ለማ መገርሳን አላውቃቸውምም ባውቃቸውም ስለማንነታቸው ምንም ማለት አልችልም፤ ይህ የእግዚአብሔር ጉዳይ ነውና።
ሆኖም አቶ ለማ ይሚሰጡትን ንግግሮች አድምጬ እጅግ ጥሩና አስተማሪ እንደሆኑና ለሉላችንም አስፈላጊ መልክቶች እንደሚያስተላልፉ ተገንዝብያለው።
ከባህር ዳር በበአዴን ስብሰባ የተናገሩትን እኚህን ዋና ነጥቦችን ላተንትን፡
1. ትህትና፡ አቶ ለም አንድም እሳቸውም ድርጃታቸውም የሰራውን ነገር አልወደሱም። አንድች። በአንጻሩ ያሉትን ችግሮች አለ ህፍረት ሙሉ በሙሉ ዘርዝረው በተዘዋዋሪ ሙሉ ሃላፊነት ተቀብለዋል። ማን ፖለቲከኛ ነው እንደዚህ የሚለው? ይህ ለሁላችንም እጅግ ታላቅ ምሳሌ ነው። ጣት ከመጥቆም ወደ ራስ ማየት ነው የችር መፍቴ።
2. ሃላፊነት፡ ላሉት ችግሮች ሃላፊነት ወሰደው ለመፍትሄውም ሃላፊነት ወስደዋል። እንደዚህ መደረግ አለበት ወይም እነዛህ እንደዚህ ማድረግ አለባቸው ሳይሆን እንደዚህ ማድረግ አለብን ነው ያሉት። ታልቅ ምሳሌ የሆነ አባባል ነው።
3. ኢትዮጵያዊነት፡ አቶ ለማ የኢትዮጵያዊነት እንዳለና እንዳልጠፋ፤ ለሰላምና ብልጽግና እንደሚያስፈልግ አስረግጠው ተናገሩ። 20 ዓመት በፊት ነውር የነበረውን «ኢትዮጵያዊነት» አኩሪ እንደሆነ ገለጸ። ይህ አባባል፤ በተለይ ከአንድ ኦህዴድ መሪ፤ እጅግ ጥንካሬንና ለእውነትና ሰላም መሻትን ያሳያል። ሌሎቻችንም እንደዚህ ብናስብ ይበጅ ነበር!
4. መልካም አስተዳደር (ሙስና)፡ የመንግስት ሹማምንት «ብቸኛይ ስልጣን» ስላላቸው ነው ችግሩ ብለዋል አቶ ለማ። ሚዛን ከህዝብ ወደ ሹማምንት ከመጠን በላይ አመዝኗል አሉ። ይህ ኢሃዴግን በተለይ የ100% ውሳኔውን የሚተች አነጋገር ነው። ኢህአዴግ ብችኛ ስልጣን ሊኖረው አይገባም። ወይም የፖለቲካ ውድድር በተወሰና ደረጃ ቢሆን ግድ ነው ማለቱ ነው። ከአንድ የኢህአዴግ አመራር አስደናቂ አባባል ነው።
5. ስለ ወጣቶች ሲናገሩ ከፖለቲካ ወደ ማህበራዊ ጉዳይ ከፍ አሉ። ወጣቱን ለቴለቪዥንና ኢንተርኔት መተው ሳይሆን ማሳደግ እንዳለብን አስታወሱን። ከዛም በላይ ግን የወደኩላቸው ቤተሰብ ዋና መሆኑን ማስረዳታቸው ንው። ማንም ኢትዮጵያዊ ምህር ቤተሰብን ከትምህርት በዚህ ማንገድ ሲያስቀድም ስምቼ አላውቅም። ትምህርት ትምህርት ትምህርት ነው የሁላችንም ጭህወት። ግን ትምህርት መሳርያ ነው ቤተሰብ ማንነት ነው የሚለውን ከዚህ በፊት ማንም ሲል ሰምቼ አላውቅም። እጅግ ጠንካራ ምልክት ነው ያስተላለፉት፡
6. በእህአዴግ ዘመን በተለያየ መድረክ የተዘለፉት ምሁራን እንዳ ማንኛውም የህዝብ ዘርፍ ለሃገሪቷ አስፈላጊ እንደሆኑ ሲያሳስበን አቶ ለማ አንድ ጉዳትን ያመጣ ቁስል አዳነ።
7. የጎሰኝነት ለሁሉም ያለው አደጋ አስረግጠው ተናገሩ። ያመጣው ጥላቻና ቅሬታ ለሁሉ ሰውና ለሃገሪቱ ጎጂ መሆኑን ማስረገጣቸው ለሁላችንም ታላቅ ማስተንቀቂያና ምሳሌ ነው። አንድነት ደግሞ የሁሉ ችግራችን ቀድሞ መፍቴ መሆኑን ገለጹ። እውነት ነው። ማንም ችግር አለአንድነት ሊፈታ አይችልም፡
8. በታሪካችን ማፈር ሳይሆን ኮርተን ጥሩውን እንደምሳሌ ወስደን መጥፎውን አስወግደን ግን ሃላፊነቱን በጋራ ተቀብለን መኖራለብን። ይህ ታላቅ የአንድነት መንገድ ነው። ታሪቅ የኔ ወይም የሱ ሳይሆን የጋራ አድረግን መያዝ አንድነትን ይየሚያዳብር ነው።
እግዚአብሄር አቶ ለማ እንዳለው ያድርግለት። ከባድ ስራ ነው ያለው። የኦህዴድ መሪነት ከባድ ስራ ነው ከጎሰኞች ጋር የሚያጋፍጥ ነውና ሚዛን ጠብቆ ነው መራመድ የሚችለው። በዚህ ጉዞአው ሁላችንም ፍርድ ሳይሆን ድጋፍ እንድንሰጠው ይገባል ብዬ አስባለው።