Friday, 5 July 2019

እግዚአብሔር እኛ ኢትዮጵያዊያኖችን እስካሁን ምሮናል፤ ወደፊትም እንዲምረን መጸለይ ነው

Perspective አችን ትንሽ መስተካከል ያለበት ይመስለኛል። ስሜታዊ ሳይሆን ረጋ ብለን ያለንበትን ሁኔታ በረዥም መነጽር እንይ።

ሶስት ዓመት በፊት «ሀገራችን እንዴት ይሆናል?» ብዬ ብጠይቃችሁ እልቂት ነው የሚመጣው ትሉኝ ነበር። ዓመት በፊት የመጣውን አይነት ለውጥ በምንም ተዓምር አናስበውም ነበር። ህወሓት ይጨፈጭፈናል ወይንም በዓብዮት እና ሁከት ይገለበጣል እና ሀገሪቷ ይተራመሳል ነበር አብዛኞቻችን የምናስበው። ግን እንሆ እግዚአብሔር ምሮን አንጻራዊ ሰላማዊ ለውጥ መጣ። እንደ ኢትዮጵያዊያን የማይገባን ምህረት ነው ከእግዚአብሔር ያገኝነው። ለዚህ ምህረት ደግሞ ለዘላለም አመሰግነዋለው።

እናስተውል፤ በሀገራችን ባለፉት 70 ዓመታት ሶስት ዓቢዮቶች ተካሄደዋል። እንኳን ሶስት ዓቢዮቶች እነሩሲያ ከአንድ ዓቢዮት በደረሰበት ጉዳት ለመዳን ከመቶ ዓመት በላይ ወስዶበታል። እንደምናውቀው ዓብዮት ተውልዶችን ነው የሚያጠፋው። ኢትዮጵያ ብዙ ትውልድ አጥታለች። ላለፉት 60 ዓመታት political continuity የላትም ማለት ይቻላል። «ደህና» ሰው ከፖለቲካ እና ከሀገር «ኮሬንቲ» ርቋል። አሁን ያሉን ፖለቲከኞች በአብዛኞች ምራጭ ናቸው (ይህን የምለው ለመፍረድ ሳይሆን ዓቢዮቶቻችን ምን እንዳመጡ ለመግለጽ ነው)።

ይህ ታሪክና ነባራዊ ሁኔታችንን ሰከን ብለን ካየን አሁን ያለንበትን የፖለቲካ ችግር በጣም ትንሽ ሆኖ ሊታየን ይገባል። ከዚህ መቶ እጥፍ የባሰ ነበር መሆን ያለበት።

ተመስገን ለአምላካችን! Glory to God for all things!

No comments:

Post a Comment

ለሀሳብዎ አመሰግናለሁ!