Showing posts with label Nassim Taleb. Show all posts
Showing posts with label Nassim Taleb. Show all posts

Tuesday, 2 October 2018

The Black Swan - አንብቡት!

ተሳስቼ ይሆናል እንጂ የኢትዮጵያዊ ምሁራን ባብዛኛው ከምዕራብ ዓለም ዘወትር ትምሕርት ነው (mainstream academia) የሚማሩት። የሚነከሩበት ልበል?

ለማንኛውም በዚህ ምክንያት ይህን «ብላክ ስዋን» ("Black Swan") የሚባለው መፀሃፍን ብዙዎች ያነበቡት አይመስለኝም። አንብቡት! እጅግ አስተማሪ ነው። ያው እንደማንኛውም ነገር ዘሩን ከእንክርዳዱ መለየት ያስፈልጋል ግን አንብቡት!

እኔ ያነበብኩት ገና ሲወጣ ወደ 11 ዓመት በፊት ነው። የገረመኝ ነገር ምን ያህል ከኢትዮጵያ ባህላዊ አስተሳሰብ እንደሚሄድ ነው። ጸሃፊው ሊባኖሳዊ አሜሪካዊ ሆኖ አስተሳሰቡ በኦርቶዶክስ ሃይማኖቱ የተገራ ይመስላል። መጸሃፉ ስለ ሳይንስ እና ፍልስፍና ቢሆንም ይህንን ዝንባሌ በደምብ ያሳያል።

አንብቡት!

https://www.amazon.com/Black-Swan-Improbable-Robustness-Fragility/dp/081297381X/ref=sr_1_1?s=books&ie=UTF8&qid=1538495240&sr=1-1&keywords=black+swan&dpID=41w4yuUG1mL&preST=_SY344_BO1,204,203,200_QL70_&dpSrc=srch

Tuesday, 25 September 2018

Detached commentators masquerading as patriots

የ«ኢትዮጵያዊነት» ልሂቃኑ "pessimism" አሳፋሪ እና ሃላፊነት-ቢስ ነው። መሪ አልባ ብዙሃኑን «ይቻላል»፤ «ኑ እንደራጅ»፤ «ብዙ ነን» ከማለት ሀገራችን ልትፈርስ ነው እያልን ህዝቡ ከሚደራጅ እና ከሚሳተፍ ቁጭ ብሎ ሰላቢ ነኝ ብሎ እንዲያለቅስ እንገፋዋለን።

የጎሳ ጦርነቱ ሲጀምር ህዝቡ በጎሳ መደራጀቱ አይቀርም ግን too late። ከሁሉም ወገን እልቂት ይከተላል። ከዛ ደግሞ ጀግና ልሂቃኖቻችን I told you so እንላለን። Detached commentators masquerading as patriots። ያሳፍራል። ህዝባችን ይቅርታ ያድርግልን።