Thursday, 15 November 2018

ሁለት ተከታታይ አብዮቶች

በ1967 እና 1983 ሀገራችን በአብዮት ክፉኛ ተተረማመሰች። ለነዚህ አብዮቶች የተማሪ ንቅናቄ ይወነጀልበታል። አዎን ይህ ንቅናቄ ታላቅ ጥፋት አለበት። ግን ምንድነው የተማሪ ንቅናቄውን የፈጠረው? ይህን ግልጽ ጥያቄ በቂ አንመረምርም። በጃንሆይ ጊዜ በቂ ከባድ ችግሮች ነበሩ። በውቅቱ ባለመስተካከላቸው ነው ለአብዮት ያበቃን። ግን የጃንሆይ መንግስት ስህተቶችም ምክንያት አላቸው፤ ከዘመነ መሳፍንት ወዘተ የወረዱ ችግሮች ነበሩ።

ግንዛቤአችን በዚህ መልኩ ነው መሆን ያለበት ይመስለኛል። ጥፋትን አንድ ሰው ወይንም ቡድን ላይ መለጠፍ ህፃናዊ አስተሳሰብ ነው። እውነታው የፖለቲካ ችግሮቻችን ብዙ ምክንያቶች አላቸው። ይህን እውነታ ስንረዳ ነው ወደ ትክክለኛ መፍትሄ መሄድ የሚቻለው። በዚህም መንገድ ነው የሌሎችን ብቻ ሳይሆን የራሳችን ጥፋት አይተን መስተካከል የምንችለው።

No comments:

Post a Comment

ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!