ገዱ አንዳርጋቸው ብአዴንም ኢህአዴግም ላደረጉት ጥፋቶች በሙሉ ይቅርታ ጠይቋል። ካሁን ወድያ ለህዝብ ተጠሪ እንሆናለን ህግ አክባሪም እንሆናለን አናሸብርም ብሏል። የ«ለማ ቡድንን» እና አብይ አህመድ ደግፎ ኢህአዴግንም መንግስትም እንዲቆጣጠሩት አድርጓል። የነ አቢይ አህመድ ደጋፊ ሆኖም እየሰራ ነው። ይህ ሁሉ ግልጽ ነው ሁላችንም ያየነው ነው።
ይህ ሁሉ ሆኖ ገዱ ትላንት ተነስቶ የብአዴንን ነባር አመራር አሞገሰ ተብሎ ጩሄት አይገባኝም። ምን ነው ለመፍረድ የምንቸኩለው? ሰውን ይሆን እንዲህ ያለው ብለን እራሳችችን አንጠይቅም? እኛም እንደዚህ በችኮላ እንዲፈረድብን እንወዳለን?
ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከመቀለ ያሉትን እናስታውስ። «ዎርቅ»! «ወልቃይት የዲአስፖራ ጉዳይ አለበት»! አንዳንዶቻችን ወረድንባቸው። ለምን? የሚሉትን ያውቁ ነበር። የነበርውን ህዝብ ለማስደሰት ህወሓቶችን የፖሮፓጋንዳ አቅም ማሳጣት ነበር። የፖለቲካ ስልት ነበር። እና በውቅቱ ሰርቷል። እንኳን መከለ ሄድው የትግራይን ህዝብ አሞገሱ!
እሺ ያኔ ብዙዎቻችን አብይ አህመድን የለማ ቡድንንም በደምብ አናውቋቸውም ነበር። አሁን ግን ለብዙ ዓመት ከኢህአዴግ ውስጥ ታግለው ድርጅቱን እንደተቆጣጠሩት እናውቃለን። ዋዛ አይደሉም ከኛ ድርብ እጥፍ የሚሰሩትን ያውቃሉ እኛ ያማናውቀውን በርካታ መረጃዎች አላቸው። ስለዚህ ቶሎ ከመፍረድ እራሳችንን መቆጠብ አለብን። አላማትች አንድ ስለሆነ መደገፍ አለብን እንጂ ትናንሽ የማንስማማበት ነገሮችን ካደረጉ ማኩረፍ የለብንም። አለበለዛ አብሮ መስራት አይቻልም።
የገዱም እንደዚሁ። እነ በረከትን ያሞሳቸው። እስኪ በቃቸው ቂቤ ይቀባቸው ምን ቸገረን። ለጊዜው ለፖለቲካ ከተመቸው እሰየው። ነው አሁንም እነ በረከትን እንፈራለን ገዱ ከሃዲ ነው ብለን እንፈራለን!! እንደዚህ ከሆነ ችግራችን ካሰብነው በላይ ነው። በስመ ጥርጣሬ ክፍፍል እና አለመረጋጋት አምጥተን እንደልማዳችን ተከፋፍለን ልንገዛ ነው ማለት ነው። እስቲ ትንሽም የፖለቲካ ስልታችንን እናዳብር።
በመጨረሻ ለፖለቲካችን ገዱ ላይ መጮሁ ጥሩ ነው። የድሮዎቹን ምን ያህል እንደሚጠሉ እና ምን ያህል ቦታ እንደሌላቸው ጡረታ ብቻ እንደሚጠብቃቸው ያስረግጥላቸዋል። ግን እኔ የምፈራው ይህ ገዱ ላይ የተሰነዘረው ጩሀት እንደዚህ አይነት ስልታማ ሳይሆን የእውነት ቅሬታ እና ንዴት ነው። ባይሆን ይሻላል። ከነ ገዱ ጋር አብረን መስራት አለብን ስራቸው ጥሩ እስከሆነ ብአዴንንም ገብተን መቆጣጠር አለብን። አማራ አንድ መሆን አለበት። የ50 ዓመት እርስ በርስ መጋጨት መከፋፈል የፖለቲካ ስልት እና ትብብር አለማወቅ ማብቃት አለበት።
የሰላም ክፍሌ ይትባረክ ብሎግ፤ ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለኝን ትናንሽ ሀሳቦች በትህትና አቀርባለሁ። ለስሕተቶቼም በቅድሚያ ይቅርታ እጠይቃለሁ
Showing posts with label ገዱ አንዳርጋቸው. Show all posts

Friday, 13 July 2018
Saturday, 27 January 2018
እንሆ ፑቲኖቻችን!
አንድ አመት ተኩል ይሆናል ርእሱ «ፑቲኖቻችን የት አሉ» የሆነውን ጽሁፍ ከጻፍኩኝ። እንሆ በነ ለማ መገርሳ፤ አቢይ አህመድና ሌሎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ይህንን የፑቲን ሚና ሲጫወቱ እናያለን። እንኳን ለዚህ አደረሰን!
