Showing posts with label ልማት. Show all posts
Showing posts with label ልማት. Show all posts

Wednesday, 5 September 2018

ልማት ሀገርን አይገነባም!

እስካሁን በሰው ልጅ ታሪክ አንድ ሀገር በ«ልማት» ተመስርቶ ተገንብቶ አያውቅም። ሰዎች ከአንድ መንደር ሲሆኑ፤ የጋብቻ እና የደም ትሥስር ሲኖራቸው፤ ባህላቸው አንድ ሲሆን፤ ለመተባበር እና ለመረዳዳት ብለው በተፈጥሮአዊ በአዎንታዊ መንገድ «ሀገር» ይሆናሉ። ሃብት ፍለጋ፤ ጦርነት፤ ግጭት ወዘተም በአሉታዊ መንገድ በሀገር ምስረታ ሚና ይጫወታል። ግን «ልማት» ሀገር አይገነባም። ትሥሥር አይፈጥርም። ዝምድና አይፈጥርም። ፍቅር የለውም። ከልብ መረዳዳት አይጠይቅም። ሀገር አይገነባም።

ለማስታወስ ያህል የተወሰነ ዓመት በፊት ህዝብን የምርጫ 1997 ችግርን ለማስረሳት፤ «ጠባብ» የጎሳ ብሄርተኝነትን ለመዋጋት፤ መንግስትን ሊጥል የሚችል መሃበረሰባዊ ክፍፍልን ለማስወገድ ኢህአዴግ «ልማታዊ መንግስት» ብሎ አወጀ። ኦሮሞ፤ አማራ፤ ትግሬ፤ ሲዳማ ወዘተ ብሄር ብሄረሰቦች አንድ መሆን ባይችሉም በ«ልማት» ዙርያ አንድነት ይፈጥራሉ ወይንም ግጭት ይቀንሳሉ ተብሎ ነው «ልማት» የታወጀው (https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2016/10/ethnic-federalism-kills-meles.html)። የዚህ የልማት ዘመቻ ደግሞ ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ ነው ተብሎ የሳቸው ምስሎች ከነ ልማት ምስሎች ጋር በማርክሲስት አይነት ስዕሎች በየቦታው ተለጠፉ።

ልማቱ መጣ ኤኮኖሚው በፍጥነት አደገ። ግን ህዝቡ ይበልጥ ተከፋፈለ። ግጭቶች እየጨመሩ እየጠነከሩ ሄደ። ሰላም እና ፍቅር እየጠፋ ሄደ። የግብረ ገብ እጦቱ በአስፈሪ መልክ በዛ አገሩን አጠለቀለቀ (https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/08/blog-post_31.html)። «ልማት» ወደ «ገንዘብ» ተተርጉሞ ለገንዘብ ብለን እናታችንን የምንሸጥ ስባዊነት-ቢስ ማህበረሰብ ሆንን። ይበልጥ ተከፋፈልን። «ልማት» የሚለው መፈከር አልሰራም።

ግን አሁንም ስለ «ልማት» እንሰማለን። «ለምን አንድ ሆነን ተፋቅረን ሁላችንም ወደ ልማት አንሄድም?» ይባላል። «ሀገራችንን በጋራ እናሳድጋት» ሲባል እንሰማለን። «አንድ ከሆነን ሀገራችን እንደ ሌሎች ሀገራት ትበለጽጋለች!» ይባላል።

አዎን ልማት እና እድገት አይከፋም። ግን ልማት ሀገር እና ህዝብ አያደርግም ወደፊትም ሊያደርግ አይችልም። ሀገር እና ህዝብ የሚያደርገን «ፍቅር» እና «ሰላም»፤ «እውነተኛ ዝምድና እና ትሥስር»፤ «መደጋገፍ» እና «መረዳዳት»፤ «አባቶችንና ተውፊትን በጋራ ማክበር» ወዘተ። እነዚህ ጊዜያዊ ሳይሆኑ ዘላቂያዊ ነገሮች ናቸው። ልክ እንደ ሃብት ቤተሰብን እንደማይፈጥር እንደማይገነባ ሀገርንም አይፈጥርም አይገነባም።

ይህን ስለተረዱ ነው ጠ/ሚ አብይ አህመድን ታላቅ የሚያረጋቸው። የሳቸው ትኩረት በጊዜያዊ አላፊ ትናንሽ ነገሮች ሳይሆን በከፍ ያሉት (higher) ነገሮች ነው። ህዝባችን ከልማት በላይ ደስታ እንዲኖረው ነው የምፈልገው ብለዋል። ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያው ትውፊታዊ አመለካከት ነው። ኢትዮጵያዊ ከገንዘብ፤ ምቾት፤ ሃባት ወዘተ ይልቅ ፍቅር፤ ሰላም፤ ፍትህ ወዘተን ያስቀድማል በሃይማኖትን እና ትውፊቱ ምክንያት። ለዚህም ነው የጠ/ሚ አብይ መልዕክት ምዕራቢያዊያንን በሚያስገርም ሁኔታ ህዝባችንን ያስደሰተው።

