ሁላችንም የምናውቀው የድሮ ከንቱ መከፋፈል ባህሪአችን እየቀነሰ እያየነው ነው። የከንቱ እርስ በርስ መጣላትና መከፋፈል ባህሪአችን አደጋ ላይ እንደጣለን እና ከምድር እንድንጠፋ ጫፍ እንዳደረሰን እየገባን ነው። ህወሓትም በዚህ ምክነያት አናሳና ትንሽ ሆኖ እንደገዛን ገብቶን እያመንን ነው።
መቼስ የመንቃታችን አንዱ ምክነያት ያየነው አደጋና የጦርነት ውጤት ቢሆንም መንቃታችን ጥሩ ነው። ግን በፍጹም መዘናጋት የለብንም። የከንቱ መከፋፈል ባህሪአችን ከውስጣችን ጨርሶ እስኪጠፋ ተግተን መታገል አለብን። አማራጭ እንደሌለን ከልባችን ማመን አለብን።
አንዱ ማድረግ ያለብን ነገር አንድነትን ዋና መግባር ማድረግ ነው። ከእውነት፤ ጽናት፤ ታማኝነት ወዘተ እኩል የሆነ መግባር መሆን አለበት። ትቢትና አውቃለሁ ባይነትን ነውር ማድረግ። ውሳኔዎችን በጋራ አድርጎ በጋራ መቀበልን ዋና መግባር ማድረግ። የክፍፍልንና እርስ በርስ መጣላትን፤ የጋራ ውሳኔን አለማክበርን ነውር ማድረግ። የህልውና ጉዳይ ነው።
No comments:
Post a Comment
ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!