ለማስታወስ ያህል የ«ፑቲን» ብዬ የሰየምኩት የፖለቲካ ሚና ባለው የፖለቲካ ሥርአት ውስጥ ሆኖ ውስጥ ለውስጥ በስውር ራሰን አለጊዜው ሳያጋልጥ ለውጥ ማምጣት ነው። የሩሲያው ቭዲሚር ፑቲንን ታሪክ ለማስታወስ ያህል አቋሙን በሚጠላው የድሮ አለቃው ቦሪስ ዬልትሲን መንግስት ይሰራ ነበር። አቋሙን በሞላ ጎደል ደብቆ እራሱንም የሱ አይነት አቋም ያላቸውን ባልደረቦቹንም ሰውሮ ውስጥ ለውስጥ ተደራጀና የአለቃው ዋና አጋዥ ሆነ። ዬልትሲን ከስልጣን ሲወርድ ጭራሽ ፑቲንን ሾመና እንደሚባለው «ሌላው ታሪክ ነው» ፑቲን የሩሲያን የፖለቲካ ሁኔታ በትክክሉ ገምቶት ነበር፤ እራሱን ከሥረዓቱ ውጭ አድርጎ ምንም አይነት ለውጥ ሊያመጣ እንዳማይችል ገብቶቶ በበር። ይገደል ነበር ወይም ከሀገር ይባረር ነበር። ሌሎችም የሱ አጋሮች ይህንን ተገንዝበው ውስጥ ሆነን በትዕግስት እራሳችንንም ንቅናቄያችንን አደራጅተን ጊዜው ሲደርስ በልጠን እንገኛለን ብለው ወሰኑ። እንዳሰቡት ሆነ።
እነ ለማ መገርሳም እንደዚህ ነው ያደረጉት። ጊዜው ሳይደርስ አጉል የፖለቲካ እርምጃ በመውሰድ ከጨዋታው ከሚፈነገሉ ቀስ ብለው አንገታቸውን ደፍተው ድራቸውንም የፖለቲካ ኃይላቸውንም አጎልብተው አሁን ትልቅ ሚና መጫወት የሚችሉበት ደረጃ ደረሱ። (ሌሎቻችን አክሩፈን ከስርአቱ ውጭ ሆነን ምንም ሳናደርግ እነሱንም ሳንረዳ።)
አሁንም ግን እነ ለማ እጅግ ከባድ መንገድ ነው የሚጠብቃቸው። መአት ተቃዋሚና ጠላቶች አሏቸው ከኢህአዴግ ውስጥ ከህወሓት ውስጥ ከኦህዴድም ውስጥ። ደጋፊዎቻቸውን ማብዛት ተቃናቃኞቻቸውን ማድከም ከባድ ስራ ነው የሚሆነው። ይበልጥ ደግሞ ዝም ያለውንና መሪ ቢስ የሆነውን ብዙሃኑን ማደራጀትና ወደ አንድ አቅጣጫ መምራት እጅግ ከባድ ስራ ነው። እግዚአብሔር ይርዳቸው፤ በነሱ ቦታ መሆን በፍጹም አልመኝም።
እዚህ ላይ ሁላችንም የኢትዮጵያ አንድነት፤ የአገር ብሄተኝነት ወዳጆች ችግራቸውንም አቅማቸውንም በትክክል እንድንረዳ ይገባል። በተፈጠረው ጉዳይ በሙሉ ዘራፍ ብለው አደገኛና ብልህ ያልሆን እርምጃ እንዲወስዱ አንጠብቅ። ያላቸውን የሃይልና የድጋፍ መጠን ያውቁታል። ጉዛዋአቸው ረዥም ነው፤ ማራቶን ነው እንጂ መቶ ሜተር ሩጫ አይደለም።
ለምሳሌ ያህል ወልዲያ በተፈጸመው ኢሰባዊ ድርጊት ተነስተው እነ ገዱ አንዳርጋቸው ይጩሁ ማለት ጥሩ ጥያቄ ቢሆንም ባይጮሁ ወይም እንደምንፈልገው ባይናገሩ አንበሳጭ። ትእግስት፤ ትእግስት። ከአንደኛ ወደ አራተኛ ማርሽ መሄድ አደገኛ ነው። እነዚህ ሰዎች በፓርቲዎቻቸው ያላቸውን ተሰሚነትና ኃይል ቀስ ብለው ያደራጁ። ከፍ ባሉ ቁጥር ይበልት ደፋር የሆነ እርምጃ መውሰድ ይችላሉ። ግን ደረጃውን አንድ በአንድ መውጣት አለባቸው። ልክ ፑቲን እንዳደረገው።
በመጭረሻ ላስታውሳችሁ የምወደው እነ ለማና ሌሎች በስልጣን ላይ ስለሆኑ የሚታዩ ቢሆንም ከነሱ በታች ብዙ የነሱን አቋም የሚጋሩ አሉ። አለነሱ ብቻቸውን ሊሰሩ አይችሉም ነበር። እነሱም እንደ እባብ ብለህ መሆን አለባቸው። ሌሎቻችንም ከኢህአዴግ ውጭ ያለነው እራሳችንን ገምግመን ውስጥ ገብተን ብንረዳቸው ይመረጣል።

Saturday, 25 November 2017
አቶ ለማና አቶ ገዱ
ይህ የአቶ ለማ መገርሳና የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ንግግር ግዥ ፓርቲው ኢህአዴግ ውስጥ የአንድነት አስፈላጊነትና የኦሮምኛ ከአማርኛ እኩል የሀገር ቋንቋ መሆን ጥቅም (ይህንና ይህን አንብቡ) የሚረዱ ወገኖች እንዳሉ ብቻ ሳይሆን ይህን ጉዳይ ለረዥም ጊዜ ያሰላሰሉበት እንደሆነ ዪገልጻል። አቶ ለማና አቶ ገዱ ለንግግሮቻቸው ሊመሰገኑ ዪገባል።፡ ያንጸባረቁት አቋም ጥሩና ተስፋ ሰጭ ነው።
ሆኖም ወደ ተግባር ስንሄድ ይህን ልውጦች፤ አንድነት፤ መልካም አስተዳደር፤ ህብረተሰባዊ መሻሻሎች ብተለይ በወጣቶች ስነ መግባር ዙርያ፤ የወላጅና የሃይምናኦት መሪዎች በልጆቻችን ጤንነትና ደህንነት ሃላፊነታቸውን መዋጣት፤ ወዘተ አቶ ለማና አቶ ደጉ ሊፈጹሟቸው ይችሉ ይሆን?