ስለዚህ የኛ መሪዎች እና ፖለቲከኞች እንዲሁም እኛ ብዙሃን «ልማት» የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ ላሁን ብንተወው እና ትክክለኛ ቦታው ብንሰጠው ጥሩ ይመስለኛል። ፍቅር እና ሰላማችንን እናዳብር። ክፍፍሎቻችንን በግልጽ እና በትህትና እንወያይ። ይቅርታ እንባባል እርስ በርሳችን እንቆርቆር። ሀገርን እንገንባ። እዚህ ላይ እናተኩር። ከዛ በኋላ ልማት እንደ ሁለተኛ ምርት (byproduct) ይመጣል። ባይፈጥንም ፍቅራችን ያኖረናል።

Monday, 10 October 2016

የትግሬ አድሎ

2009/1/29 .. (2016/10/9)

(pdf)

ፖሊሱን ምንድነው የሚያበሳጭህ ብዬ ስጠይቀው እንደዚህ ይለኛል«አድሎው በዛ፤ እድገት «ለነሱ ሰው» ብቻ ነው፤ ምርጥ ቦታ «ለነሱ»የማይፈለግ ስራ ለሌላው። አይን ያወጣ ነው እኮ! ሰዉ እጅግ መሮታል»

ለመንግስት እቃ የሚያቀርብ ነጋ እንደዚሁ ብሎ ይነግረኛል«ኮንትራቶች አገኛለሁ። ግን ምርጥ ኮንትራቶች «ለነሱ» ብቻ ነው። ጊዜ ቢያሳልፉም ጥራት ቢያጎሉም ምንም አይባሉም እንደ በፊቱ አይደለም፤ አሁን አይን ያወጣ ሆኗል፤ ሰ በጣም ተናዷልና ሁኔታው ያስፈራል»

ባለ ሀብቱም እንደዚሁ አይነት እሮሮ ያሰማኛል«አዎ ደህና መሬት ማግኘት ለሁ ግን ምርጥ ቦታዎቹ «ለነሱ» ሰው ነው። አንድ ቆንጆ ቦታ አግንቼ ከፍተኛውን ብር ተጫርቼ «ለነሱ» ተሰጠ። እጅግ ተበሳጭቻለሁ። አይን ውጣ አድሎ ነው» ይለኛል። በተዘዋዋሪ ይህ ባለ ሀብት ከ ፓርቲው ጋር በሚያስፈልገው ደረጃ ግንኙነት አለው

የዩኒቨርሲቲ ተማሪውም ከትንሽ ውይይት በኋላ ወደዚሁ አርእስት የገባል። «የነሱ» ተማሪዎች የሚያገኙትን እርዳታ ብታይ። ትርፍ ትምህርታዊ ምክር፤ ሳምፕል ፈተናዎች፤ ከነሱ አስተማሪዎች በትርፍ ግዜ እርዳታ» ዝምብሎ ከማማረር ለምን እናንተም እንደዚህ አታረጉም ብዬ ጠይቀዋለሁጥያቄዬን ያልፈዋል፤ ስለ «እነሱ» ነው ማውራት የሚፈልገው

«እነሱ» ማን እንደሆኑ ሁላችንም እናውቃለን። አዎ በትክክሉ ለመናገር የኢህአዴግ አባላትና አደርባዮቻቸው ናቸው። ግን ሰ«እነሱ» ሲል ባጭሩ ትግሬዎች ማለቱ ነው፤ አድሎ ሲል የትግሬ አድሎ ማለቱ ነው።

እውነቱን ለመናገር የትግሬ አድሎ ገርሞኝም አያቅም። የመንግስታችን አወቃቀር ይህን አድሎ የሚያስከትል ነውየአንድ ፓርቲ አገዛዝ ነው ያለንፖለቲካ ተቀናቃየለም አይፈቀድምም። እንኳን የነፃ ምርጫ ከፊል ነፃ ምርጫ የለም። በዚህ አይነት «አውራ ፓርቲ» አገዛዝ ሁልግዜ ለፓርቲ አባላትና አደርባዮቻቸው ከፍተ አደሎ ይኖራል። በደርግ ዘመን ለኢሳፓ አባላት አድሎ አልነበረም? በኃይለ ስላሴ ዘመን ከቤተ መንግስት ግንኙነት ያላቸው የተሻለ ያገኙ አልነበረም? የዛሬውም እንደዚህ ነው።

