይ ሳንደርስ ወደ ምርጫ መሄድ አደገኛ ይመስለኛል። እንደ ግብጽ፤ ኢራቅ፤ እና ሌሎች ምርጫ ያላቸው ወይም የነበራቸው ግን ሰላምና ፍትህ የሌላቸው አገሮች እንድንሆን አይፈለግምና።
እሺ፤ በርካታና አስፈላጊዎቹ ባለጉዳዮች አንድ ገጽ ላይ መሆናቸውና ስምምነት ላይ መድረሳቸው እንዴት ልናውቅ እንችላለን? አንዱ ዋና ምልክት የሚመስለኝ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በስል ማለት ነው። ጠንከር ያለ ተቃዋሚ ፓርቲ ከሌለ ወይም ፓርቲዎቹ በጎሳ ብቻ የተመሰረቱ ከሆነ ይህ ጥሩ ምልክት አይመስለኝም። ተመሳሳይ የሆኑ አቋም ያላቸው ተቃዋሚዎች የመዋኸድን ሂደት ለማሟለት ብቃት ከሌላቸው ጥሩ ምልክት አይሆንም። ይህን ያልቻሉ እንዴት አብረው መንግስት ይሆናሉ ወይም እንዴት የአስተዳደሩን ህግ ያከብራሉ? የጎሳ ፓሪቲ ብቻ ካለ ደግሞ እንዴት ነው ፖለቲካ ስረአቱ የማይቀረውን የጎሳ ውድድሩን በሰላም ማስተናገድ የሚችለው? አሁንም ከባድ ጥያቄዎች። እንደምናየው ወደ ምርጫ ከመግባታችን በፊት ብዙ ስራ አለ ቀድመሁኔታዎችም መሟላት አለባቸው።
ይህን ካልኩኝ በኋላ እስቲ ይህን ጥያቄ ልጠይቃችሁ፤ ዴሞክራሲ ቢኖር ሰላምና ፍትህ ይኖራል ማለት ነው? እስቲ አንድ አንድ እውነታዎች እንመልከት። በዓለም ታላቅ የሚባለው ዴሞክራሲ አሜሪካ ነው። በጦሩ ኃይል በርካታ የዴሞክራሲ አገርዎች በሰላም እጠብቃለሁ እሸከማለሁ ባይ ነው። ግን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ አሜሪካ ወደ 20 ሚሊዮን ሰዎች በተለያዩ ጦርነቶች ገድሏል ይባላል። አጭር ትዝታ ያለን መቼም ስለ ኢራቅ፤ ሊብያ፤ ሶርያ እናውቃለን። ኢህአዴግ ከዚህ ጋር ሲወዳደር መለአክ ነው ማለት ይቻላል! ግን አሜሪካ ለኑሮ ጥሩ አገር ነው። ገንዘብ አለ፤ ከሞላ ጎደል ፍትህ አለ፤ የተወሰነ ነፃነት አለ። ሁላችንም ወደዛ ለመሄድ እንሻለን። ግን ገንዘቡ ባይኖር በአሜሪካ ምን ይሆን ነበር?
ምናልባት አውሮፓ ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን ለምን አሜሪካን እንደ ምሳሌ ትጠቀማለህ ትሉ ይሆናል። ሰላማዊዋ ስዊድንሳ? እውንቱን ለመናገር የስዊድን የጦር መሳርያዎች በዓለም ዙርያ ምን ያህል ሰው እንደተገደለ የተቆጠረ አይመስለኝም። ግን ትንሽ አይመስለኝም። ደግሞ ከሳውዲ አራቢያ ያላቸው ጓደኝነታቸው እንዴት ፍቅር የተሞላ ነው?!
