Wednesday, 30 June 2021

የቶክስ ማቆም ውሳኔውና የጎሳ ብሔርተኝነት አደጋ

ስሜታዊና በፖለቲካ ያልበሰልን ስለሆንን የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ጋር ወግኗል እንላለን። ይህ አመለካከት እጅግ simplistic ነው። በሕብረ ብሔሪዊ ሀገራት የህዝቡ ታማኝነት ከፊል ለሀገሩ ከፍል ለጎሳው/ብሔሩ ነው። ሀገሪቷ ጤናማ (ሰላማዊ) የምትሆነው የህዝቡ ታማኝነት ከጎሳው ይልቅ ወደ ሀገሩ ቢያደላ ነው። ለምን ሲባል የሀገርና የጎሳ ፍላጎትና ጥቅም አልፎ አልፎ ሊለያዩ ይችላሉ። ጎበዝ ፖለቲካኞች ካሉ እነዚህን ልዩነቶች የሳንሳሉና ወደ ሁሉንም የሚጠቅም መንገድ ያመራሉ። ምንም ቢጥሩ ግን አለመስማማት አይቀርም። ስለዚህ ህዝቡ ከጎሳው ይልቅ ሀገሩን የሚያስቀድም ከሆነ፤ ማለት የጎሳ ብሔርተኝነት ስሜት እናሳ ከሆነ፤ በጎሰና በሀገር ያሉት ልዩነቶች በቀላሉ ይፋታሉ። ካልሆነ ግን ሀገሪቷ የግጭት ስፍራ ትሆናለች።

አሁን በትግራይ የምናየው ይህ ነው። ለ57 አመት ለትገራይ ህዝብ የተሰበክለት የጎሳ ብሔርተኝነት ዋጋ እያስከፈለ ነው። ከ 57 አመት በፊት የትግራይ ህዝብ የጎሳ ብሔርተኝነት ስሜት አልነበረውም ማለት አይደለም። ግን ስሜቱ በየጊዜው እየጨመረ ሄደና አሁን ከመጠን በላይ ትግራዊ ጎሳውን ከሀገሩ በደምብ የስቀድማል።

የጎስንነት ስሜት ተቀያያሪ ነው። 69 ዓመት በፊት ኤርትራዊያን ከኢትዮጵያ ጋር እንቀላቀል አሉ። 41 ዓመት በሗላ ከ90% በላይ እንገንጠል አሉ! ፖለቲካ፤ ኤኮኖሚ፤ ግጭት ወዘተ የሰውን ስሜት ይቀይራል። የጎስኝነት ስሜቹን መመለሱ ቀላል አይደለም። ብዙ ጊዜ አይቻልም። 

ሰባት ወር በፊት መንግስት አብዛኛው የትግራይ ህዝብ ልብ የት እንደሆነ መገመት ብቻ ነበር የሚችለው። የጎሳ ብሔርተኝነት ስሜቱ ምን ደረጃ ላይ ነው? ሰላም፤ ፍትህና የኤኮኖሚ እርዳታ ከሰጠነው የሀገሩ ስሜት ከጎሰኝነቱ እንዲያይል ማድረግ ይቻላል ወይ? መሞከሩ ነው የሚያዋጣው ብሎ ወስነ መንግስት። ሞክረና አልቻለም። ወደ ሁለተኛው አማራጭ ዞረ። ብዙ ሰዎች፣ ቤተሰቦች፣ መንዶሮች ዋጋ ይከፈላሉ ልክ እንደ የኤርትራ መገንጠል።

በዚህ ምክንያት በሕብረ ብሔራዊ ሀገራት የጎሳ ብሔርተኝነት እንዳይበዛ መንግስት ሁልጊዜ መጠንቀቅ አለበት። ያለውን የገንዘብ፣ የፖሊሲ፣ የኃይል አቅም በሙሉ ተጠቅም የጎሳ ስሜትና ፍላጎት እንዲከበርና ሀገራዊነት እዲያይል መደረግ አለበት።