ይህን ሃሳብ ስናገር አብዛኛው አዳማጭ ይገረመዋል«የዛሬው አድሎ ግን በዘር ነው እኮ» ይሉኛል። አዎን የዘር አድሎ ነው ግን ህይ የዘር አድሎ፤ ማለት የትግሬ አድሎ፤ መኖሩ ልንገረም አይገባም። ሁላችንም የኢህአዴግ ታሪካዊ አመጣጥን እናውለን። ከመጀመሪያው ህውከኢህአዴግ ከፍተኛ ኃይል ያለው ፓርቲ ነበር ዛሬም ነው፤ ቶር ስራዊቱንና በተለይ ደህንነቱን እንደሚቆጣጠር እናውቃለን። ደግሞ በአንድ ግንባር ወይም ፓርቲ አገዛዝ ከዛ ፓርቲ ውስጥ ኃይል ያለው ቡድን ይበልጥ ስና አድሎ ይታይበታል! ለምን ቢባል ሙስናና አድሎ ዋና የኃይል ማከማቸትና ማንጸባረቅ መንገድ ናችሀው። ምርጫ ወይም የፖለቲካ ውድድር ሰለሌለ ኃይል በዚህ መልኩ ነው የሚከማቸው። በአውራ ፓርቲ አገዛዝ ሌላ አካሄድ ሊኖር አይችልም

ይህ ሁሉ እያልኩኝ ሳለ ኔ አመለካከት የትግሬ አድሎ ካሉት የሀገራችን የፖለቲካና ህብረተሰባዊ ችግሮች ንሹ ነው። ለኢህአዴግ ግን ዋናው ችግ ነው! ይህ እንዴት ይሆናል? ለኔ ዋናው ችግር የአንድ ፓርቲ የልማት መንግስት አገዛዙ የህዝቡን የአንድነትና የህብረተሰባዊ መንፈስ እያጠፋ መሆኑ ነው። ከሌሎች ጽሁፎች እንደጠቀስኩት የኢህአዴግ መንግስት ለህዝቡ ያቀረበው ውል እንዲህ ነው፤ ልማት ሰጥሃለሁአንተ ደግሞ በልጣኔም ይሁን በሙስናዬ አትምጣብኝ። በዚህ ውል መሰረት ሰዎች ከመሬታቸው ይፈነቀላሉ። መሬታችሁ ለባለ ሀብት ይፈለጋል እየተባለ ሳንቲም ተሰተው ይባረራሉ፤ ክስ ላይ ባለስልጣኑ ወይም አደርባዩ ጥፋተና ቢሆንም ይረታል፤ ሰዎች ትንሽ ጸረ ኢህአዴግ ነበር ቢናገሩ ይታሰራ ህዝቡ ከፍርድ ቤት ፍትህ አያገኝም ጉቦ ካልሰጠ ውይም ወዳጅ ከሌለው ንብረቱን ስራውን ወዘተ ያጣ ይችላል። ለኔ እነዚህ ችግሮች ከትሬ አድሎ እጅግ የሚበልጡ ናቸው። ፍትህ፤ ነፃነት፤ ወዘተ አለመኖራቸው ነው ዋናው ችግር። ሁለተኛ ደረጃ ችግር የማንም አድሎ። ሶስተኛ ደረጃ ችገር የትግሬ አድሎ ነው

በተዘዋዋሪ ባለንጀራችን መሬቱን ሲቀማ፤ አለ አግባብ ሲታሰር፤ ፍትህ ሲያጣ፤ ወዘተ ማንኛችንም ዞር ብለን እንርዳህ አንለውም። አይዞህ ብለን የገንዘብም ወይም ሌላ ድጋፍ አንሰጠውምየራሳችንን ኑሮ፤ የራሳችንን«ልማት» ድርሻ እያሳደድን ባለንጀራችን እየተጎዳ ዝም እንላለንምንስት ላይ ጮኸን እንታሰር አደለም። እንርዳው፤ ግን አንረዳውም። ታላቁ ችግር ይህ ነው። እውነቱን ለመናገር ኢህአዴግን በስልጣን እስካሁን የጠበቀውም ይህ መንፈስ ነው።

ግን ይህ መሰረታዊ ችግር እያለ መንግስቱን የሚያናጋው የዘር ችግሩ ነው። ይህ የሰውን አስገራሚ ባህሪ ያሳያ። «ሀገሬን በዚህም በዛም አበላሽ ግን በዘሬ አትምጣብኝ! ጉቦኛና ዘራፊ ሁን ግን በዘር ስም አታድርገው!» እኛ ኢትዮጵያዊያን እንዲህ እንላለን። ያሳዝናል።

ይህን አውቆ ኢህአዴግ የዘራውን ነው የሚያጭደው። ግን ለሀገሪቷ ህልውና አይበጅም። እኛ የ«ትግሬ አድሎ» ሳይሆን ምንም አይነት «አድሎ»ን አንፈልግም ስንል ነው ሀገራችን የሰላም መንገድ የምትጀምረው።