ወራት በፊት የሀገራችን ፖለቲካ አውንታዊ ለውጦች እያመጣ እያለ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ እራሱን በቅድምያ አላስተካከልም። ፖለቲካው ከተቀየረ በኋላ በፖለቲከኞች (እነ ጠ/ሚ አቢይ) ግፊት እና ማበረታታት ቤተ ክርስቲያን ወደ ትክክለኛ ሰላም መንገድ ገባች። የቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶስ ከመምራት ፋንታ ተከታይ ሆነ (https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/02/blog-post_15.html)። ያሳዝናል። ግን መከተሉም እራሱ ተመስገን ነው።
አሁን ደግሞ መንግስት የፍትህ እና ሰላም ስራዎች በሰፊው እየጀመረ ነው። ያለፉትን ጥፋቶች ከነ ሙስና እንዲመረመሩ እና ሰላም፤ ፍትህ እና እርቅ እንዲመጣ ሂደቶች እና መዋቅሮች እያቋቋመ ነው። በቤተ ክርስቲያናችን የሚፈፀም የነበረው ኢሰባዊነት እና ሙስና ይታወቃል። የምርመራ ስራዎች በትንሹ የተጀመሩ እንደሆነ ይታወቃል። ግን ስራው ገና ነው፤ መዋቀራዊ አልሆንም እና ለመላው ሀብረተሰብ ግልጽ እንዲሆን አልተደረገም።
አሁንም ቤተ ክርስቲያን ከመምራት ፋንታ ኋላ ቀር ሆኖ እንዳይገኝ። ሙስና እና ሌሎች ኢ-ክርስቲያናዊ ድርጊቶች ቤተ ክርስቲያኗን ማለትም ምዕመኗንም እጅግ እንደሚጎዳ በታሪክ የታወቀ ነገር ነው። የህልውና ጉዳይ ነው። ይህ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን አሁንም መንግስትን ቀድማ እራሷን ማጽዳት አለባት። ለመላው ሀገራችን ምሳሌ መሆን አለባት።
ስለዚህ ቤተ ክርስቲያንን ከሙስና እና ሌሎች ኃጢአቶች የማጽዳታ ዘመቻ አሁኑኑ ጠንክሮ መጀመር አለበት። ይህ ካልሆነ መንፈሳዊ ጉዳቱ እጅግ የከፋ ነው የሚሆነው።
No comments:
Post a Comment
ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!