Monday, 27 November 2017

ማንን እንሰዋ

በ2012 ጠቅላላ ስብሰባቸው የቻይና ኮምዩኒስት ፓርቲ መሪዎች ለህልውናቸው ብለው በሙስና ላይ ታላቅ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ተረድተው የእርምጃ ውሳኔ ወሰዱ። እርምጃቸው ሺ ዢንፒንግን  መሪ (ፕሬዚደንት) መሾምና የጸረ ሙስና «ሚኒስቴር»፤ ክፍል ወይ ቢሮ ሳይሆን ሚኒስቴር» ማቋቋም ነበር። ፕሬዚደንት ሺ ሙስናንና ጸረ መልካም አስተዳደርን እዋገለሁ ዋናው ጉዳዬም አደርገዋለሁ በማለት ለምርጫ ቀረበ። የኮምዩኒስት ፓርቲ ሹማምንት ይህን አውቀው ተስማምተው መረጡት።

ልምን? የጸረ ሙስና ዘመቻ እራሳቸውን ሊጎዳ ሊያከስር ሊያሳስርም እንደሚችል እያወቁ እንዴት የጸረ ሙስና ዘመቻ እንዲካሄድ ፈለጉ? ምክነያቱ ሙስና ፓርቲውን (አባላቱን) እጅግ እየጎዳና ህልውናውን ሊያጠፋ እንደሚችል ስለተረዱ ነው። የተለያዩ መሪዎቻቸውም በዪፋ እንደዚ ብለው ግመው ተናግረው ነበር፡ « ፓርቲአችንም ሀገራችን በሙስና ምክነያት ሊፈርሱ ይችላሉ» ብለዋል።

ስለዚህ ፓርቲው ፈርሶ ሁላችንም ከምንሞት ሙስናን ቀንሰን ህዝባችንን አባብለን ፓርቲው ይትረፍ አብዛኞቻችን እንትረፍ ግን አንዳንዶቻችን በተለይ ሙስና ውስጥ እጅግ የሰመጡት ደግሞም የማንፈልጋቸው ባልደረቦቻችን ይውደቁ ይታሰሩ። ይህ ነበር የቻይና ኮምዩኒስት ፓርቲ ሹማምንት አስተሳሰብ ፕሬዚደንት ሺን ሲመርጡት። ሰውነታችን ሙሉ በሙሉ ከሚሞት ትንሽ እንድማ ነው።

ከመረጡት በኋላ ሃይሉን ማንቀሳቀስ ጀመረና አብዛኛው ካሰበው በላይ ደም ፈሰሰ። ብዙ ሰው ተሰወ። እንግዲህ እንደዚህ አይነቱ ሰፊ እቅድ ሁልግዜ እንደተጠበቀው አይሄድም። ሆኖም ፕሬዚደንት ሺ ተእልኮዋቸውን በሞላ ጎደል አሟሉ።

እንዲሁም በኢትዮጵያ ከህወሃት ጠቅላላ ስብሰባ የሚካሂደው በችይና ኮምሁኒስት ፓርቲ 2012 ስብሰባ የተካሄደው ነው። ሙስና እየገደለን እንደሆነ እናውቃለን፤ ሙስናን ማጥፋት አለበን፤ ግን ከማህላችን ማንን እንሰዋ?! ፖለቲካው በዚህ ዙርያ ነው። ስብሰባውም ሳምንታት የሚፈጀው ለዚህ ነው! ህወሃት መትረፍ ከፈለገ ይህን እርምጃ መውሰድ አለበት ግን ውሳኔው ከባድ ነው።

በኔ ሚስኪን እይታ የተወሰኑ ዋና ሹማምንት መውደቅ አለባቸው። እስር ይሁን በሙስና የተገኘውን ሃብት መንጠቅ ይሁን ተገቢውና ውጤታማ እርምጃ አላውቅም ግን ህዝቡ ይህን ይጠብቃል። መዋቀሩም ይህ መድሃኒት ያስፈልገዋል። የወደፊት ሙሰኞችን ተጠንቀቁ ይቅርባትሁ የሚለው ምልእክት በትክክል የሚደርሳቸው ታላላቅ ሹማምንት ከወደቁ ብቻ ነው።

ከዛም ቀጥሎ ግን ከዚህ በፊት እንደጠቀስኩት የሙስናን ደረጃ በቋሚነት ዝቅ አርጎ ለመጠበቅ የ100% መመሪያውን ኢህአዴግ መሰረዝ አለበት። ከፌደራል ምክር ቤት እስከ ቀበሌ የኢህአዴግ ሹማምንት ስራውን በደምብ ካልሰራ በህዝብ ድምጽ ብልጫ ከስልጣን ሊወርድ እንደሚችል ማወቅ አለበት። ይህ ነው ዋናው የሙስና መቋቋሚያ መንገድ።

No comments:

Post a Comment

ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!