ዴሞክራሲ ለሰላምና ፍትህ ሊበጅ ይችላል፤ ይህ ጥያቄ የለውም። ግን ሰላምንና ፍትህን ለማስፈን ሥርዓቱ በራሱ አይበቃም። ብዙሃኑም ልሂቃኑም ቀድሞ በትወሰኑ መሰረታዊ ጉዳዮችና አስተሳሰብ መስማማት አለባቸው። ከህግና የሂደት ደምብ አስተሳሰብ ይቀድማል። አሰተሳሰቡ ካለ ህጉ ይመጣል በሚገባውም ይተገበራል። ህጉ ካለን አስተሳሰቡ ከሌለ ዋጋ የለውም። ብዙ ነገር በጽሁፍ ላይ የዋለ ህገ ደምቦች ሊካታቱ ይችላሉ ግን አስተሳሰብ በጽሁፍ ሳይሆን በልብ ውስጥ የሚሰክን ባህል ነው መሆን ያለበት። ከዛ በኋላ እንቅፋት ሲያጋጥም ይህ አስተሳሰብ፤ ስምምነትና አንድነት ናቸው ከወረቀት ላይ ከሰፈረው ህግ ይልቅ ወደ መፍትሄ የሚመሩን።
ስለዚህ ዴሞክራሲን እንደ ዋና ግብ ወይንም እንደ ጣዖት አንመልከተው። ዋናው ግብ ፍቅር፤ ሰላምና ፍትህ ነው። እነዚህ እንዲሰፍኑ ዴሞክራሲ አንዱ መሳርያ ሊሆን ይችላል። በዴሞክርሲ ዘንድ ፍቅር፤ ሰላምና ፍትህ ሊሰፍኑ ይችላሉ። ግን ቀድሞ ዝግጅቶች ካልተደረጉ፤ ግባችን እነዚህ እንደሆኑና ዴሞክራሲ መንገድ ወይም ሂደት ባቻ እንደሆነ ካልተረዳን ፍቅር፤ ሰላምና ፍትህ የሌለው ዴሞክራሲ ሊሰፍን ይችላል። እንደዚህ አይነቱ ዴሞክራሲ ደግሞ በበርካታ አገራት ልምድ እንደምናየው አይበጅም።
የሰላም ክፍሌ ይትባረክ ብሎግ፤ ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለኝን ትናንሽ ሀሳቦች በትህትና አቀርባለሁ። ለስሕተቶቼም በቅድሚያ ይቅርታ እጠይቃለሁ
Showing posts with label መተማመን. Show all posts

Thursday, 8 March 2018
Tuesday, 20 February 2018
ታሪክን አንድገም፤ ሀገርን እንገንባ
አሳፋሪና አገር አፍራሽ ታሪካችንን እንዳንደግም ነው ይህን ጽሁፍ የምጽፈው። ታሪክ እንደመዘገበው ከኢህአዴግ ውጭ ያለነው ምሁራን፤ ፖለቲከኞችና ብዙሃን በፖለቲካ ረገድ ቁም ነገር ለማድረግ እድል ባጋጠመን ቁጥር እልዳችንን አበላሽተናል። በተደጋጋሚ ጊዜ ለአገራችን የፖለቲካ መስተካከል ከኢህአዴግም ይበልጥ እንቅፋት ሆነን ተገኝተናል። ይህን ደፍሬ መናገር የምችል ይመስለኛል።
አንዱ የድክመታችን ምክንያት ተልዕኮአችንን አለማወቃችን ወይም መርሳታችን ነው። ተልዕኮአችን የአገር ፖለቲካ ግንባታ ነው እንጂ የፖለቲካ ውድድር አይደለም። የአገር ፖለቲካ ስርዓት ግንባታ ሲባል ሁላችንም ስለ ህገ መንግስትን ማርቀቅ ነው የምናስበው። ግን ከዚህ ህገ መንግስት ማርቀቅ ስራ በፊት የልብ ለልብ መተዋወቅ፤ በተወሰነ ደረጃ መተማመን፤ መግባባትና መስማማት ያስፈልጋል። እነዚህ ለአገር ግንባታ የፖለቲካ ድርድር ቀድሞ ሁኔታዎች ናቸውና። አለነዚህ ማንኛውም በወረቀት ያለ ህግ፤ ምንም አይነት ወርቅ የሆነ ህግ ቢሆነም፤ በስራ ሊተገበር አይችልም።