አይችሁሉም ወይም እጅግ ይቸገራሉ አንዳንድ መሰረታዊ መዋቀራዊ ለውጦች ከሌሉ። እነዚህ ችግሮች ዛሬ ያሉት በግለሰብ ድክመቶች ብቻ ሳይሆኑ በመዋቅር ድክመት ነው። በተለይ የአውራ ፓርቲ ፖለቲካ ስርአት ለውቶችን እጅግ አፍኗል። ሌላው በዋንነት ሁለተኛው ችግር በኢህአዴግ ውስጥ የህወሃት የበላይነት መጠን ነው። እነዚህ ሁለቱ ነገሮች በመጠኑ መስተካከል አለባቸው።
የመጀመሪያውን ለማስተካከል ለባለስጣን («ህዝብ ተወካይ») ምርጫዎችን በመጠኑ ነጻ መደረግ አለበት። ሙሉ ነጻነት እንደማይሆን፤ ከአውራ ፓርቲ አገዛዝ ጋር እንደሚቃረን እረዳለሁ። ግን አውራ ፓርቲ 100% ማለት አይደለም። 100% ይባለስጣን ችለተኝነት ያመጣል። ቢሰርቅም ስልጣኑን ለማይሆን ነገሮች ቢጠቅምም ምንም አይደርስብኝም ብሎ። ግን ከስልጣን መውረድ የተወስንም ቢሆን እድል እንዳላቸው ሲረዱ ጥንቃቄ ይጨምራሉ። ስለዚህ ከ 100% ወደ 80 ወይም 70ም አስፈላጊ መሰለኝ።
ሁለተኛው ጉዳይ ይከብዳል። ከብአዴን ኦህዴድና ሌሎቹ ጅግንነትም ብልጠትም ይጠይቃል። ከህዝባቸው ጋር ያላቸውን ቅርበት ማጠናከር ግድ ነው። ይህ ነው ኢህአዴግ ውስጥ ስልጣናቸውን የሚጎለብተው። አሁንም ላለፉት ሶስት ዓመታት የዚህን ፍንጭ እያየን ነው ነገር ግን መጠንከር አለባቸው። መልካም አስተዳደር ለነሱ የህይወትና ሞት ጉዳይ ነው። መልካም አስተዳደር አቋማችንና ግባችን ነው ብለው ቢይዙትና በዚህ ጉዳይ ቆራጥ ቢሆኑ ከህዝቦቻቸው ጋር አንድነት ያመጣሉ። በዚህ ጉዳይ እጅግ ታላቅ ሳ መሰራት አለበት።
በተዘዋዋሪ ከላይ የጠቀስኩት በሙሉ ይሚቻል ነገር ነው። ደም አያፈስም ጦርነትም አያስነሳም። ትንሽ ብልጠት ብቻይ ነው የሚያስፈልገው። ማንንንም አይጎዳም ከሙስናና ጎጂ አስተዳደር መሪዎች በቀር። አይ፤ ማድረግ የሚቻል ነው።
እግዚአብሔር ይርዳቸው። እኛንም ከዳር ቆመን አንገታችንን ደፍተን የምንታዘበው ወይም የምናጨበችበው የምናዝነውም ከዳራችን ወደ መሃል ገትብተን የመፍትዬው አካል እንድንሆን ይርዳን!

Labels:
ህወሃት,
ለማ መገርሳ,
መልካም አስተዳደር,
ሙስና,
ስልጣን ክፍፍል,
ብአዴን,
ኦህዴድ,
ገዱ አንዳርጋቸው
Subscribe to:
Posts (Atom)