Thursday, 5 October 2017

ኢሳት፤ ተስፋ የሚሰጥ ወይም የሚያስቆጥ?

ይህን ቪዲዮ (https://www.youtube.com/watch?v=OUGKE49Lagg) ይመልከቱ። እኔ እጅግ ከምወዳቸው ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ስለ ኦህዴድና በአዴን ለህወሃት ሙሉ ተገዥነት ይተቻል። ቪዲዮውን ካያችሁ በኋላ እስቲ ንገሩኝ፤ ስለሀገራችን ኢትዮጵያ በተስፋ ተሞላችሁ ወይም ቆረጣችሁ? ይህ ለናንተም ለሃገሪቷም ይበጃል አይበጅም? የፖለቲካ ለውጥ ለዘላለም አይመጣም ወይም አንድ ቀን ይመጣል ያሰኛችኋል? ከዚም አልፎ በሀገሬ ለውጥ ለማምጣት ሚና መጫወት እችላለሁ አልችልም፤ የትኛው ስሜት ይይላል?
ከዚህ በፊት ደጋግሜ እንደጻፍኩት፤
1. የትግራይ ተወላጆች በምክላከያ አናሳ ቁጥር ነው ያላቸው። የሌሎች ጎሳ ተወላጆች ከነኦሮሞና አማራ እጅግ አብዛኛው ናቸው። ይህ ሃቅ ነው። ህወሃትም ፍልጎት ሳይሆን ምርጫ የለውም፤ ትግሬ ቢበዛ ለውግያም ለሰላምም አይበጅም። ስለዚህ ትግሬዎች የስልጣን ቦታዎኦች ተቆጣጥረው ሌሎቹ ሌላውን ይዘዋል። ግን ይህ ሁኔታ ለርጅም ጊዜ አይዘልቅም። ሌሎቹ ወደፊት ግድ ሹመት ያገኛሉ ሰላምን ለመጠበቅ።
2. የደህንነቶ የጎሳ ክፍፍል በዪፋ ባይታወቅም ከሸፈቱ ምስክሮች ዘንድ በርካታ ቲግራይ ያልሆኑ ደህንነት ውስጥ እንዳሉ መረጃ አለን። ሆኖም ከሁሉም የመንግስት አካል ደህንነት ነው በህወሃት ታንቆ የተያዘው። ማንኛውም አምባገነን መንግስት ከሁሉም በላይ ደህንነትን ነው ተጠንቅቆ የሚይዘውና።
3. የትግራይ ህብረተሰብ አሁንም የኢትዮጵያ 8% በላይ አይደለም።
እነዚህ ሃቆች የሚነግሩን ህውሃት ኢትዮጵያን የሚገዛት በበርካታ ህዝብ ፈቃድና ተባባሪነት ነው። ግን በዛው መጠን ፈቃደኛውም ተባባሪውም በሙሉ ልቡ አምኖበት ሳይሆን በአቅም፤ በብስለት፤ በመተባብር፤ ወዘተ ጉድለት ነው የሚያደርኩትን የሚያደርጉት። አቅም፤ ብስለት፤ ትብብር በትንሹም ቢጨእር ያለው አገዛዝ በሰላም ይዘየር ነበር። ስለዚህ ይህ ሁኔታ እንዲፈጥር ነው ማድረግ ያለብን።
ለዚህ ነው ከዚህ በፊትም አሁንም የምለው ከነ የሩሲያ ቭላዲሚር ፑቲን አይነቱ እንማር። ፑቲን ከጎጀውን ከሀዲው የልትሲን መንግስት እየሰራ ውስጥ ለወስጥ ጥሩ ስራ እየሰራ ግን ማንነቱን ደብቆ ሃይሉን አከማቸ። ተቃዋሚ አልሆንም። ለምን፤ እንደማያዋጣና እንደምይሆን ገቡንም ለማሳካት እንደማይሆን ተረድቶ ከመንግስት ውስት በስውር መስራቱ ያዋጣልብሎ ሰራ። የሱም ቢጤዎች ብዙ ነበሩ ጉብዝናና ብልጥነታቸውም እንዲአሸንፉ ረዳቸው።
የኢትዮጵያም ሁኔታ እንደዚህ ነው። በደርግ ጊዜ ታላቅ የሆነ የግዥ መደብ ሞተ እራሱንም አጠፋ አቅምም አጣ። አሁን ያለው አማራጭ ከውስጥ ሆኖ መስራት ነው።
ደግሞ ይቻላል። ከላይ እንደጠቀስኩት ህውሃትም ደጋፊዎቻቸውም እጅግ አናሳ ናቸው። ዛሬም እንደሚታየው ተገዥ ፓርቲዎቻቸውን ኦህድድና በአዴንን እንደፈለጉት በዘላቂነት ማሽከርከር አቅቷቸዋል። ስለዚህ ተስፋ አለን፤ ከሰራን። ከመሸሽ ወይም ከማይሆን የፊትለፊት ግጭት መንገድ ከመያዝ ብልጥ ሆነን ከውስጥ ሃገሪትን መያዝ ነው።

No comments:

Post a Comment

ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!