ቀጥሎ በነዚህ ተመስርቶ ህገ መንግስትና ሌሎች የርዓይና የህግ ሰነዶች ይደነገጋሉ። ቅራኔ ወይም አለመግባባት ካለ በህግ መሰረት ይፈታል ህጉ ደግሞ በቂ ካልሆነ ያለው መተማንና ስምምነት ለፍትህ ይረዳል። የአገር የፖለቲካ ግንባታ ሂደት እንደዚህ ነው መሆን ያለበት።
የፖለቲካ ውድድር ደግሞ የሚጀምረው የፖለቲካ ስረዓቱ ከተዋቀረ በኋላ የሚመጣው የፖለቲከኞችና ሌሎች ለመሪነት እርስ በርስ በህጉ መሰረት መወዳደር ነው። በምእራብ «ዴሞክራሲዎች» እንደዚህ አይነቱ ውድድር በርካታ ክርክር፤ ክስ፤ ዘለፋም ወዘተ ያካትታል። የህጉን ገደብ ዳር ዳር እየነኩ ግን ሳያልፉ እነዚህን አይንቶች ባህሪዎችን ያንጸባርቃሉ። ይህ ስልጣን ለመያዝ ሊበጃቸው ይችላል ግን ምንም አይገነባም። እርግጥ መተማመንንና ውይይትን ይጎዳል ግን ከምርጫው በኋላ የደረሰውን ጉዳት ይጠግኑና የአገር ማስተዳደር ስረአቸውን ይጀምራሉ። ይህ ነው በተለምደው የምናውቀው የፖለቲካ ውድድር።
የፖለቲካ ውድድር ደግሞ የፖለቲካ ስርዓቱ ከተዋቀረ በኋላ የሚከተለው የፖለቲከኞችና ሌሎች ለመሪነት እርስ በርስ በህጉ መሰረት መወዳደር ነው። በምእራብ «ዴሞክራሲዎች» እንደዚህ አይነቱ ውድድር በርካታ ክርክር፤ ክስ፤ ዘለፋ ወዘተ ያካትታል። የህጉን ገደብ ዳር ዳር እየነኩ ግን ሳያልፉ እነዚህን አይንቶች ባህሪዎችን እያንጸባርቁ ይወዳደራሉ። ይህ ስልጣን ለመያዝ ሊበጃቸው ይችል ይሆናል ግን አገርን አይገነባም ይጎዳልም። ሰልዚህም ነው ውድድሩ ምርጫው ካለፈ አሸናፊዎቹ ውድድሩ ያደረሰውን ንዴት፤ ቂምና ጉዳት ይጠግን ዘንድ ትሸናፊዎቹንም መላው የአገሪቷን ህዝብ አንድ የሚያረግ እርቃዊ ንግግርና ተግባር የሚአደርጉት። ይህ ነው በተለምዶ የምናውቀው የፖለቲካ ውድድር።
ስለዚህ አገርን መገንባትና የፖለቲካ ውድድር የተለያዩ ባህሪያት፤ ተግባራትና ልምድ ያስፈልጋቸዋል። የአገር ግንባታ ሂደት እንደ መተማመን፤ ስምምነት፤ አንድነት፤ መግባባት፤ ህብረት፤ ቅራኔን መፍታት፤ ውይይት ወዘተ አይነቱ ባህሪያትና ልምዶች ያስፈልጉታል። የፖለቲካ ውድድር ግን ክርክር፤ ውድድር፤ ፉክክር፤ መካሰስ፤ ህግና ስረዓትን ዳር ዳሩን መጣስ፤ ወዘተ አይነቱን ልምዶች ያካትታል። በአገር ግንባታ ሂደት መካከል እነዚህን የፖለቲካ ውድድር ባህሪያትና ልምዶች ይዘን ከገባን አገርን መገንባት ሳይሆን ማፍረ ነው የምናደርገው።
