Showing posts with label መጠላለፍ. Show all posts
Showing posts with label መጠላለፍ. Show all posts

Saturday, 30 March 2019

ጥልፍልፍ ጥልፍልፍ...

https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/09/blog-post_21.html

ብርሃኑ ነጋ፤ እስክንድር ነጋ፤ በለጠ ሞላ (አብን)፤ ኤርሚያስ ለገሰ፤ «የአቢይ ደጋፊዎች» አንድ የሚያደርጋቸው የዜግነት ፖለቲካ መሻታቸው ነው። ይህ ታላቅ አንድነት ነው። ልዩነቶቻቸው ከታክቲክ ብዙ አያልፍም። ግን በዙዎቹ ለጋራ እምነት እና ጥቅማቸው ጠንክረው አብረው ከመስራት ፋንታ እርስ በርስ በትናንሽ ጉዳይ መቃረን እና መጣላት ይመርጣሉ። እንሆ አሁንም ግዙፍ የአንድነት ድርጅት አላቋቋምንም! ይህ ነው የመጠላለፍ ፖለቲካ definition።

ንስሀ ያስፈልገናል። የመጠላለፍ ደዌ እንዳለን አምነን ልናስወግደው ይገባል። የ40 ዓመት የህፃንነት ፖለቲን አቁመን ወደ ጥንት አባቶቻችን ብስልነት እንመለስ።

Thursday, 6 December 2018

የ «መጠላለፍ» ፖለቲካ

በቅርብ ጊዜ ነው የ«መጠላለፍ ፖለቲካ» የሚለውን አባባል ያወቅኩት። በጣም የወደድኩት አባባል ነው፤ ችግሩን በሚአምር መንገድ የሚገልጽ።

የመጠላለፍ ፖለቲካ ሲባል የሚታየኝ የአንድ የኳስ ቡድን ተጨዋቾች በግጥሚአ መሃል እርስ በርሳቸው ላይ «ፋውል» ሲሰሩ እና ሲጠላለፉ ነው! የሌላው ቡድን ተጨዋቾች ገርሟቸው በንቀት ያመለከቷቸዋል!

አንድ ተጨዋች ከአሸናፊ ቡድን መሆን ይጠቅመዋል። የተጨዋቹን ዋጋ ማለትም ደሞዝ እንዲጨምር ያደርጋል። ስለዚህ የእያንዳንዱ ተጨዋች ጥቅሙን የሚያስከብረው ቡድኑ እንዲያሸንፍ በማድረግ ነው። ግን ተጨዋቾቹ ይህን አይገነዘቡም። ምናልባት ከባልደረቦቻቸው ጋር ትናንሽ ጸቦች አላቸው። በነዚህ ትናንሽ ጸቦች ምክንያት ያላቸው ንዴትን ለመወጣት ብለው ጥቅማቸውን ይጎዳሉ። ቡድናቸው እንዳያሸንፍ ያደርጋሉ!

ፖለቲካችንም እንዲሁ። እጅግ የሚያማርረኝ የፖለቲካ ታሪካችን የኢትዮጵያ ብሄርተኞች ፖለቲካ በተለይ ከ1967 በኋላ ነው። ብዙ ጽሁፎች ስለኛ የኢትዮጵያ ብሄርተኞች አሳዛኝ ታሪክ ጽፍያለሁ። ከኢዲዩ ጀምሮ እስከ ቅንጅት ከዛም አልፎ ታሪካችን የ«መጠላለፍ ፖለቲካ» ነው። ከሁሉም ታሪክ በላይ ይህንን በደምብ የሚገልጸው የቅንጅት ታሪክ ነው። የቅንጅት አመራርም ተከታዮችም እስክንቆሳሰል ተጠላለፍን! በአስርት ሚሊዮን ሰው የተደገፈውን ድርጅት አፈረስን።

ብዙዎቻችን ደጋግመን ከነህ ከመጠላለፍ ታሪካችን እንማር እንላለን። መቼም አይደገም እንላለን። በመጠላለፍ ኢትዮጵያን ወደ አደጋ ጫፍ አድርሰናታል። እግዚአብሔር ጥፋት ይበቃችኋል ብሎ አቢይ አህመድን ልኮልናል። የህን የመጨራሻ እድላችንን በአግባቡ እንጠቀምበት።

https://asfawdarguemeshal.blogspot.com/2018/09/blog-post_21.html