Sunday, 4 November 2018

ጠ/ሚ አቢይ፤ መሬትን የግል በማድረግ የኤኮኖሚ ድል ያገኛሉ

እነ ጠ/ሚ አቢይ የለውጥ ሂደታቸውን ለማረጋጋት፤ አቅም ለመገንባት እና ጥሩ መሰረት ለመገንባት ኤኮኖሚይ እንዲጠነክርላቸው ይፈልጋሉ። ይህን ለማድረግም ብዙ እርምጃዎች እየወሰዱ እናያለን።

አንድ ያልወሰዱት እርምጃ መሬትን የግል ማድረግ ነው። ወይንም ህገ መንግስቱን ሳይቀይሩ በተዘዋዋሪ መንገድ ከተማም ገጠርም መሬት መሸጥ መለወጥ ማድረግ ነው። ልምሻሌ አማራ ክልል እንደተደረገው የረዥም ዓመት ግለሰብ ለግለሰብ ሊዝ (አማራ ክልል 25 ዓመት) መፍቀድ እና ማበረታቻ ህጎች ማርቀቅ ነው። ለምሳሌ 25 ዓመቱ 199 ዓመት ከሆነ de facto ሺያጭ ማለት ነው።

መቼስ ዛሬ መሬት መሸጥ መለወጥ ቢቻል ለኤኮኖሚውም ለማህበረሰብ ጤንነትም ታላቅ ድል እንደሚሆን ማስረዳት አያስፈልገኝም! ምርትን ይጨምራል፤ የገበሬ አቅምን (human capital) ይጨምራል፤ ሙስናን ይቀንሳል፤ የመሬት ዋስትናን (ማለትም የአዕምሮ ረፍት) ይጨምራል፤ መሬት በሚገባው ደረጃ ጥቅም እንዲውል ያደርጋል ወዘተ። ለዝርዝሩ እነዚህን ጽሁፎች  ተመልከቱ፤

፩፤ https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/03/blog-post_47.html
፪፤ https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/10/blog-post_94.html

በመጨረሻ የጎሳ ብሄርተኝነት ፖለቲካ ይህን እርምጃ ለመውሰድ የሚያግድ ከሆነ የጎሳ ብሄርተኝነት የማይበዛበት ቦታዎች እንደ አዲስ አበባ፤ አማራ፤ ደቡብ፤ ሌሎችም ይህን ፖሊሲ ማካሄድ ነው። ጥናቱ ቶሎ ይጀመር። ድሉ ብዙ ነው የሚሆነው።

No comments:

Post a Comment

ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!