ለዚህ ደግሞ በርካታ ታሪካዊ ምሳሌዎች አሉን። እስቲ ወደ 15 ዓመታት ወደ ኋላ ተመልሰን የ«ተቃዋሚ» ምሁራን፤ ጋዜጠኛና ፖለቲከኞች እያደረጉ፤ እየተናገሩ፤ እየጻፉ ምን እንደነበር እናስታውስ። ስራቸውን ባጭሩ ለመግለጽ «እርስ በርስ መበላላት» ማለት ይቻላል! ተቃዋሚዎች ኢህአዴግ ከሚተቹት ይበልጥ እርስ በርስ ነበር የሚፋጁት። ጋዜጣ ላይ ቁም ነገር ሳይሆን ስድብና የመንደር ወሬ ነበር የሰፈነው። ከሞላ ጎደል ስራቸው 90% አፍራሽ 10% ገምቢ ነበር። ስለዚህም ነው ተቃዋሚው ጎራ ምርጫ '97 በግንቦት ሆኖ እሰከ የካቲት አካባቢ የትብብር መዋቅሮች ያላደራጀው! ለዚህም ነው ከምርጫው በኋላ ተቃዋሚዎች በቀላሉ የተበታተኑት። በበፊቱ ዓመታት እዱሉ እያለን ቅስ ብለን በትብብር ጉዳይ ተወያይቶ ትብብርን ከመፈጸምና ጠንካራ መሰረት የሆነ መዋቅርን ከመገንበት እንደ ምርጫ ተዋዳዳሪዎች እየተሰዳደብን ዋልን። ችግር ሲመጣ ለመቋቋም አቅሙ አልነበረንም። እርስ በርስ ተፋጅተን አለቅን። የግንባታ ስራ ያልተሰራባቸው ቅንጅትና ህብረት በቀላሉ ፈረሱ። የፖለቲካ መዋቅር ግንባታንና የፖለቲካ ውድድርን መለየት ያልቻሉትም ከፖለቲካ ወጡ። የህዝብም ትዝብት አደረባቸው።
በርካታዎቻችን በምዕራብ የሚዲያ ዜና፤ ትምህርትና ፕሮፓጋንዳ ስላደግን የነዚህ አገራት ፖለቲካ ስናይ ፖለቲካ እንደዛ መሆን እንዳለበት ይመስለናል። የናየው ደግሞ የፖለቲካ ውድድራቸውን ነው። ክርክሩን፤ ዘለፋውን፤ ስድቡን፤ ሴራውን ወዘተ። እኛም እንደነሱ ማድረግ እንወዳለን መሰለኝ። ግን ኢትዮጵያ ያለችበት ቦት፤ ለረዥም ዓመታት ያለችበት ቦታ፤ ገና የአገር ፖለቲካ ግንባታ ላይ ናት። ብዙሃኑም ልሂቃኑም የፖለቲካ መደቦቻችን እስካሁን በእምነት የተመሰረተ አገራቷን ምን መምሰል አለበት የሚል ሰፊ ስምምነት ላይ አልደረስንም። አሁንም ያለው ዋና ስራችን የህ ነው። አዎን ህገ መንግስት አለን ግን ሰፊው ርአይና ስምምነት የለንም። ነገ ኢህአዴግ ከስልጣን ቢወርድም ይህ ስምምነቱ ስለሌለ ሁከትና አብዮት ይከተላል።
በዚህ ምክንያት ሁላችንም፤ ምሁራን፤ ብዙሃን፤ ፖለቲከኛ፤ የመንግስት ሰራተኛ፤ ወዘተ ትኩረታችን ወደ አገር ግንባታ መቀየር አለበት። ይህ ማለት ከታች የተጠቀሱትን ለአገር ግንባታ አስፈላጊ የሆኑትን ብሃሪያት፤ ተግባሮችና ልምዶች ከራሳችን ጋር መዋሃድና በዚህ አስተሳሰብ ወደ ፊት መራመድ።
ስምምነት፤ አንድነት፤ መግባባት፤ ህብረት፤ መተማመን፤ በስነ ስረዓት መነጋገር፤ ውይይት፤ ቅራኔን መፍታት።
የሚቀጥለው ጊዜ አንድ ሰውን ወይም ቡድንን መዝለፍ ወይም መስደብ ካሰኘን ቆመን እናስብ። የፖለቲካ ውድድር ውስጥ አይደለንም። እንደዚህ አይነቱ ባህሪያት ታሪካችን እንደሚያረጋግጠው ሁላችንንም ጠርጎ ገደል ውስጥ ያስገባል አገራችንን ያፈርሳል። በሰላም እየተከባበርን እየተማመንን ነው መወያየት ያለብን። ይህ የሁላችንንም ጥቅም ያስከብራልና። ይህንን ብቻ ተግባራዊ ካደረግን አለ ምንም ጥርጣሬ ታላቅ አገር እንገነባለን ጠላት የምንላቸውም ምንም ሊጎዱንም አይችሉም።

Subscribe to:
Posts (Atom)